"የችግራችን ሁሉ ምንጭ ሕመንግስቱ ነው፤ ሕገመንግስቱ ይሰረዝ፤ ይሻር፤ ይቀደድ፤ የሚሉ ሀይሎች፤ ሕገመንግስቱን በቅጡ አልተረዱትም፤ አገሪቱ ላይ ሌላ ችግር የሚጋብዙ ናቸው" ልጅ ተክሌ
Posted: 21 Mar 2021, 10:48
ሕገ-መንገስታዊነት አልሰረጸም፤ ሕገ-መንግስታዊነት ይለምልም
16- ኢትዮጵያ ውስጥ ችግሩ ሕገ-መንግስቱ ሳይሆን፤ ሕገ-መንግስታዊነት፤ ወይንም በሕገ-መንግስቱ መሰረት የመመራት ባህል አለመዳበሩ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት፤ ሕገመንግስቱን አልተረዱትም ወይም ሆን ብለው አጣመው ተርጉመውታል፤ ወይም ኢህአዴግ በፈለገው መንገድ ብቻ እየተተረጎመ ስለመጣና፤ ሕገመንግስቱ ማለት ኢህአዴግ/ብልጽግና የሚለው ስለሆነ፤ ሕገመንግስቱ በነጻነት እንዲዳብርና እንዲያድግ እድል ስላልተሰጠው እንጂ፤ ሕገመንግስቱ ያለምንም ማሻሻያ፤ የኢትዮጵያዊያንን መብት የሚጠብቅበት ሀይልና ስልጣን አለው፡፡ ችግሩ፤ ሕገመንግስታዊነት አልዳበረም፡፡ ለምሳሌ፤ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርም ይሁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ባለደራስ ለዛሬ የጠራው ሰልፍ የከለከሉበት አግባብ ሕገ-መንግስታዊ አይደለም፡፡ ሕገ-መንግስቱ በአንቀጽ 30 ያረጋገጠውን፤ ሀሳብን በነጻነት፤ የመግለጽ፤ የመደራጀትና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን የጣሰ ነው፡፡ ይሄ ችግር ደግሞ የሚታየው፤ በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ በቻ ሳይሆን፤ ሌሎች ገለልተኛ ናቸው የሚባሉ ተቋማት ዘንድም ነው፡፡ በዚህ ረገድ ጥሩ ምሳሌ፤ የሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤው የምርጫን መራዘም የተመለከተው የቅርብ ግዜ ውሳኔ ነው፡፡
17- የሕገ-መንግሰታዊ አጣሪ ጉባኤው ውስጥ፤ የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ፤ ሌሎች 6 ታዋቂ ሕግ ባለሙያዎች ቢኖሩም፤ የወሰኑት ውሳኔ፤ ኢህአዴግ ከቀናት፤ ሳምንታት ስብሰባ፤ ግምገማ በኋላ ከሚያወጣቸው መግልጫዎች ያልተለየ ውሳኔ ነው፡፡ እንኳንስ የኢህአዴግ/ብልጽግና ባለስልጣናት ጋር፤ የተማሩ የተመራመሩ የሕግ ባለሙያዎችን፤ የተሰጣቸውን ሕመንግስታዊ ስልጣን፤ በቅጡና የሕዝብን መብት በሚያስጠብቅ መልኩ አልተረዱትም፡፡ ውሳኔያቸው ምንም ይሁን ምንም፤ ቢያንስ የግራ ቀኙን ሀሳብ ማስፈር ሲገባው፤ የመንግስትን ፍላጎት ብቻ ባማከለ፤ እንደውም መንግስት ከጠየቀው በላይ መብት በሚሰጥ መልኩ ምርጫው ላልተወሰነ ግዜ እንዲራዘምና፤ እስከዚያውም ገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ እንዲቆይ ወስነዋል፡፡
18- ስለዚህ፤ የችግራችን ሁሉ ምንጭ ሕመንግስቱ ነው፤ ሕገመንግስቱ ይሰረዝ፤ ይሻር፤ ይቀደድ፤ የሚሉ ሀይሎች፤ አንድም ሕገመንግስቱን በቅጡ አልተረዱትም፤ በሌላም በኩል፤ አውቀውም ይሁን ሳያውቁት፤ አገሪቱ ላይ ሌላ ችግር የሚጋብዙ ናቸው፡፡ ምክንቱም፤ ይሄ ሕገመንግስት የሚቀደደው፤ በኛ መቃብር ላይ ነው የሚሉ ሀይሎች በሌላ አንጻር ተሰልፈዋልና፤ ሁላችንም ካከረርን፤ ትርፉ መጫረስ ነው፡፡ ሕገ-መንግስቱ ተቀዶ እንዲጣል የምንፈልገውን ያህል፤ ሕገ-መንግስቱ ከተነካም ለመሞት የተዘጋጁ እንዳሉ እያየን ነው፡፡፡ በሁሉም ወገን ማክረር እንቀንስ፡፡ ችግራችን ሕገመንግስቱ አይደለም፡፡ ከሆነም፤ በከፊል ነው፡፡ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ሕገ-መንግስታችንን እናስጠብቃለን ብለው በስተርጅና ጫካ የገቡ አሉ፡፡ ለ27 አመታት ያሸነፉን ሕወሀቶች ለጊዜው በሸነፉም፡ መጪውን አናውቀውም፡፡ ፓርቲያቸው እንጂ፤ ሀሳባቸው ግን ተሸንፏል ማለት አንችልም፡፡ ምክንያቱም የሀሳባቸው ወራሽ አያጡምና፡፡
መቀየር ያለበት ምንድር ነው
19- ኢትዮጵያ ውስጥ መቀየር ያለበት፤ ሕገመንግስቱ ሳይሆን፤ የህገመንግስቱ መንፈስና የገዚው ፓርቲዎች አስተምህሮት፤ የካድሬዎቻቸው የተሳሳተ መንፈስ፤ ወይንም ድንቁርና ነው፡፡ በኢትዮጵያ፤ እስካሁን ባብዛኛው እየተፈጸመ ያለው፤ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት ሳይሆን፤ ቀደም ሲል ኢህአዴግ፤ አሁን ደግሞ የተረከበው ብልጽግና የፖለቲካ ርእዮትና መረዳት ነው፡፡ ሕገ-መንግስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ጭቆና ነበር፤ ብሄር ብሄረሰበቦች ባህላችንን እንድናሳድግ፤ በማንነታችን እንዳንኮራ፤ ራሳችንን በራሳችን ማስተዳደር እንዳንችል ማእቀብ ተጥሎብን ኖረናል፤ እንደቡድን ካልቆምን፤ አውሬ ይበላናል ባሉ ቡድኖች አሸናፊነት የተሰናዳ ሰነድ ነው፡፡ የሕገ-መንግሰቱ መንፈስ በዚህ ተቃኘና፤ እንደብሄር ስልጣን የያዙ ሀይሎች፤ የቡድን መብታቸውን ለማስከበር የት ድረስ መሄድ እንደለባቸው ድንበር ጠፋባቸው፡፡ ስለዚህ፤ አነዚህ የቡድን ሀይሎች፤ በማወቅም፤ ባለማወቅም፤ የግለሰቦች መብት ለይ ተረማመዱበት፡፡ ያ ስህተት ነው፡፡ ማስታረቅ ያለብን እነዚህን ሁለቱን ሀሳቦች ነው፡፡ የቡድንና የግለሰብ መብቶች፤ በሕገመንግስቱ እንደተረጋገጠው፤ እንዴት ጎን ለጎን መሄድ ይችላል የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ትልቁ ሕገ-መንግስታዊ ፈተና እሱ ነው፡፡
20- ሕገ-መንግስቱን በሙሉ ማስፈጸም ከጀመርን፤ መብታችንን ማስከበር፤ የማንፈልጋቸውንም አንቀጾች በትእግስትና በሂደት፤ በድርድር፤ ማስለወጥ እንቸላለን፡፡ የኢትዮጵያን ሕገ-መንግስት መተግበር ማለት ደግሞ፤ የትም ክልል ኑሩ፤ የኢትዮጵያዊያን መብት ሳይሸራረፍ መፈጸም/መከበር ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፤ የኢትዮጰያ ሕገመንግስት ክልሎችን ፈጠረ፤ እንጂ ክልሎችን፤ ለዚህ ወይም ለነዚያ ብሄሮች በባለቤትነት አልሰጠም፡፡ ቢያንስ ሕገመንግስቱ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ እንደዚያ አይነት አንቀጽ የለም፡፡ የፌደራል ሕገ-መንግስቱ ይሄንን ስልጣን፤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ፤ ለክልሎች አልሰጠም፡፡ ስልጣን፤ እንደሀብት ስለሚጣፍጥ፤ አንዳንድ ቡድኖች፤ ክልሎች፤ በኢህአዴግ ፖለቲካዊ ትርጓሜ በመታገዝና፤ ሃይ ባይ ስላጡ፤ ያንን ስልጣን ነጥቀው ለራሳቸው ወሰዱ እንጂ፤ የፌደራል ሕገመንገስቱ እንዲህ ያለውን ስልጣን ለክልሎችም ይሁን ለብሄሮች/ብሄረሰቦችና ሕዝቦች አልሰጠም፡፡ የብሄር ብሄረሰቦችን መብቶች የሚደነግጉት፤ አንቀጾች፤ አንቀጽ 2፣ 8፤ 39፤ 47፤ ለየትኛውም ብሄር፤ የትኛውንም ክልል በብቸኛ ባለቤትነት አይሰጡም፡፡ ይሄ አንድን ክልል ለአንድ ወይም ካንድ ለበለጠ ብሄሮች ብቻ በባለቤትነት መስጠት፤ ሕገመንገስታዊ አይደለም፡፡ ይሄ ትልቁ መታረም የለበት ሕገ-መንግስታዊ ሸፍጥ ነው፡፡ ይሄንን በብዙ መልኩ መመልከት ይቻላል፡፡
ክፍል 4: ይቀጥላል; የመጨረሻው ክፍል
የክሎች ብቸኛ ባለቤት ብሄር/ብሄረሰብ የለም፤

Please wait, video is loading...