"ኢትዮጵያ ብልጽግናንና መደመርን ከተቀበለች ከ2010 ወዲህ የጤፍ ዋጋ ከ2500 ወደ 5000 ብር አድጓል። ደመወዜ ምንም ሳይጨምር የኑሮዬ ዋጋ 100% ጨምሯል።" Meron Getu
Posted: 18 Mar 2021, 20:17
አቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን እንደመጣ "ስልጠና" ያልሰጠው ቡድን አልነበረም። ለሁሉም ክልሎች ተወካዮች፣ ለአርቲስቶች፣ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለህግ ባለሙያዎች፣ ለወጣቶች፣ ለሴቶች፣ ለሀይማኖት መሪዎች፣ ለዞን አስተዳዳሪዎች፣ ለክልል ርእሰ መስተዳድሮች፣ ለሚኒስትሮች፣ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለመምህራን እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች ቤተ መንግሥት እየወሰደ ስልጠና ሰጥቷቸዋል። ምናልባት የቀረ ካለ መጨመር ትችላላችሁ።
ከየትኞቹ ሰልጣኞች እንደሆነ ባላውቅም፣ አንድ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት ተጠይቆ ማብራሪያ ሲሰጥ እንዲህ አለ፦ "እኔ ኢትዮጵያ 11 በመቶ አደገች የሚለውን ነገር አልቀበለውም፣ የኢትዮጵያን እድገት የምለካው፣ በህዝባችን ህይወት ላይ በምናመጣው ለውጥ ነው። ህዝቡ የእለት ተእለት ኑሮውን ለመግፋት የማይቸገር መሆኑን መሬት ላይ የሚያረጋግጡ እውነታዎች ከሌሉ 11 ወይም 10 በመቶ አደገች ተብሎ በዓለም ዘንድ ቢወራ እኔ አልቀበለውም" ብሎ ነበር።
ኢትዮጵያ ብልጽግናንና መደመርን ከተቀበለች ከ2010 ወዲህ የጤፍ ዋጋ ከ2500 ወደ 5000 ብር አድጓል። ደመወዜ ምንም ሳይጨምር የኑሮዬ ዋጋ 100% ጨምሯል። የአቢይ አህመድ መንግሥት ኢኮኖሚ ደግሞ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ከ6 እስከ 9% ሲመነደግ ነበር።

Please wait, video is loading...