Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በምዕራብ ትግራይ ብአማራ ክልል መንግስት እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል አስደንጋጭ አሃዛዊ መረጃ

Post by sarcasm » 15 Mar 2021, 19:14

የዘር ማጥፋት ወንጀል አስደንጋጭ መረጃ
======================
በምዕራብ ትግራይ የነበረው አጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ብዛት ከ800,000 - 1,000,000 ነበር። ከነዚህ ውስጥ፣ ከ71,000 በላይ የግራይ ህዝብ ተፈናቅሎ ወደ ሱዳን መሰደዱ ይታወቃል።

የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ያወጣው በጣም አስደንጋጭ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ፣ ከ577,000 በላይ የትግራይ ህዝብ ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅሎ ወደ ሰሜን ምዕራብ እና ሌሎች የትግራይ ክፍሎች ተፈናቅሏል።

በመገባደድ ባለው ሳምንት በሶስት ቀናት ብቻ ከ70,000 በላይ ሰዎች ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅሎ ወደ ሽረ አከባቢ ገብቷል።

18,000 የሚገመት ህዝብ በአማራ ሚሊሻ/ፋኖ/ልዩ ሃይል እንደተገደሉ፣ ከ10,000 በላይ ህዝብ ደግሞ በተለያዩ እስርቤቶች እየማቀቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

በምዕራብ እና በደቡብ ትግራይ፣ የአማራ ክልል መንግስት ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሱት ግፍ ይህ ነው ተብሎ ተቆጥሮ አያልቅም። የግፍ ፅዋ ሞልቶ ፈሷል።
ያ ሁሉ ሆኖም፣ አሁንም የምናስተላልፈው መልእክት የሰላም እና የፍትህ ጥሪ ብቻ ነው።

የአማራ ክልል መግንስት፣ ይህንን አስከፊ ለዘላለም ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል አሁኑኑ በማቆም፣ ሃይሎቹን በሙሉ (ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች በማምጣት ያሰፈራቸው ህዝቦች) በማውጣት ትግራይን ለቆ እንዲወጣ እናሳስባለን። በዘር ማጥፋት ወንጀሉ የተሳተፉ ሀይሎች በሙሉ ወደ ህግ ቀርበው ተገቢው ፍርድ ማግኘት አለባቸው። የተሰረቀው ንብረት ሁሉ መልሱ፣ ለወደመው ንብረት ሁሉ ካሳ ክፈሉ።

የአማራ ክልል መንግስት ታጣቂ ሃይሎች (ሚሊሻ/ፋኖ/ልዩ ሃይል) በትግራይ ያደረሱት ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ ንብረት ማውደም እና ሌሎች ግፎች በተከታታይ ስናስተላልፍ መቆየታችን ይታወቃል። እዚህ 👇👇 አለላችሁ።

https://www.facebook.com/YomePost/posts ... 3157569335