Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ወልቃይትን የካደው ማን ነው? እኛ ወይስ እናንተ? - ኃይለየሱስ አዳሙ

Post by sarcasm » 14 Mar 2021, 19:51

የወልቃይት አማራ መብቱ እንዲከበር እንጅ የወልቃይት ትግሬ መብት እንዲገፈፍ አልታገልኩም

ብዙ ግዜ ወልቃይትን የካዳችሁ የሚል ክስ ይቀርብብናል። እውነት ወልቃይትን የካደው ማን ነው?

እውነት ነው አብዛኛዎቹ የጎጃም ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የትግራይን ጦርነት አልደገፍነውም። እነ ይልቃል ጌትነት ፣ አዲሱ ጌታነህ እና እኔን ጭምር ለአብነት ብትወስዱ ሀገራዊ ድርድር እና ውይይት ይቅደም የሚል አቋም ነው ስናንፀባርቅ የቆየነው። ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ እንድትሸጋገር ሁሉን ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ይመስረት እርቅና መግባባት ይፈጠር የሚል አቋም ይዘናል። ጎጃሜ ከጥንት ጀምሮ የውጭ ወራሪ ጠላትን ለመመከት አንደኛ ነው። በጎጃም የገበሬዎች አመፅ ላይ እንዳየነው ደግሞ በሀገሩ ውስጥም ፍትህ ርትእ እንዲሰፍን ይፈልጋል። ትጉህ ሰራተኛ ነው። ለሀገሩ ቀናኢ ነው። በኢትዮጵያ የከፍታ ታሪክ ላይ ካልሆነ በቀር በቆሸሸው ታሪክ ላይ እጁ የለበትም። ማንንም ጭሰኛ አድርጎ አልገዛም። ማንንም ጠላቱ አያደርግም። ለራሱ አራሽ ገበሬ ነው። አቋማችን ነፃነት ፣ እኩልነትና ፍትህ ርትእ የሰፈነበት ስርአት ማህበርና መንግስት ይኑረን የሚል ነው!!!

ለወልቃይት አማራዎች ላለፉት አመታት ድምፅ ሁነናል። ዛሬ ቀኜ ግራዬ እያሉ የሚያንቆለጳጵሷቸው ሰዎች የአገዛዙ አካል ሁነው የወልቃይት አማራን ሲበድሉ በቋንቋው እንዳይማር ፣ መብቱን ሲገፉ ከቀዬው ሲያፈናቅሉ አዎ ከወልቃይት አማራዎች ጎን ተሰልፈናል። መሰለፍ ብቻ ሳይሆን በባህር ዳር እና በተለያዩ የጎጃም ከተሞች ወጣቱ የህይወት መስዋዕትነት ጭምር ከፍሏል። ታዲያ አሁን ለምን አልደገፍናችሁም?

የእኛ ድጋፍ የወልቃይት አማራ መብቱ እንዲከበር እንጅ የወልቃይት ትግሬ መብቱ እንዲገፈፍ አልነበረም።
የእኛ ትግል ከቀዬው የተፈናቀለው የወልቃይት አማራ ወደ ርስቱ እንዲመለስ እንጅ የወልቃይት ትግሬ ከትውልድ ቀዬው እንዲፈናቀል አልነበረም።
የእኛ መጮህ የሞቱት የተጎዱት የወልቃይት አማራዎች ፍትህ ርትእ እንዲያገኙ እንጅ የወልቃይት ትግሬዎች በጠራራ ፀሃይ እንዲገደሉ አልነበረም።
የእኛ አላማ ወልቃይት ከጭቆና ነፃ እንድትሆን እንጅ ንፁሃን የሚጨፈጨፉባት የደም መሬት እንድትሆን አልነበረም።


ለወልቃይትም ይሁን ለመተከል ለአዲስ አበባም ሆነ ለራያ ሚዛናችን ትክክል ነው። አቋማችን የፀና ነው! በምድሪቱ የሚፈሰው የንፁሃን ደም ይቁም!
አዎ በጠቅላላው የእኛ መስዋዕትነትና ትግል ዜጎች በሰላም ወጥተው የሚገቡባት በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሀብት ንብረት አፍርተው ቤተሰብ መስርተው የሚኖሩባት ነፃ እኩልነት እና ፍትህ ርትእ የሰፈነባት ሀገርን ለማየት ነበር። ታዲያ ማነው ከሃዲው??? በጎ ህሊና ስላለን ዛሬም ለተገፋት እንጮሃለን። አዎ ዛሬም ነፃነት ፍትህ እና እኩልነትን እንሻለን። ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል ብለን በተስፋ እንናፍቃለን። ደሞዛችን ፍትህ ፣ስንቃችን ሀቅ፣ ጉልበታችን ሰብአዊነት ነው!!!

https://www.facebook.com/haileeyesusada ... 6080375232