Page 1 of 1

ጌጅ ኮሌጅ/Gage College እንዴት እውቅና ሊያገኝ ቻለ?

Posted: 11 Mar 2021, 12:39
by Abaymado
ካለኝ መረጃ ፈተና ላይ መኮራረጅ በሽ ነው: የተሰረቁ ስራዎችን እንደራሳቸው ማቅረብ :የተለመደ ነው::

ትዝብት አንድ:
ጌጅ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስመርቃል:: በድግሪም እንደምያስመርቅ ኣቃለሁ:: አንድ የታዘብኩት ነገር ተማሪዎች ፈተና ዛሬ አለ ሲባሉ : ዛሬውኑ ሲጣደፉ ነው ያየሁት:: "ከዚህ ነው ፈተና የሚወጣው ይባላል" ብለው በወረቀት ፕሪንት የተደረገ ኣምጥተው ወደ ሞባይል ጫኑ:: "ወረቀቱን ይዘን ብንገባ አስተማሪ ይይዘናል በሞባይል ይዘን ገበተን እንሰራለን" ሲሉ: እኔ ስመለከታቸው : አንዱ ኣሾልቆ ሲያየኝ አየሁት ::
የዚህን ግዜ እኔ : "የምትኮርጁ ከሆነ ሄጀ እነግራቸዋለሁ " ስላቸው::

አንደኛው" እንዳለ እዛ ያለው የታጠቀ ፖሊስ ነው ይመጣልሃል" ሲለኝ ግዜ ሳቄ ኣመለጠኝ::

በነገራችን ላይ እነዚህ ሰዎች ፖሊሶች ናቸው በማታ የሚማሩ::

ይህ በጣም ትንሽዋ ትዝብት ናት : እንዳለ ሁሉ ነገር በተሰረቀ ነገር ነው የሚጨርሱት:: የሚገርመው በዚህ ዓመት የሚመረቁ ሆነው: ብዙ እንግሊዘኛ ኣያቁም:: ያ ማለት ምን እንደተፃፈ አያውቁትም:: ለምሳሌ involve የሚለውን ኣያቁም:: እና እንዴት ሊገባቸው እንደምችል ግራ ገብቶኛል::

Re: ጌጅ ኮሌጅ/Gage College እንዴት እውቅና ሊያገኝ ቻለ?

Posted: 11 Mar 2021, 13:57
by Abaymado
ትዝብት ሁለት:
ኮሌጁ assignment በወረቀት ፕሪንት የተደረገ ይሰጣቸዋል : እናም በሰዓቱ ስርተው እንዲያስገቡ :ይነገራቸዋል:: እኔን የገጠመኝ አንድ ሴት ይህንን መስራት አቅትዋት ሁሉንም ስሩልኝ ብላ ትጠይቃለች:: በስንት መከራ ተሰርቶ ተሰጣት:: ፈተና ላይ ምን ብላ ሰርታ እንደጨረሰች የምታቀው ራስዋ ናት::እናም በዚህ ዓመት ተመረቀች::

ትዝብት ሶስት:

የሆነ ሰው መጥቶ የአንድን ልጅ ከዩንቨርስቲ የተመረቀበትን ፅሑፍ ለአንድ ሰው ሰጠውና "እንዴት edit ላርገው?" አለው:: "ለምን edit ታረገዋለህ" ሲባል : "መመረቅያ ፁሑፌን በትንሹ ቀይሬ ልመረቅበት" አለ::

ኢንተርኔት ላይ pdf የሆነን ወደ word መቀየር ስለሚቻል :ልጁ ቀየረለት ከዛም ሰውየው በደስታ ጮቤ ረገጠ:: የተሰረቀውን ነው :

ትዝብት አራት: