Page 1 of 1

አለምን ያስደነቀው የኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ትዕይተ ሕዝብ (አዲስ አበባ፣ ዲሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ካናዳ፣ ብራስልስ፣ ጄኒቫ፣ ጀርመን፣)

Posted: 11 Mar 2021, 01:00
by Horus

Re: አለምን ያስደነቀው የኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ትዕይተ ሕዝብ

Posted: 11 Mar 2021, 01:19
by TGAA
ሆሩስ! እንደ ሀዝብ ሁል ግዜም ለመከበር የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለብን፡ ስለዚህ የወያኔ ሆያ ሆዬ ጭፈራ የሚያቆመው የአብይ መንግስት ኮስተር ያለ አቋም መውሰድና በተመጣጣኝ መንገድ መግፋት ሲችል ብቻ ነው፤ አሜሪካ በስሙኔ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደሸቀጥ የሚቸበችብ የወያኔ መንግስት ማጣት ማለት ትልቅ ነገር ነው፤ ነገር ግን ምን ያህል እንደፈለጉት የማንገፋ መሆናችንን ሲያውቁ ይመለሳሉ ፤ በተለይ ደግሞ የኤርትራና የኢትዮጵያ የተቀናጀና ጠንካራ አቋም ገና ሳምንት ያልሞላው ብሊንከን ሲገባው ይስተካከላል፡ አሁን ከኋላ ሱዛንናት የወያኔ ጫወታ የምትጫወተው እንዲሁም አድህኖም ፤ ጠንክር ነው መልሱ፡፡

Re: አለምን ያስደነቀው የኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ትዕይተ ሕዝብ

Posted: 11 Mar 2021, 02:04
by Horus
TGAA
ከምትለው ጋር በመሰረቱ ብስማማም አንድ ምርሳት የሌለብን ነገር አለ ። ሁለት ወይም ሶስት የሆኑ ብዙ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ሰዎች ናቸው ያሜርካንን ዲፕሎማሲ የሚዘውሩት ። ሲወስኑ ሁል ግዜ በሃይል ላይ የተመሰረተ ነው (ፓወር ፕሮጀክሽን)። ስለዚህ አመሪካ ባፍሪካ ያላት ፖሊሲን የምዘውረው ሱዛን ናት ። ብሊንከን ለብዙ ዘመን የባይደን ረዳት ቢሆንም አፍሪካን አያውቃትም ፣ ለዚህ ነው ሶስቱ ሴቶች ሱዛን፣ ጄንዳይ እና ሊንዳ የተባሉ ጥቁር ሴቶች አፍሪካን የሚዘውሩት ፣ እነሱ ደሞ ከተማሪነታቸው ጀምሮ የሚያውቁት ዎያኔን ነው። ባንድ ቃል በግትርነት አሜሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጨማለቅ ያደርጉታል ። ያላቸው ምክኛት የላይ የልዩ ሰባዊ መብት የሚል ነው ። ግ ን ዋና ኣማው ከቻይና እና ሩሲያ ጋር ለመታገል ነው። የኔ ግምት ያሜሪካ ጣልቃ ገብነት እያደገ እንጂ እየቀነሰ አይመጣም ። መዘጋጀትም ያለብን ለዚያ ይመስለኛል ።