እኔ ለብዙ አመት ለሁልም ሳስተምረው የኖርኩት የኢትዮጵያ አላማ፣ የሷ ምክያታዊነት፣ የኢትዮጵያ አጀንዳ በ4 መድቤያቸዋለሁ ።
አንደኛው፤ አገር
የኢትዮጵያ አላማ ብሄራዊ ማለትም አገራዊ አንድነት፣ ብሄራዊ ሰላም ማለትም አገራዊ መረጋጋት ሰርዓት፣ እና አገራዊ ደህንነት ማለተም ብሄራዊ ጥንካሬን ያረጋገጠ አገር፣ ብሄረ አገር መሆን ነው። ይህ በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ ሰዎች አቋም ነው ። ይህ አጀንዳ ከዎያኔ መደምሰስ ጋር እና ከግብጽ ፉከራ በኋላ በጣም በተሻለው ሁኔታ ላይ ነው ።
በተቃራኒው የዘር ወይም የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚፈልጉት፣ የተከፋፈለች ማለትም የተሰባበረች አገር፣ የተቃወሰች ማለትም የተበጠበጠች ስርዓት አልባ አገር፣ ሰላም አልባ ያልተረጋጋች ማለት ደህንነት የሌላት ኢትዮጵያን ማየት ነው ። ይህ ሃይል ከትህነግ ጋር ተሸንፏል፤ ሆኖም አሁንም በግብጽ ድጋፍ የሚንከላውሱ አሉ ።
ሁለተኛው፤ ማህበረሰብ
የኢትዮጵያ አላማ ነጻ፣ ዴሞክራሳዊና ፍትሃዊ ማህበረ ሰብ መፍጠር ነው ። ይህ በኢትዮጵያዊነት እና ዴሞክራሲ፣ በፍትህ የሚያምኑ ሰዎች አቋም ነው ። ዛሬ ምርጫ ውስጥ ያሉት እነ ብልጽግ ና፣ ኢዜማ በሚያድርጉት ውድድር ይታላል ። ነጻ ማለት ነጻ ዜጋ ማለት ነው ። ዴሞክራሲ ማለት በሕዝብ፣ ለሕዝብ የሕዝብ ማለት ነው ። ፍትህ፣ ቅጥነት፣ ልክነት፣ እኩልነት፣ ሚዛናዊነት ያለው ማህበራዊ ሴራ ማለት ነው። ሆኖም ምርጫው ተስፋ አለው።
በተቃራኒው የዘር ወይም የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚፈልጉት፣ የጎሳ ገነንነት ማለት የዘር የበላይነት፣ የጎሳ ቡድን አገዛዝ አምባ ገነንነት፣ የጎሳ የዘር አድልዎ እና የዘር ኤእኩልነትን ማቆም ነው ። ይህን ሰባኪው ትህነግ ፈርሷል። የኦሮሞ ፓርቲዎች ምን እንደ ሚወስኑ ይታያል።
ሦስተኛው፡ ግለሰብ (ሕዝብ)
የኢትዮጵያ አላማ የበለጽገ ማለትም ሃብታም ሕዝብ፣ የተማረ ማለትም አዋቂ ሕዝብ፣ ጤናማ ማለትም ጤነኛ ኢትዮጵያዊ ሕዝብን መፍጠር ነው ። ይህ በኢኮኖሚውም በትህምርቱም በኩል ትልቅ ችግር አለ። ግን አዝማሚያው እድገት ነው ። ይህ እንዲሆን የሽፍቶች ዉጊያ የሱዳንና ግብጽ ትንኮሳን በጥበብ ማፍረስ ፣ ያለም ሃያላን መንግስታትን በዜዴ መያዝ አለብን።
በተቃራኒው የዘር ወይም የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚፈልጉት እነሱ እስከገዙ ድረስ የቆረቆዘ፣ ያልተማረ በስጋዊና አይምሮ ደዌ የተጠቃ ጎሳን መቆጣጠር ነው ። ይህ ሃይል እየደከመ ነው ።
አራተኛ፤ ካልቸር
የኢትዮጵያ አላማ በፈጠራ የተካነ ማለትም አፍላቂ ባህል፣ ራሱን ካካባቢው ያማዘነ ባህል፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ብሄራዊ ባህል መፍጠር ነው ። ይህ እጅግ ወሳኝ አጀንዳ ነው ። ግን ኢትዮጵያ አረንጓዴ ፓርቲ የላትም። ኢትዮጵያ አረንጓዴ የዉሃ ስልጣኔ ነው ስንል ትርጉሙ ያ ነው። ሆህም ይህን ካልቸር የሚመራ፣ የሚያደራጅ ፓርቲ ገና አልተፈጠረም ።
በተቃራኒው የዘር ወይም የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የሚፈልጉት እነሱ እስከገዙ ድረስ የደደበ የድንቁርና ባህል፣ አካባቢና ተፈጥሮ የሚደመስ ስ ባህል፣ መንፈሳዊነትና ሰብዓዊ ሞራልነት የራቀው ባህልን መፍጠር ነው ። ይህ እየደከመ ቢሆንም አሁንም ጠንካራ ነው ።