Page 1 of 1

ይህ አመት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃያልነት የሚታይበት ይሆናል! ለምን?

Posted: 06 Mar 2021, 15:38
by Horus
አል ሲሲ ሱዳን ሄዶ ምን አለ መሰላችሁ? የአባይን ሙሌት ለማደራደር፣ ማለትም ኢትዮጵያን ለማስጎንበስ ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ ያደረገላቸው ሃይሎች የሚከተሉት ናቸው።

አሜሪካ
ያውሮፓ ህብረት
የተባበሩት መንግስታት
ያለም ባንክ
ያፍሪካ አንድነት

ልብ በሉ ባለም ካሉ ሃይሎች ያልጠቀሰው ያረብ ሊግ ብቻ ነው። ያረብ ሊግ በምስጢር ፋይናንስ ስለሚያደርገው!

ዛሬ ኢትዮጵያ ያልችበት ሁኔታ ልክ ሃይለ ስላሴ 1928 በጄኔቫ የነበሩበት ጋር አንድ ነው ። ዛሬ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በ እውነት እንደ ምንለው ጀ ግ ና ፍጡር መሆን አለመሆናችንን የምናሳየው ይህን ያለም ርብርቦሽ በመሰባበር !!

የኢትዮጵያ ክረምት እየደረሰ ስለሆነ ውጥረቱ እየተነፋ ነው ። ያበሻ ዘር አንድና አንድ ብቻ የምንሆንበት ሰዓት ላይ ነን

አንድ ባስቸኳይ ማድረግ ያለብን ነገር ፣

የዲያስፖራ ኢትዮ ተወላጅ አገር ውስጥ ያሉንን ወጣት ዘመዶች አገር መከላከያ እንዲገቡ ማሳሰብ፣ ማነቃቃት፣ በገንዘብ መርዳት ግድ ይለናል ። ስራ የሌላቸው ወጣቶችን ዝም ብሎ ገነዘብ ከመላክ ጦር እንዲገቡ መርዳት ግዜው አሁን ነው።

ልክ እንደ ጣሊያን ዘመን ኢትዮጵያ ብቻዋን ቆማለች ! ይህን ከበባ ሰብረን ስንወጣ ነው ኢትዮጵያዊነታችን ሚመሰከረው !!


Re: ይህ አመት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃያልነት የሚታይበት ይሆናል! ለምን?

Posted: 06 Mar 2021, 16:00
by Horus