Page 1 of 1

"የገዛ እናቴ ሳይቀር ስቃይ ውስጥ ነች ፤ ልጆችዋ የት እንዳሉ አታውቅም። እኔም ወንድሞቼና እህቶቼ የት እንዳሉ አላውቅም።" የኣቢይና የጦርነቱ ደጋፊ ወልቀታይ መለስ ብስራት

Posted: 26 Feb 2021, 22:44
by sarcasm
"የገዛ እናቴ ሳይቀር ስቃይ ውስጥ ነች ፤ ልጆችዋ የት እንዳሉ አታውቅም። እኔም ወንድሞቼና እህቶቼ የት እንዳሉ አላውቅም።"

ከስምንት አመት በላይ የምናውቃቸው የሰብኣዊ ጥስት ድምፅ የሚያሰሙና በኢትዮጵያ አንድነት ሲያቀነቅኑ የምናውቃቸው ሳይቀር የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ አልመስል እስኪለኝ ድረስ እስየው የኤርትራ ሰራዊት እንኳንም ገባ፣ የእጃቸውን ነው ያገኙት፣ ውሸት ነው የሞተ የለም አይነት ጥላቻ እያራመዱ እየታዘብን ነው።
የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ሳይቀር ከትግራይ ህዝብ ይልቅ ለኤርትራ ሽምጣቸው ገትረው እየተከራከሩ ነው።

ያሳዝናል እንደ ሀገር ተዋርደናል።

በፌዴራል መንግስት የተዋቀረው እዛው በአካል እየሰሩ እያዩ ያሉ የትግራይ ግዝያዊ አመራሮች ሳይቀር በግልፅ ትግራይ ወድማለች። ንፁሃን ተገለዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ንብረት በባእድ ሰራዊት ተወሯል እስካሁን ከ4200 በላይ ተሽከርካሪዎች 25% የትግራይ ከተሞች ተዘርፈዋል ይህንን የፈፀነው የኤርትራ ሰራዊት ነው ብለው በመንግስት ሚድያ ሳይቀር እየመሰከሩ፤ አይ ውሸት ነው እኛ ነን ስለ ትግራይ የምናውቀው ብለህ በህዝብ እንባ ላይ መሳለቅ እንደ ሀገር በጣም በጥላቻ ሰክረናል ተዋርደናልም።

የገዛ እናቴ ሳይቀር ስቃይ ውስጥ ነች ልጆችዋ የት እንዳሉ አታውቅም እኔም ወንድሞቼ እህቶቼ የት እንዳሉ አላውቅም የኢትዮጵያ ህዝብ እባካችሁ ዜጎች ነን እና ድምፃችሁን አሰሙ ስንል ዝም በል ጁንታ የእባብ ዘር ይባልልኛል!!!

እባካችሁ ከእኛ ጋር አታልቅሱ ድምፃችሁን አታሰሙልን ግን ጭሆታችን ሀዘናችን በቁስላችን ላይ አትቀልዱ።

#አክሱም ላይ የተፈፀመው ግፍ አብዝሃኛው የትግራይ ከመቐለ ውጭ ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል። ንብረታቸው ወድሟል ተዘርፏል። ሴቶች ተደፍረዋል። ህዝብ ቀየውን ለቆ ተፈናቅሏል።

ይህ በትግራይ ህዝብ ላይ የምናሳየው መረን የለቀቀ ጥላቻ የምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዳናጣት ከመጠን በላይ እሰጋለሁ።

መንግስትና የመንግስት ሚድያዎች ፖለቲካ ስለሆነ ዴሞክራሲ ስላልገነባን ነፃና ፍትሃዊ ሚድያ ስላላገነባን ይዋሹ ያስመስሉ የዜግነት መብት ጠበቃ ነን የምትሉ ግን ከስህተት ላይ ስህተት እየደጋገማችሁ በሄደ ቁጥር ኢትዮጵያን እያፈረሳችሗት እንደሆነ ሁኖ ይሰማኛል።


My questions for Meles are:

ቃልስኻ ቤተሰብካ ዘጽንት እንተ ኾይኑ አንታይ ዋጋ ኣለዎ?

ንወድኻ ፤ "ዓወት ቃልሰይ ፤ ቤተሰብና ኣባዲሙ።" ዲኻ ኽትብሎ?



Please wait, video is loading...

Re: "የገዛ እናቴ ሳይቀር ስቃይ ውስጥ ነች ፤ ልጆችዋ የት እንዳሉ አታውቅም። እኔም ወንድሞቼና እህቶቼ የት እንዳሉ አላውቅም።" የኣቢይና የጦርነቱ ደጋፊ ወልቀታይ መለስ ብስራት

Posted: 01 Mar 2021, 22:51
by sarcasm
Please wait, video is loading...