ፈጽመው ሊግባቡ የማይችሉ ኀይሎችን ምን አግባባቸው?
Posted: 25 Feb 2021, 19:38
ፈጽመው ሊግባቡ የማይችሉ ኀይሎችን ምን አግባባቸው?
Woldegiorgis G. Teklay
ርእዮተ አለም፣ እሳቤና ፓሊሲ ፈጽሞ የማያግባባቸው ህ.ግ.ደ.ፍ (ሻዕቢያን)፣ ፒፒ፣ አብን፣ ኢዜማ፣ ስለምን ትግራይን ለማጥፋት፣ ለማደህየትና ለማንበርከክ በተጀመረው ወረራ ፍጹም ተመሳሳይ አቋምና አካሄድ ሊኖራቸው ቻለ? ምን ስለሚያገኙ? የሚያገኙት ተጨባጭ ፓለቲካዊ ትርፍስ ምንድነው?
በርግጥ ህ.ግ.ደ.ፍ (ሻዕቢያ) ለኢዜማ አባት ነው። ኢዜማ በኤርትራ ለአመታት የተቀለበው 'ገነት ሆቴል' ለመድረስ እንዳልሆነ ከአውቆ ደንቋሪው በቀር ሁሉም ያውቃል።
በሌላ በኩል ህ.ግ.ደ.ፍ (ሻዕቢያ) የፒፒ የእንጀራ አባት ነው። የፒፒ ዋነኛ 'soft' ቢሮ አስመራ፣ 'hard' ቢሮ በአዲስ አበባ የኤርትራ ኤምባሲ፣ ቀፎው ደግሞ በአራት ኪሎ እንደሚገኝ ፓለቲካው የገባቸው ንቁዎች ያስተውላሉ::
አብን የአማራ ፒፒ የ'ክብር ዘበኛ' ተጠባባቂ ተከፋይ ክንፍ ስለመሆኑ ተግባራቸው ዐቢይ ምስክር ነው። ለዚህም እኮ ነው በነሱና በፒፒ መሐከል መሰረታዊ ልዮነት በወረራው፣ በሱዳን የመሬት ጉዳይ ላይ አንዳችም የማይተነፍሱት- ዝም ያሉት በነሱ ቤት ፓለቲካዊ ስትራቴጂ መሆኑ ነው።
ከመቶሺዎችየአማራ መፈናቀል ይልቅ የአንድ ትግራዋይ የስነ-ልቦና ጥንካሬ እንቅልፍ ይነሳቸዋል:: ትግራይ ቀና ከምትል ሚሊዮን አማሮች በኑሮ ውድነት ቢሰቃይ ጉዳያቸው አይደለም፣ ከአማራ ሴት የዮኒቨርስቲ ተማሪዎች ደብዛ መጥፋት ይልቅ የትግራዋይ ሴቶች የመብት ጥያቄ ያንገበግባቸዋል።
ትምክህተኛው አማራ ከነውጡ ምን አገኘው ከማለት ይልቅ ትግራዋይ ምን አጣ የሚለው እጅጉን እንቅልፍ ይነሳዋል:። ለምን? ስሪቱና የስነ ልቦናው ውቅር - - - የተመሰረተ ስለሆነ
ታዲያ ምን አግባባቸው? ያግባባቸው 'የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው' የሚለው እሳቤ ብቻ ነው። በፍጹም በጋራ መምራት አይደለም - በጋራ ወክ ማድረግ የማይችሉ ኀይሎች ናቸው ነገር ግን ህገ መንግስቱ ለሁሉም እንቅፋታቸው ነው፣ ለሁሉም ህዝባዊነት ሬት ሬት ይላቸዋል፣ ዲሞክራሲ ለሁሉም ያቅራቸዋል፣ ፍትሃዊና ነጻ ምርጫ ያስደነብራቸዋል፣ አርቆ ማሰብ ያቅታቸዋል፣ ባርነት ከነጻነት የተምታታባቸው ድንብር መሆናቸው ያመሳስላቸዋል።
ምስለኔነትና የተላላኪነት ሰንሰለት የህልውናቸው መሰረት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ያቀራርባቸዋል::
https://www.facebook.com/WoldeHagereseb ... 3621252228
አንዳንዶች አሉ - መሪ አልባ ከነሱ ጋር በፍርሃት የተዳበሉ፣ የሃይል ሚዛን ቢገለጥ ለሰከንድ አብረዋቸው የማይሆኑ፣ አሉ ደሞ አንዳንዶች ታክቲክና ስትራቴጂ የተምታታባቸው - - - ብዙዎች ዝም በዝምታ የተባበሯቸው ቢመስሉም የብርሃን ፍንጣቄ ቢያዩ የሚገለበጡ አማራጭ አልባ ኀይሎች በርካታ ናቸው።
አስመራ - ከአዲስ አበባ የበለጠ የፓለቲካ ስህበት ማዕከል ለጊዜው ሆናለች። ነገ ደግሞ - - -