Page 1 of 1

The last 10 year development plan vs the new 10 year plan. What went wrong and what was good.

Posted: 25 Feb 2021, 03:58
by temari

Re: The last 10 year development plan vs the new 10 year plan. What went wrong and what was good.

Posted: 25 Feb 2021, 08:45
by Ethoash
ይህ በጣም ቀላል ነው።

ጥያቄው ለምን የአስር አመት ፕላናችን ሳንፈፀመው ሌላ የአስር አመት ፕላን አስፈለገን የሚል ነው። እንዲህ አይነቱን ጥይቄ ለመመለስ ከፋፍለን ማየት አለብን።

ፓላኑን የሚያውጡትን ስውች መመልከት ነው። ሁለተኛ ደግሞ ገንዘብ የሚፈስበትን ቦይ መመልከት ነው። ለምሳሌ አንድ ባለስልጣን የዛሬ አስር አመት እቅዳችን መድሀኒቶችን ከውጭ ማስቀረት ነው። እዚሁ አገራችን ውስጥ ማምረት ነው እንለዋለን። ይህ የጤና ሚኒስተር አረ ባክሽ ያህ ሁሉ ጉቦ ሊቀርቢኝ ነው ብሎ ፕላኑን አይተገብረውም።

ለምሳለ የጤና ሚኒስተር የ፩፳ ሚሊዬኖችን መድሀኒት ለመግዛት ሕንድ ይሄዳል። ለሕንዱ ባለ ህብታም የመቶ ሚሊዬን ሕዝቦች መድሀኒት ልገዛህ ነው ግቦ እፈልጋለሁ ይላል። ታድያ ይህ ሕንድ ፣ ቻይናዊ ይህ እድል እንዲያመልጠው አይፈልግም። ቢፈልግም ካለ ጤና ሚኒስተር ማንም መድሀኒቶችን የሚገዛ ድርጅት ኢትዬዽያ የለም በቁጢ ቁጢ ካልሆነ በስተቀር። የትምህርት ሚኒስተሩ ይህንን የሚያረገው ነገሩ ጠፍቶት ሳይሆን ሕንዶች ወይም ቻይኖች ሚስጡሩን ይጠብቁለታል። ስለዚህ ይህንን ሲስተም መቀየር አይፈልግም

የግብርና ሚኒስተር ደግሞ ትራክተር ከውጭ ማስገባት ይፈልጋል ። የገቡት ገደል ቢገቡ ደንታ የለው እሱ የሚፈልገው በአመት ሁሌ አዳዲስ ትራክተሮችን ማስገባት ነው የሚፈልገው ለምን እንደገና ጉቦ የትራክተር ካፓኒው ወጭ ኮሚሽኑን ያስቀምጥለታል።

ትናንትና የትራንስፖርት ሚኒስተር ፲ ሺህ አምስት መቶ ታኪሲዎችን ከውጭ ለማስገባት ማንንም ሳያማከር ተዋወሎ ጨርሶ እልል ተባለለት ። እንደው ሃይሌን ይህንን ታክሲዎች እንዲያመርት ተጠይቆ ነበር ወይ። አረ ትንሽ እንኮዋን ጥረት ተደርጎ ነበር ወይ አይደረግም ዝም ብሎ ማስገባት ነው። ሚኒስተሩ ደንታ የለውም እሱ ጉቦዎን ካገኘ ። እስቲ ተመልከቱት ፮ ቢሊዬን ዶላር ይሁን ብር ቀለጥን ምንም እንጥፍጣፊው አገር ውስጥ ሳይገባ።

ታድያ ይህንን ችግር ካልፈታን ምድረ ጉቦኛ ይዘን እንዴት ነው የምናቀደው እቅዱ ከባለስልጣኑ መስራቤት እቅድ የተለየ ከሆን ጉቦ የሚያገኙበትን መንገድ ከዛጋ እንዴት ብሎ ነው ሚኒስተሩ የሚተባበረው።

አንዳንዴም ሚኒስቶራቸን ጉቦ ውስደው ቢገላግሉን ጥሩ ነበር ግን አገር የሚጎዳ ነገርም ያረጋሉ። ለምሳሌ ማዳበሪያ። የኢትዬዽያ ዋና ማዳበሪ ሻጭ ኩፓኒያ ለአብይ መቶ ሺህ ዶላር ሽልማት ስጥቶታል ። ከኢኮኖሚክሱዋ ሴትዬም መቶ ሺህ ዶላር ስጥቶዋል ታድያ ይህ ጉቦ ካልሆነ ምኑ ነው ጉቦ ። ስለኬሚካል ማዳበሪ የሚያወራ አንድም ባለስልጣን አታገኝም መሬታችንና ለም አፈራችንን እያቃጠለ ካንስር በካንስር ያረገን ይሄው ኬሚካል ማዳበሪያና ወተት በብዛት ት ስጣለች እየተባል ሆርሞን የሚወጉት ላሞቻችን ናቸው። ግን ከአመት ወድ አመት ፕላን እናውጣለን ከስር መስረቱ ችግሩን ነቅለን እንደማውጣት።

እንደኔ ከሆን ሚኒስተሮቻችን ከሚያዙት ገንዘብ አንድ % ማግኘት አለባቸው። ለምሳሌ የግብርና ሚኒስተር አንድ ቢሊዬን ባጀት ካለውና ከዚያ ውስጥ % ለሀገር ካዳነ እዚህ አገራችን ውስጥ በማምረት ያ ካምፓሊ ላይ ፩% ሼር ማግኘት ከቻለ በቢሊዬን ዶላር ካምፓኒ ከከፈተ ደግሞ ከቢሊዬን ዶላር % ካገኘ ። ልክ እንደራሱ ገንዘብ አይቶት መስራት ይጀምራል አለበለዚያ ሚኒስትሮቻችንን በሶስት ሺህ ብር ደሞዝ የቢሊየንን ዶላር ኢኮኖሚ አንቀሳቅስ ብንለው አይስማህም።

ዩኒቨርስታችንም እንዲሁ ነው። በያመቱ ቢሊዬን ብር ውጭ እናረግባቸዋለን ለአንድ ዩኒቨርሲቲ ግን እራስ ህን ቻል ፣ እራሰህን ከቻልክ ደግሞ % ያንተ ነው ከተባለ ይተኛው ዲን ነው ገንዘብ የሚያባክን በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ዩኒቨርስቲያችንን እራሳቸውን ችለው ይንቀሳቍሱ ነበር። አሁን ግን የወተት ላም ከማርባት ወተት መግዛት ነው የሚቀላቸው ። አታክልት ከመትከል አታክልት መግዛት ነው የሚቀላቸው ቢሊዬኑን ቶሎ አጥፍተው ሌላ ቢሊዬን ለመቀበል እንደው ቀልድ ነው።

ገንዘብ ለነዚህ አስተዳዳሪዎች በሚሊዬን ሳይከፈል ግን የፕላን መቀያየር ቢኖር ልፋቱ ከንቱ ነው ባይ ነኝ።