"ኢትዮጵያ ለትግራይ ህዝብ ሉዓላዊነት እየነፈገች ነው። የትግራይ ሰዎች ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ?" የኣቢይ ደጋፊ Activist ወልቀታይ መለስ ብስራት
Posted: 31 Jan 2021, 22:27
ፍቅራችሁ ያዝልቀው!
የአማራ አክቲቪስትና ፖለቲከኞች ሰሞኑን በኢሳያስ ፍቅር ተንሰፍስፈው ሊሞቱ ነው። ፍቅራችሁ ያዝልቅላችሁ ብያለሁ።
እንደዚህ ዓይነት የማስመስል ሽር ጉድ ሲታዘቡ የትግርኛ ተናጋሪ ህዝቦች "ኣዲኣ ገዲፋስ ሓትንኣ ትናፍቅ" እናትዋት ትታ አክስትዋን የምትናፍቅ! ብለው በአሽሙር ይነግሩሃል።
አሁን እያየነው ያለ እናታቸውን እየገፉና እየበደሉ አክስታቸው ላይ የማስመስል ፍቅር ዘለቂታው የት እንደሚያደርስ አብረን የምናየው ነው።
ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያገናቸው ድልድይ የትግርኛ ተናጋሪ የትግራይ ህዝብ ነው። ይህ መራር እውነት ነው።
የትግራይ ና የኤርትራ ህዝብ ትግርኛ መናገሩ ብቻ ሳይሆን በጋብቻና በደም የተሳሰረ ህዝብ ነው።
ይህ ህዝብ ትናንት በእኛ እድሜ ሳይቀር ደርግን ለመጣል ያላቸውን ተካፍለው እየበሉና እኔ ልሙት አንተ ቆይ እየተባባሉ ለ17 አመታት በተራራና በጉድጓድ አብረው እስከ ድል የዘለቁ ህዝቦች ናቸው።
ይህንን የአንድነት ቃልኪዳናቸው ከድል በኋላ እርስ በርስ ሽኩቻ ውስጥ ገብተው ወደ አልተፈለገ ደም መፋሰስ ቢገቡም። ለ20 አመታት አጥር አጥረው ህዝቡን ለማራራቅ ቢጥሩም የፈለጉትን የህል ግን አልተሳካላቸውም።
በጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድ መልካም ፍቃድ እርቅ ሲፈፀም የሁለቱ ህዝቦች እንባ እየተናነቃቸው ናፍቆታቸውንና አንድነታቸውን አስመስክረዋል። ይህም እመነኝ ከህወሓት ሞት በኋላ በትግራይና በኤርትራ የነበረው የአንድነት ማእተብ አጠናክረን እንሳቅጥለዋለን።
የትግራይ ህዝብን ጠልተህ ኢሳያስ ላይ በፍቅር መውደቅ ለዛውም የማስመሰል ፍቅር ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ወደየት እንደሚያመራን ግልጥልጥ እያለ ነው።
የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም ያማለት ህዝቡ አሁን እየደረሰበት ያለን መረን የለቀቀ ጥላቻ ብሎም በግልፅ እንደ ጠላትነት መፈረጅ ገፍትረን ወደ አልተፈለገ ሊያመራው እንደሚችል ነብይ መሆን አያስፈልግም።
ፍቅራችሁ ያዝልቅላችሁ እናት ጠልተን አክስት ላይ መጠምጠሙ ነገን ሳስብ ግን ኢትዮጵያ ትልቅ አደጋ ውስጥ ነች የሚል ስጋት ይሰማኛል።
የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደርና ለውጥ ፈላጊ የትግራይ ልጆች ከፍተኛ ፈተና ውስጥ መሆናችን የማይካድ እውነት ነው።
በጣም ማመን የሚከብደኝ የኤርትራ ወታደር ትግራይ ገብቶ መዋጋቱ ትክክለኛ እንደሆነና ምስጋናና ክብር እንደሚገባው እየገለፁ ሳይ የትግራይ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ ወደሚል ጥያቄ ይደጋገምብኛል።
ሉዓላዊነት ለትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያ እየነፈገች መሆኑም ነው የሚያመላክተው!!!
ትግራይ INTERNETሲከፈት የተፈፀሙ አስፈሪ ነገሮች የት እንደሚያመራን አብረን የምናየው ይሆናል።

Please wait, video is loading...