አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት ገለጸ
Posted: 29 Jan 2021, 16:44
አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት ገለጸ
January 29, 2021
እነ ስብሀት ነጋ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በፌፌራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው ጉዳያቸው የታየው ፡፡ የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የቄስ ልብስ ለብሰው መታወቂያቸውን ቀይረው ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ፖሊስ ለችሎት ገለጸ።
–
በሀገሪቱ ሁከት በመቀስቀስ ሰዎች እንዲገደሉ እና እንዲፈናቀሉ ከማድረግ ጀምሮ የነዳጅ ዲፖ ዘረፋ መፈጸማቸውን የሚያመላክት ማስረጃ መሰብሰቡን መርማሪ ፖሊስ ለችሎት ገልጿል፡፡
–
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መርመሪ ቡድን የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ከንግድ ባንክ በርካታ ገንዘቦችን እና ወርቆችን አውጥተው ወደ ደደቢት ማይክሮ ፋይናነስ ተቋም በማስገባት ከተጠርጣሪ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ በየበረሃው ለነበሩ አመራሮች ሲያከፋፈሉ እንደነበር ማስረጃ መሰብሰቡን ጠቅሷል።
–
መርማሪ ቡድኑ ይህን የገለጸው ዛሬ በእነስብሀት ነጋ ፤ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ስም በተደራጀ ሶስት መዝገብ የተካተቱ 21 ተጠርጣሪዎችን ፍረድቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።በእነ ስብሀት ነጋ፤ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ስም የተዘጋጁ ሶስት መዝገቦች የተካተቱ አጠቃላይ 21 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ በፍርድ ቤት ታይቷል።የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በቀዳሚነት በስብሀት ነጋ መዝገብ የቀረቡ አጠቃላይ 9 ተጠርጣሪዎችን በቀዳሚነት ተመልክቷል። ....
https://mereja.com/amharic/v2/448141
-------------