Page 1 of 1

አንድ ስንኝ ለትግሬ

Posted: 27 Jan 2021, 03:33
by Horus
ወያኔ ፎከረ ትግሬ ተሸበረ
ፍልስፍና ሞተ ሃሳብ ተቀበረ
ሳይንስም ተሻረ እብደት አመረረ
እምነት ተቀየረ አርት ተፎገረ
ፍርሃት ዋሻ ገባ ቁጣ ሰማይ ወጣ
በጥጋብ የመጣ የእብሪተኛ ጣጣ
የህይወት አናርኪ ከስሩ ቅጥ ያጣ።

ሆረስ አይነ ኩሉ
January 26, 2021

Re: አንድ ስንኝ ለትግሬ

Posted: 27 Jan 2021, 04:46
by Meleket
ትግሬ የቅርስ አገር፡ የታሪክ መዲና፣
የገዳማት ሃገር፡ እስከ ትላንትና።

ወያኔ ምትባል አንዲት መዥገር ወልዶ፣
ኤርትራ ምድር ላይ በዕብሪት ተጥዶ፣
ይኖር ነበር አሉ ጦቢያ ላይ ቀልዶ።

አመሻሹ ላይ ግን በቀዶ ጥገና፣
መዥገሩን ለይቶ ሚያደባይ መጣና፣
እፎይ ይል ጀምሯል ሸፍኖ ገበና፣
ትግሬ ነጣ ወጥቶ ታግዞ በጀግና።
:mrgreen: