Page 1 of 1

አንድ ስንኝ ለተራራው

Posted: 26 Jan 2021, 03:07
by Horus
ለዘላለም ቆሞ ሺ አመት የኖረ
ደጀን እንደ ጋሻ፣ ከራስ የገነረ
ዝናብ የፈጠረ ታቦት የደበቀ
አባይን የሞላ አገር የጠበቀ
ሰማይ የጠቀሰ ላራዊቱ ደብር
ለሸፈተ ምሽግ ለመነነው አገር
ማን ይሙት ይንቀጥቀጥ
ማን ይሙት ይናወጥ
በከሸፈ ባንዳ በቀለለ ቀቢጥ
በዋሻ ነዋሪ በጃርት አይጠ ሞገጥ።


ሆረስ አይነ ኩል
ጃኗሪ 25 2021

Re: አንድ ስንኝ ለተራራው

Posted: 26 Jan 2021, 04:24
by TGAA
:( wonderful 👏

Re: አንድ ስንኝ ለተራራው

Posted: 26 Jan 2021, 05:00
by Meleket
ግሩም ታሪካዊ ስንኝ ነው ወንድማችን Horus። እስቲ እኛም በስንኞች እንዝናና ለተራራው . . . ይሄም ያንስበታልና!

የተራሮች ራስ፣
የተራሮች ንጉሥ፣
እንደም ነህ ደጀን፣
ያምርብሃልና ኮራ በል ተጀነን!

እኒያ የቋመጡት አንተኑ ሊሰርቁ፣
ሳር ሳሩን ሲግጡ ገደሉን ሲንቁ፣. . .

ጣቱ ላይ ሰክቶ የቀይባሕር ዕንቁ፣
አሻግሬ ቢመጣ ታጥቆ ከነ ስንቁ፣
. . .

ሰም ሰሙን ሲፈቱ ጠፍቶባቸው ወርቁ፣
እየተለቀሙ ወኅኒ ሲወሸቁ፣
አየሃቸው አይደል እንዴት እንደሚያስቁ?
:mrgreen:


Horus wrote:
26 Jan 2021, 03:07
ለዘላለም ቆሞ ሺ አመት የኖረ
ደጀን እንደ ጋሻ፣ ከራስ የገነረ
ዝናብ የፈጠረ ታቦት የደበቀ
አባይን የሞላ አገር የጠበቀ
ሰማይ የጠቀሰ ላራዊቱ ደብር
ለሸፈተ ምሽግ ለመነነው አገር
ማን ይሙት ይንቀጥቀጥ
ማን ይሙት ይናወጥ
በከሸፈ ባንዳ በቀለለ ቀቢጥ
በዋሻ ነዋሪ በጃርት አይጠ ሞገጥ።


ሆረስ አይነ ኩል
ጃኗሪ 25 2021

Re: አንድ ስንኝ ለተራራው

Posted: 26 Jan 2021, 05:14
by Horus
ቲጂኤኤ
አመሰናለሁ! ውስጠ ወይራውን ሆነ ብዬ ይዥዬው ነው እንጂ ተራራዋ ኢትዮጵያ ነች ። ዉሸት ነው እኛን ሚያንቀጠቅጥ አንድም ሃይል የለም !!

መለከት፣
ወብ ነው ስንኝህ ! ደጀንን አውቄ ነው የጠቀኩት። ዎያኔ የተሸነፈው በጎንደሮች ነው፤ ጀግኖች ናቸው ! ሱዳንም ብታርፍ ይሻላታል !! ኤቦ ኢትዮጵያ !!