ኦነግ "ህወሃት ከፖለቲካው መድረክ በመሰረዙ ደስተኛ ነኝ"
Posted: 25 Jan 2021, 07:31
ኦነግ "ህወሃት ከፖለቲካው መድረክ በመሰረዙ ደስተኛ ነኝ"
ህወሓት ከፖለቲካው መድረክ እንዲሰረዝ መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው – ኦነግ
‹‹ህወሓት ከፖለቲካው መድረክ እንዲሰረዝ መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው›› አቶ ቀጄላ መርዳሳ የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ህወሓት ከፖለቲካው መድረክ እንዲሰረዝ መደረጉ ከሕግም ሆነ ከፖለቲካ አንጻር ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አስታወቀ፡፡የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ህወሓት ቀደም ሲል ጀምሮ ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ጦርነትና ግጭቶችን መሠረት ያደረገ ነው፡፡
–
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ 1162/2011 ላይ በግልጽ እንደሰፈረው አንድ የፖለቲካ ድርጅት አላማውን በትጥቅ ትግል ለማሳካት የሚሞክር ከሆነ በፖለቲካ ፓርቲነት ሊመዘገብ አይችልም ከተመዘገበም እንደሚሰረዝ በግልጽ ማስቀመጡን ጠቁመው፣ ከዚህ አንጻር የቦርዱ ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
–
ህወሓት ማነው የሚለውን ስንመለከት ሕዝብና መንግሥት ላይ ጦርነት ካወጀ ከሁለት ዓመት በላይ የሞላው እና በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊትን ከኋላው በመውጋት አሳፋሪ ድርጊት የፈጸመ ድርጅት ነው ብለዋል።
–
የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለጹት፣ የህወሓት ቡድን በሕዝብ አመጽ መቀሌ ከገባ ጀምሮ ሰላማዊ አማራጮችን ከመጠቀም ይልቅ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ትርክቶችን በማሰራጨትና ሁከቶችን በመቀስቀስ ሀገሪቱን ሲያተራምስ ቆይቷል፡፡
–
https://www.press.et/Ama/?p=40065