A post by Mer Addis on FaceBook:
ማታ ዞር ዞር ብዬ መተኛት ሲያቅተኝ 360 መስማት ጀመርኩኝም።
ኤርሚያስና ብሩክ በጀመሩት ፕሮግራም ላይ ሀብታሙ ቆይቶ ተቀላቅሎ መጀመሪያ ስለ ደመቀ የቤኒሻንጉል አስተያየት ቀጥሎ ስለትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ውይይቱ ቀጠለ ።
ዘ ኢኮኖሚስት የኢትዬጲያ መንግስት ርሀብን እደጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው ብሎ ያወጣውን ዘገባ መነሻ አድርጎ ኤርሚያስ እኔ በግሌ የኢትዮጲያ መንግስት እደዚህ ብዬ አላምንም የኤርትራ መንግስት ግን ያደርጋል ብዬ አምናለው

እህእ ብዬ ተገርሜ መጨረሻቸውን ልስማ ብዬ ቁጭ አልኩኝ ። ከዛ ቀጠል አድርጎ የኢትዬጲያ መንግስት ኤርትራ መግባቱን ክድዋል ግን አቅም አንሶት አስገብተቶት ሊሆን አሁን ካንሰሩ ህወኃት ስለተቆረጠ መውጣት አለበት ይሄ ሁላ ግፍ የመጣው ጦርነቱ ካለቀ ነው ።
ይሄ ማለት መግባቱን ይደግፋሉ ። ሁለተኛ ነገር ሻቢያ ሰው መረሸን የጀመረው መቼ እደሆነ ይክዳሉ እኛ ግን እናቃለን ።
የባሰ የሚገርመው ቆየት ብሎ ተጋሩን እያጣናቸው ነው ተመልከቱ ለዚህ ሁላ በደል አማራ ነው ሊደርስለት የሚገባው ።ጎረቤት መዳኒት ነው ብአዴን አይሰማም እኮ በስልክ እየደወልን ስለሴራው እየነገርናቸው ነው። ኦሮሙማ ምን እየሰራ እደሆነ እዮ አባ ገዳ ልኮ እኛ አበላቹ እነሱ ገደላቹ እያለ ድራማ እየሰራ ፀብ እየተከለ ነው።
ኦቢኤንና ትግራየ ቲቪን ወንድማማች ብሎ እያሰባባበ ነው። በሁለቱ ህዝቦች በትግራይና በአማራ መካከል ፀብ እየተከለ ው። ለበአዴን እየነገርን ነው ደረሱላቸው. ሴራውን አክሽፉ ብለን። እነቴድሮስ ፀጋዬን እያጣን ነው ትግራይን ዕያጣን ነው እኝኝኝ እያለ በሀብታሙ እየታጀበ ሴራ አለ ብለው ሲያላዝኑ አመሹ
እኔ የገረመኝ ሻቢያ እራብን እደመሳሪያ ከተጠቀመ መጠየቅ ያለበት በቤቱ ጎትቶ ያስገባው መንግስት ነው ወይስ ሻቢያ ። ምን ጠብቃቹ ነበረ ጎትታቹ ያስገባቹት ከመረቁ አጠጡኝ ከስጋው ፆመኛ ነኝ የለም። ሲቀጥል ሻቢያ ብቻ አደለም ፋኖም ነው። ነገር ግን ለ 360 ፋኖ ቅዱስ ቄሮ ደሞ እርኩስ ነው። ባለፈው ሶስት ወር ገደማ ተሳስተው ስሙ ለባርኮት እነጂ ለኩናኔ አንስተው አያቅም።የፈፀሙት ግፍ እየፈፀሙት ያለውን በማስረጃ አስደግፈን እያስቀመጥን ነው።
ሁለተኛ በአዴን ለትግራይ ህዝብ ድረስላቸው ኢዝ ፈኒ እስከምድር ጥግ ጠላታችን በአዴን ከነኮልኮሌዎቹ ናቸው። ማን ጦርነቱን እደተከለ ማን ጦርነቱ ጭብጨባ እደሚሰጥ ማን ለደረሰው በደል ክህደት በሚድያ በአለማቀፍ መድረኮች እደሚፈፅም እናቃለን። ይሄ ነገር ዘላለም አይፈጠርም። ከንግዲህ ይሄ የሰሜን ህዝቦች ዘበዘባ ጉርብትና የሚባል ነገር የለም መዝገቡ ተዘግትዋል።ሑላችንም በየፀበላችን። እራሳቸው 360 ላለፈው ሶስት አመት የጦርነቱ ደጋሽ ነበሩ። ወያኔ ሰራዊት ሰበሰበ ወያኔ ሊገነጠል ነው። በፌደራል መንግሱቱ መመታት አለበት ሲሉ ነበረ። እነሱ ረሰተውታል እኛ አንረሳውም አልረሳነውም።
ሶስተኛ አሮሙማ ሴራ እየፈጠረ አማራና ተጋሩን እያጣላ ነው የሚል ቀልድ እደመቀለድ የሚያስቅ ነገር የለም። ኦሮሙማ የሚያገባው ነገር የለም። ለክሬ መሰክራለው
በዚህ ጦርነት ወገንተኝነትም ያሳዩን ከህወሓት ጋራ ሳይሆን ከህዝብ ጋራ ቆመው ሰው እንዳለን ያሳዩን ድምፅ የሆኑን የኦሮሞ አክቲቪስት ፖለቲከኞች ናቸው ብትፈልጉ ሽርሙጥና በሉት።እደውም የሚገባቸውን ምስጋና እና ክብር አልሰጠንም። አሁን ድረስ ማን አለማቀፍ ተቋማትን ለመጫን የደረሰውን በደለ በግር በፈረስ ለመሸፈን እደሚታትር እናቃለን። ያለፈው ሶስት ወር ያላቹትን ስሙ
አክሱምን በደል እንኳን መንግስት ያጣረው ይሄን ያህል ሰው አይሞትም ቀልድ ስትቀለልዱ ነበረ።
እናም ሂዱና ሾርት ሚሞሪ ፈልጉ
ዘ ዳሜጅ ኢዝ ደን መዝገቡ ተዘግቷል
https://www.facebook.com/meron.addis.18 ... 5327574275