Page 1 of 1

በመተከል ለሁለት ዓመታት ያለፍርድ ከቆዩ ተጠርጣሪዎች መካከል 614ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ -ፋና

Posted: 23 Jan 2021, 15:01
by sarcasm
በመተከል ለሁለት ዓመታት ያለፍርድ ከቆዩ ተጠርጣሪዎች መካከል 614ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ለሁለት ዓመታት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከቆዩ ተጠርጣሪዎች መካከል 614ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ ከግብረ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ፍርድ ቤት ቀርበው በተደረገው የማጣራት ሂደት 614 ተጠርጣሪዎች ዛሬ በዋስ እንዲለቀቁ ተደርጓል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት ተጠርጣሪዎች ከዚህ በኋላ በወንጀል የሚፈለጉ ሳይሆን የልማት አርበኞች ሆነው እንዲገኙ አሳስበዋል።

የክልሉ መንግስት በመተከል ዞን ይፈጸም የነበረውን ኢሰብዓዊ ድርጊትና ሰፍኖ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት መዋቅራዊ ለውጥ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

በመሆኑም ዛሬ ከማረሚያ ቤት የወጡ ዜጎች በተለይ ደግሞ ወጣቶች ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ለጋራ ደህንነታቸው በቅንጅት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል አባል ብርጋዴር ጀነራል አለማየሁ ወልዴ “ወጣቶች በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው ማረሚያ ቤት መቆየታቸውን የቂም በቀል መወጣጫ ሳይሆን መማሪያ ሊያደርጉት ይገባል” ብለዋል።

https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%88% ... %e1%8b%a9/