"ክቡር ፍ/ቤት እኛን በሰበብ አስባቡ ከሰው እስር ቤት አቆይተው የፍ/ቤቱን ጊዜ አባከኑ የኛንም ጊዜ አባከኑ።"
Posted: 23 Jan 2021, 09:11
ጀዋር መሃመድ ዛሬ ችሎት ላይ ከተናገረው
-----
ክቡር ፍ/ቤቱን አመስግናለሁ። ከተያዝንበት ቀን ጀምሮ ስንል እንደነበረው የተከሰስንባቸው ጉዳዮች እውነት ወንጀል ፈፅመን ሳይሆን ከምርጫ ሊያወጡን ነው ስንል እንደ ነበረ ፍ/ቤቱ ያስታውሳል። በመሣሪያ ዙሪያ የቀረበው ክስ አንደኛ አሁን ችሎቱ እንደወሰነው የሚያስከስስ እንዳልሆነ ያውቅ ነበር ዓቃቤ ህግ ሁለተኛ ከኛ ጋር የተያዘ መሳሪያ ወንጀል የተሰራበት ወይም በወንጀል የተገኘ ህገ ወጥ ሳይሆን መንግስት የሰጠኝ ፌዴራል ፖሊስ የሰጠኝ ሌሎቹ ደግሞ በህግ የተመዘገቡ እንደሆነ ዓቃቤ ህግ ያውቃል እኛም ስንነግራቸው ነበር። ነገር ግን ዓላማቸው እኛን በሰበብ አስባቡ ከሰው እስር ቤት አቆይተው ከምርጫ ማሳለፍ ስለነበረ የፍ/ቤቱን ጊዜ አባከኑ የኛንም ጊዜ አባከኑ።
ክቡር ፍ/ቤት ደጋግሜ የምናገረው አነዚህ ልጆች (ሴኩሪቲዬ) ግማሾቹ ፌዴራል ፖለስ አባል የነበሩ መንግስት የመደበልኝ ሌሎቹ የአጋዚ ኮማንዶ አባል የነበሩ በክብር ተሰናብተው በመንግስት ፀጥታ ዘርፍ ጥንካሬያቸው ታማኝነታቸው ታውቆ የተመደቡልኝ ሀገር ያገለገሉ ልጆች ናቸዉ። እኛስ እሺ እዚህ ያለን ፖለትከኞች ነን እነዚህን ልጆች አስሮ ማቆየት አግባብ አይደለም። ዓቃቤ ሊያስብበት ይገባል።
ክቡር ፍ/ቤት የቀሩ ክሶችም ቢሆን ዓቃቤ ህግ ያውቃል፤ በማስረጃ በኛ ላይ አረጋግጠው ሊያስቀጡን እንደማይችሉ በደንብ ያውቁታል፤ ምንም የሰራን ወንጀል እንደሌለ ያውቃሉ። ትልልቅ አንቀፆችን ጠቅሰው እኛን ከሰው የናንተንም ጊዜ እያባከኑ ያሉት እኛን ከምርጫ ለማስቀረት ነው እንጂ ሌላ ነገር የለም። እኛ እያልን ያለነው የኛ በምርጫው መሳተፍ ለሀገር ደህንነት ለሀገር ሰላም ስለሚፈጥር አሁንም ነገም የዛሬ 3 ወርም ብትቀጥሩት አንድም ተጨባጭ ማስረጃ አያመጡም የሀሰት ማስረጃ ነው የሚያመጡት እሱንም እኛ ተከላክለን ውድቅ እናደርገዋለን ያነ ግን ምርጫ ያልፋል።
እኛን ከምርጫ በማስቀረት ሀገርንና ዲሞክራሲያዊ ሽግግሩን ከማደናቀፍ ይልቅ ዓቃቤ ህግ ነገ የሚያፍሩበትን ጉዳይ ዛሬ ተጠቅመው ሀገርን ህዝብን ከሚጎዱ አሁኑኑ እንዲያስቡበት ነው የማሳስበው ። ክቡር ፍ/ቤቱ እንዲረዳልን የምንፈልገው ምንም ጭብጥ የሌለውን ነገር ይዞ ምንም ወንጀል ያልሰራን ከምርጫ ለማስተጓጎል ብቻ በችኮላ ከዚህም ከዚያም የሰበሰቡዋቸው አንቀጾች እንጂ ምንም የሚያስከስስም የሚያስቀጣም ጉዳይ እንደሌለ ለማሳሰብ ነው። አመስግናለሁ!
-----
~ Oromo political prisoners' defence team