Page 1 of 1

Video News Of: ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ:--የጁንታው ሽንፈት በጣም አሳፋሪ ነው***አዋይ ውርደት***!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 23 Jan 2021, 08:34
by tarik
‹‹ የጁንታው ሽንፈት በጣም አሳፋሪ ነው ›› ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ጁንታው ያጋጠመው ሽንፈት በጣም አሳፋሪ እንደሆነ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።
ጁንታው የዘረፈውን ንብረት ሁሉ ጥሎ ነው የሸሸው ። የዘረፈውን ንብረት በሙሉ አስጥለን ከመኪና አስወርደን ነው ያባረርነው ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፣ ከትላልቅ ብርጌዶች ወደ ትናንሽ ዩኒቶች ፣ከሻንበል ጋንታ ከፍ ሲል ሻለቃ ወርደው እሱም እንደገና ተደምስሶባቸው አሁን ግለሰብ ነው እየፈለግን ያለነው ብለዋል።
የህውሓት የጥፋት ጁንታ ለ27 ዓመታት በሴራ ሲመራ ቆይቶ በሕዝብ ትግል ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ዳግም ለመመለስ በሰሜን ዕዝ ላይ የተነኮሰው ጥቃት የጥፋቱ ጥግ እስከምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ እንደነበር አመልክተዋል።

====================================================================================