Page 1 of 1

መልስ ለኣ/ር ዲና ሙፍቲ "የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ገብቷል። ምን ችግርስ ፈጠረ፧" የኣቢይ ደጋፊ ትግራዋይ ኣማንሚካኤል መስፍን (Geez Media)

Posted: 21 Jan 2021, 18:03
by sarcasm
የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ገብቷል። ምን ችግርስ ፈጠረ?

ለየውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ አንባሳደር ዲና ሙፍቲ ያለኝ አስተየት - ኣማንሚካኤል መስፍን (Geez Media ግዕዝ ሚዲያ)

የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ላይ ገባ አልገባም?



አንባሳደር ዲና የኤርትራ ሰራዊት አልገባም ብለው ትላንት በነበረው ፕረንስ ኮንፈረንስ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ይህን ስሰማ በጣም ተሰማኝ ነገሮች እንዳናባብስ ብዬ ዝም ያልኩትን እውነቱ ለማፍረጥ ተገደድኩኝ።

በአንባሳደር ዲና በጣም ነው ያፈርኩት የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ክልል መግባቱ የሰሜን እዝ አዛዥ ጀነራል በላይ ስዩም በመቐለ እኔ በነበርኩበት መድረክ ያመኑበት ጉዳይ በሚዲያ ያለፈ ነገር አንባሳደር ዲና መካዳቸው ትእዝብት ላይ ነው የጣላቸው። የኤርትራ ሰራዊት ከመቐለ እስከ ራያ ያሉት አከባቢዎች ውጪ በተቀሩት አከባቢዎች ገብቷል።

ሲገባ ለራሱ በግላጭ ነው ዩንፎርም ለብሰው መኪና ይዘው ነው ለዛውም ምንም ህፍረት የላቸውም በታሪክ እንወቀሳለንም አላሉም

አምባሳደር ዲና የትግራይ ህዝብ በአይኑ ያየው ነገር መካድ ምንድነው ጥቅሙ ? እስቲ የዓዲግራት፣ ውቅሮ፣አክሱም ፣ ተንቤን፣ሽረ፣ሑሞራ ፣ሸራሮ ፣ዘላምበሳ ህዝብ ይጠየቅ በሚዲያ ይቅረብ።

የሚሻለው የኤርትራ ሰራዊት መግባቱ ፣ንብረት መዝረፉ ፣ድርጅቶች ማውደሙ አምኖ ይሄ የሆነበት ምክንያት መግለፅ እዛ ሲጠብቅ የነበረ ሰራዊት ስለተመታ ነው ቢሉ ይሻላል እንደ ወዳጅ ሃገርስ እርቅ እንደፈፀሙ ሃገራትስ መከላከያው ይኑር አይኑር መግባት ነበረባቸው ወይ ሌላ ነገር ሁኖ። አሁንም መፍትሄ የሚሆነው የገባው የኤርትራ ሰራዊት በፍጥነት እንዲወጣ ማድረግ፣የተዘረፈው ሰው መካስ የፈረሱ ድርጅቶች ጠግኖ ወደ ነበሩበት መመለስ።

የኤርትራ ሰራዊት መግባቱ በጣም ነው የማዝነው። ኢትዮጵያ ልአላዊነትዋ መደፈሩ ይሰማኛል ይሄ ሰሞ በየትኛውም ዘመን አልሆነም። ኢትዮጵያ ክብርዋ አሳልፋ የሰጠችበት የታሪክ አጋጣሚ የለም።

የኤርትራ ጦር መግባቱ ለኔ ዬለው ትርጉም ኤርትራ ሃገር አይደለሁም እያለች ነው። ኤርትራ እንደ ወዳጅ ሃገር በውስጥ ለውስጥ መሳርያ ምናምን ብታግዝ ማንም ሃገር የሚያደርገው ያለና የነበረ ነው። አሁን የተደረገው ግን የትግራይ ህዝብ ምንም አያመጣም በሚል ንቀት ሰው እያያቸው ነው የገቡት ፣የዘረፉት ንብረት ያወደሙት ይሄ እውነት ፈላጊ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ሊገነዘበው ይገባል።

ጠ/ሚ አብይ በጣም ጎበዝ ሰው ነው ኢትዮጵያ መቀየር የሚችል ሰው ነው ፈተና እንደበዛበት አቃለሁ ነገር ግን የኤርትራ ሰራዊት ድንበር ጥሶ መግባቱ እና እሳቸውም ምንም አለማለታቸው በታሪክ ተወቃሽ ይሆናሉ።

አሁንም የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ በፍጥነት ይውጣ የዘረፈው ንብረት ይመልስ።

እውነት እንነጋገር ከተባለ ዓዲግራት ዩንቨርሲቲ፣ዓዲግራት መድሃኒት ፋብሪካ ፣ሰማያታ እምነበረድ ውቕሮ፣ሸባ ሌዘር፣አልመዳ ወዘተ የኤርትራ ወታደር ያወደመው ነው። ይሄ የትግራይ ህዝብ ያቃል አይኑ እያየ የተደረገ ነገር ነው። ትንሽ እንዃ ሰው እያየን ነው አላሉም።

በመቐለ የጠፋው ጥፋት ሙሉ በሙሉ ጁንታው ነው ተጠያቂ። ዘላምበሳ በከባድ ብረት የመታ ጁንታ ነው። ተንቤን ሆን ብሎ የመታት ጁንታ ነው።
አልመዳ የኤርትራ ሰራዊት በከባድ ብረት ከመታው ቦሃላ ህዝቡ ራሱ ሲዘርፍ ነበር ምንጮች አሉኝ። በዕዳጋ ሓሙስ ነዋሪ ቄስ ሳይቀር ሰርቆ ሲሮጥ ሰው አይቶት የቀረፀው ቪድዮ እጄ ላይ አለ።ስልክ በከፊል እና መብራት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ያደረገ ጁንታው ነው።

በመቐለ ያሉ ፅህፈት ቤት በሙሉ የቀረ ንብረት የለም ይሄ ያወደመው ጁንታው ነው የቀረው የሰረቁት ጁንታው የለቀቃቸው ከ10ሺህ በላይ እስረኞች ናቸው።
ያልተደመሰሱ ነገር ግን ትርጉም የሌለው ሃይል የጁንታ ታጣቂ በየቦታው አለ። ይሄ ለማጥፋት ሙከራ አለ ግን በቂ አይደለም መከላከያው በድሉ ረክቷል አንዳንዴ ሳስበው ትግራይ ወደ ነበረችበት ለመመለስ ፍላጎት ያለም አይመስለኝም እንጂ ቀርቶ ያለው ሃይል እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ትግራይ ሰላምዋ መመለስ ይቻላል። ይሄ በየቦታው የተበተነ ሽፍታ የሚዋጋበት አላማ ስሌለው ሽብር እየፈረጠ ይደበቃል ህዝባችን እርዳታ በሰአቱ እንዳይደርስለት እንቅፋት ሁኗል።

በትግራይ ክልል ያለው ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲጠናከር የማይፈልግ የውስጥም ውጪም ሃይል አለ የህወሓት ደጋፊ ጨምሮ ይሄ ለህዝባችን አደጋ ነው።
ጁንታው አጥፍቷል ፣ክዳል ልአላዊነታችን እንዲደፈር ምክንያት ሁኗል ፣የተዳከመ መከላከያ እንዲኖረን አድርጓል ፣ጁንታው የዘረፈው በድሮን ሲመቱ የነበሩት ከባድ ብረቶች የሃገር ንብረት ነው ይሄ እንድናጣ አድርጓል።

ባጠቃላይ ይሄ ሁሉ ነገር እንዲደርስ ምክንያት የሆነው ጦሰኛ ጁንታ ህወሓት ነው ምንም ክርክር የለውም። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነው ሰፊ በደል ደርሶበታል አሁን እንካሰው።

ጁንታ ህወሓት በሰሜን እዝ የፈፀመው አሰቃቂ በደል ግፍ መቼም የሚረሳ አይደለም እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ቤት ያንዃዃ በደል ነው። የትግራይ ህዝብ የማይመጥን ስለሆነ እንደ ህዝብ ይቅርታ ልንጠይቅበት የሚገባ ነገር ነው። ሰራዊቱ ተቀይሟል።





https://www.facebook.com/GeezMedia/post ... 1599348116