Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

ሚስማር ጁሓ ወይም የጁሓ ምስማር ምንድነው ?

Post by Abe Abraham » 18 Jan 2021, 01:45


ሚስማር ጁሓ ወይም የጁሓ ምስማር ምንድነው ?

ጁሓ* በጣም የሚወደው ቤት ነበረው ። ቤቱን ለመሸጥ ፈለገ ። በቀላሉ ከቤቱ መላያየት ግን ከበደው ። ኣንድ ቀን ለኣንድ ቤቱን ሊገዛ የመጣው ሰው እንዲህ ብሎ ተናገረው ፥ " ቤቱን እሸጥልሃለሁ ፡ ግድ የለም፡ ሆኖ ግን ስንስማማ በቤቱ ውስጥ በጣም የምወዳት ምስማር ኣልችኝ ስለ'ዚህ ከግዜ ወደ ግዜ መጥቼ ልጎበኛት ብታፈቅድልኝ ቆንጆ ይሆናል ። " ገዢው እሺ ብሎ ቤቱን ገዛው ። ከጥቂት ሳምንታት ቡሃላ ሸያጭው በሩን ያንኳኳል ፡ ኣዲሱ ባለ-ንብረት ይከፍተዋል ገብቶ ደሞ ከምስማሩ ተዝናንቶ ይወጣል ። በመጪው ግዜ ይህ ኣካሄድ ይደጋገመል እስከ ሸያጩ በሸጠው ቤት ደንበኛ እስክሚሆን ድረስ !

ስለዚህ ነው ኣረቦች ኣንድ ትንሽ ነገር ነው ተብሎ ተገቢ ኣትኩሮ ካልተሰጠበት ያለፈ ነገር ተመልሶ ትልቅ ጣጣና ችግር ሲፈጥር " ሚስማር ጁሓ " ( የጁሓ ምስማር ) ብለው የሚጠሩት ። ያሁኑ የፈሸጋ ገበሬዎች ጉዳይ እንደ ወቅታዊ ምሳሌ ሊጠቀስ ይቻላል ።



* ጁሓ ካልተሳሳትኩ እንደ ኣባ ገብረ-ሃና የመሳሰሉት ለኣስተምሆ(በትግርኛ ዋዛ-ምስ-ቁም-ነገር እንለዋለን) የሚጠቅም የተረት ሰው ነው ።