Page 1 of 1

ሆያ ሆዬ ለገና (በጉራጌ)

Posted: 06 Jan 2021, 04:07
by Horus

የገና ጀምበር ፣ የንጋት ጨበር
የጽብሃ ኮከብ፣የጠጥበት ኢምር
ያሙነ ራዕይ ፣ የሰማይ የምድር
አስትሮ እሳት፣ የሶባ ጨረር
የሳባ ሃሩር፣ የበጋ አባር

የንጋት ገና፣ የጠዋት ጺዮን
ዬሎሄ ሶራ ፣ የቆሬ ብርሃን
ያዮ አይነቁር፣ የደራቃ አይን
የለሊት ጮራ፣ የቀናት በያን

የሶባ ጾራ፣ራዕይ የዛኘት
የገና ውልደት፣ የገና ፍጥረት
እንሰሳ ከሰው የተለየበት
አዳም ከምኝት የተነሳበት
ኮከብ ጭለማን ያሸነፈ እለት
የብርሃን ገና የብርሃን ልደት :!: :idea:

ሆረስ አይነ ኩሉ
በ2021 ገና ዋዜማ


Re: ሆያ ሆዬ ለገና (በጉራጌ)

Posted: 06 Jan 2021, 04:27
by Horus

Re: ሆያ ሆዬ ለገና (በጉራጌ)

Posted: 06 Jan 2021, 14:59
by Horus
ዬቦ ለገና አምላክ!

በሁለት አጭር ወራት ኢትዮጵያን ከቆሻሻው ዎያኔ የገላገላት!

አሜሪካን ከዘረኞች ነጻ ያረጋት!

የኬር ገና ለኢትዮጵያ የብርሃን ልጆች!!

Re: ሆያ ሆዬ ለገና (በጉራጌ)

Posted: 07 Jan 2021, 00:38
by Horus
እንኳን ለዚህ እጹብ ድንቅ ወራት የገና ወቅት አደረሰን !!

Re: ሆያ ሆዬ ለገና (በጉራጌ)

Posted: 07 Jan 2021, 00:43
by Noble Amhara

Re: ሆያ ሆዬ ለገና (በጉራጌ)

Posted: 07 Jan 2021, 02:46
by Horus
ገና ገና ገና ገና ገና

አበሻ እንደ ፈረደብት ፈረንጅን እንደ እግዚአብሄር ማምለክ ነው ባህሪው ።

ገና ጠማማ ዱላ ማለት አይደለም ።

አሲና ገናዬ ማለት እነሆ ገና ማለት ነው ።

ገና ልደት ማለት ነው ።

ይህ ተነጋሪ ይዘባርቃል እንጂ አንቃት የጥንት ግብጽ ቃል ሲሆን ትርጉሙ የህይወት መነሳት፣ መውጣት ፣ ልደት ማለት ነው።

ዱላ፣ በትር፣ ሩር፣ ጥንግ በስረ ቃላቸው ጸሃይ ወይም ብርሃን እንጂ ሌላ ዘመናዊ ትርጉም የላቸውም።

ጥልቅ ጥናትና እውቀት የሌላቸው ብዙ ባይሉ ጥሩ ነው !!

በሁሉ ነገር ዘሎ ወደ ቱሪስት ሸቃጭነት መሮጥ ያሳፍራል !!

እዚህ ምት ሰሙት ወረኛ ደቡብ ደቡብ ይላል ፣ ደቡብ ከሚለው ሕዝብ እንደ ባህል ገና የሚጫወት ጉራጌ ብቻ ነው። ያን ማለት አይፈልግም ፈሶ !!