Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42400
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በትግሬ ጦርነት ላይ ሃያ ሙሉ ፊልሞች መሥራት ይቻላል

Post by Horus » 31 Dec 2020, 03:46

ከዚህ በኋላ ያለው የትህነግ አልሞት ባይ ተጋዳይነት በትናንሽ የደፈጣ ዉጊያ የሚዘጋ ስለሆነ ከዚህ በኋላ በትግሬ ለሙሉ ፊልም መጣኝ የሆነ ፕሎት ሊፈጠር አይችልም ። ባለፈው ወር በተደረገው የ30 ቀን ጦርነት ላይ ግን ቢያንስ ሃያ ሙሉ ፊልሞችን የሚያጽፍ ድርጊት ተፈጽሟል ። ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት አመታት በኢትዮጵያ እስማርት የፊልም እስክሪፕት የሚጽፉ ካሉ እነሆ ሃሳቤን በነጻ!

አንድ፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሚመልከት አንድ ወይም ብዙ ኤፒክ የጀግንነት እና መስዋዕትነትፊልሞች መስራት እጅግ ቀላል ነው።

ሁለት፣ ስለ ትህነግ ምኞት ወይም መሻት 6 ፊልሞች መስራት ይቻላል። የነዚህ ፊልሞች ፕሎቶች፡ ስግብግብነት፣ ሁሉን ያዥነት፣ ጠላትነት፣ የፍላጎት መስዋዕትነት ፣ የበታችነት፣ ጭፍን ምኞት ። በፊልም ቲኦሪ ውስጥ እነዚህ ባህሪያት ወይም የታሪክ ፕሎቶችስ እያንዳንዱ አንድ ፊልም ሊሰራባቸው ይችላል።

ሶስት፣ ትህነግ ምን እንደ ሚያደርግ ያውቅ ነበርን በሚለው ጥያቄ ላይ ሁለት ፊልም መስራት ይቻላል። ከሁለቱ ፕሎቶች አንዱ ከእግዚአብሄር ጋር መዋጋት እና የተሳሳተ ስሌት ይባላሉ ። እነዚህ እግጅ ግዙፍ የትህነግ ወድቀት ምክንያቶች ናቸው

አራት፣ የትህነግ ችሎታ በተመለከተ ሁለት ፊልሞች መጻፍ ይቻላል። እነሱም የጠፊ ድድብና (ድንቁርና) እና ጭፍን እስትራተጂ ናቸው ። አንዱ ፌታል ኢምፕሩደንስ ሲባል ሌላው ኤሮኒየስ ጃጅመንት ይባላል።

አምስት፣ የትህነግ ትግበራ ወይም ፐርፎርማንስ በተመለከተ ሶስት ፊልሞች መስራት ይቻላል። እነሱም ከላይ ያለው አጥፊ ድድብና፣ አመጽ (ሕገ ወጥነት)፣ እገታ (ውንብድና)፣ ናቸው።

ስድስት፣ የትህነግ አመጽ ወይም ውንብድና ውጤቶች ምንድን ናቸው? ዎያኔ ምን አተረፈ? በሚለው ላይ አራት ፊልሞች ማዘጋጀት ይቻላል። እነሱም ዲስአስተር (ጥፋት)፣ የከሸፈ ምኞት፣ ጸጸት፣ የያዙትን ማጣት ናቸው።

ሰባት፣ የትህነግ አመጽ ትርጉም ምንድን ነው? ለሚለው አንድ ፊልም ግራግብት የሚል ፕሎት ይኖረዋል። ብዙዎቻችሁ ይህን ፖስት መከታተል ይከብዳችሁ ይሆናል፣ የፊልም እስክሪፕት መጻፍ ሃሳብና ልምድ ለሌላችሁ። ግን የፊልም ወይም የቲያትር ድርሰት ምን እንደ ሆነ ለሚያውቁ እጅግ ጠቃሚ ጥቆማ ነው ፤ በትኮራ አንብቡት፣ ተጠቀሙበት፣ ለሚጠቀሙበት አስተላልፉት ።

ኬር ገና !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42400
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በትግሬ ጦርነት ላይ ሃያ ሙሉ ፊልሞች መሥራት ይቻላል

Post by Horus » 02 Jan 2021, 01:58

አው ያበሻ ፊልም ጸሃፊዎች በአይናቸው ስር ያለውን ትልቅ ታሪክና የድራማ ፖሎት ማየት ሳይችሉ የፈንጅ ሲሊማ ኮፒ ማደግ ላይ ነው የተጠመዱት !

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: በትግሬ ጦርነት ላይ ሃያ ሙሉ ፊልሞች መሥራት ይቻላል

Post by Wedi » 02 Jan 2021, 02:35

Horus እረ ከ100 በላይ ድንቅ ምርጥ ፊልሞች መስራት ይቻላል!!



የህወሃት(ጁንታ) ባህርያት በጥቂቱ፦

1-የሀገር ክህደት
2-ዘረኝነት
3-ሌብነት
4-አድልኦ
5-ሙስና
6-ማጭበርበር
7-አድመኝነት
8-የዘር ማጣፋት ወንጀል jenocide
9-ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር
10-የሰዎች የውስጥ አካል ሽያጭ(የሚጣራ)
11-ህገ ወጥ የጦር መሳርያ ዝውውር
12-የከተማ መሬት ምዝበራ
13-የሀገር ሀብት ማባከን
14-ከጠላት ሀገር ጋር በመወገን ሀገርን መውጋት
15-የሀገርን ሚስጢር ለጠላት አሳልፎ መስጠት
16-ብሄርን በብሄር ላይ ማነሳሳት
17-ሀገርን ለመገንጠል ማሴር
18-መከላከያ ሰራዊትን መውጋት
19-ታላላቅ ግድያዎች
20-የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ወዘተ ናቸው

Horus
Senior Member+
Posts: 42400
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በትግሬ ጦርነት ላይ ሃያ ሙሉ ፊልሞች መሥራት ይቻላል

Post by Horus » 02 Jan 2021, 02:43

Wedi wrote:
02 Jan 2021, 02:35
Horus እረ ከ100 በላይ ድንቅ ምርጥ ፊልሞች መስራት ይቻላል!!
Wedi

ጥሩ 20 ! ግ ን ልብ በል ፕሎቱ ድራማ ሆኖ የሚተገበር መሆን አለበት ። ስለዚህ አክት በሚደርጉበት ደረጃ አውርዳቸው ! አው የፊልም ወይም የድራማ ባለ ሙያዎች ለዙ አመት የሚሆን ፕሎቶች አግኝተዋል ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: በትግሬ ጦርነት ላይ ሃያ ሙሉ ፊልሞች መሥራት ይቻላል

Post by Abe Abraham » 02 Jan 2021, 15:39

Horus wrote:
02 Jan 2021, 01:58
አው ያበሻ ፊልም ጸሃፊዎች በአይናቸው ስር ያለውን ትልቅ ታሪክና የድራማ ፖሎት ማየት ሳይችሉ የፈንጅ ሲሊማ ኮፒ ማደግ ላይ ነው የተጠመዱት !
ረጋ ብለው የሚያስፈልጋቸው ግዜ ወስደው የሚሰሩ ኣይመስለኝም ። ስለዚ ነው ኣብዛኛው ግዜ እንደ ናይጀርያውያን "የጥቁር ስራ " የሚያቀርቡት ። በኢትዮጵያ የኣክተሮች ሊሆኑ የሚበቁ ቆንጆ ሴቶች እጥረት የለም ። ሌሎችም እንደዝያም ። ዋና ችግሩ የመጻፍና የተራቀቀ የፍልም መቅረጽና ማንሳት ነው ።

በኢትዮጵያ ታሪክና ባሁን ላይ ያለውን ክስተት ከስነ-ጽሑፍ ደባልቆ ትልቅ ትረካ የመጻፍ ምሉ እድል ኣለ ። ሆኖ ግን ኣብዛኞች ተናጋሪዎችና እና የመጻፍ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ግዜያቸው በፖለቲካ ብቻ ነው የሚያሳልፉት ።

Post Reply