ኧረ እኔ በሳቅ ፈነዳሁ። ወያኔ ትግራይ ሠልጥና ሚሳይል እስከ አፍንጫዋ ታጥቃለች አለችን ሰርቃ።ጉድኛ ዝንጀሮ ከሰው ክምር ነዶ ሰርቆ አራሽ ገበሬ ነኝ ብሎ ይፎክራል።
አሥራ ሦስት ፍሬ ሚሳይል ሰርቃ እነ ሃላፊመንገድ የትግሬ ካርታ ከሱዳን እስከ ጅቡቲ ቀይ ባህር፣ከወሎ አስከ ኤርትራ፣ወዘተ ሰርተው ዳንኪራ ጨፈሩበት። እርግዝና ከሆነም ይገፋል ቂጣ ከሆነም አድሮ ይጠፋል ይሉ ዘንድ ነገሩ በጎጆ መጋዝን ተሰርቃ የተቀመጠች ሮኬት ነበረች። እግዜር ይኸን ቀልበ ጠባብነት አይቶ ኒዮክለር ነሳቸው እንጅ ህልማቸው እሩቅ ነበር።