Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ በተባለ ቀበሌ የሚኖሩ 13 የሚሆኑ የ4 አባዎራ ቤተሰቦችን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከፊሎችን በአሰቃቂ መልኩ አንበርክከው በጥይ ረሽነዋል

Post by Za-Ilmaknun » 28 Dec 2020, 13:55

በሆሮ ጉድሮ ዞን ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ አመራሮች ሀይል ባለመላካቸው የተነሳ 13 የሚሆኑ አማራዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይትና በስለት በግፍ ተገደሉ፤ በርካቶች አድራሻቸው አልታወቀም።በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ በተባለ ቀበሌ የሚኖሩ 13 የሚሆኑ የ4 አባዎራ ቤተሰቦችን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከፊሎችን በአሰቃቂ መልኩ አንበርክከው በጥይት ረሽነዋል፤ ቀሪዎችን ሴትና ህጻናት በገጀራ፣በቆንጨራ እና በካራ እንዳረዷቸው ነው ከአሸባሪዎች ጥቃት ያመለጡ ነዋሪዎች የተናገሩት።

ከተገደሉት መካከልም 2 አዛውንቶች ሲገኙበት አብዛኞች እናቶችና ህጻናት ናቸው፤ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል።በተጨማሪም የ7 ኛ ክፍል ተማሪው ሀሚድ ይብሬ ቆስሎ ህክምና ባለማግኘቱ ከሌሊቱ 10:30 ሰዓት ላይ ህይወቱ አልፏል፤ ሀሰን ይብሬ የተባለ አባትም ታፋው ላይ በጥይት ቆስሎ እየተሰቃዬ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የአቶ አህመድ ገዳሙ 7 ቤተሰብ፣ የእስሌማን መሀመድ 13 ቤተሰብ፣የአቶ ፈንታው አያሌው 7 ቤተሰብና ሌሎችንም እስካሁን የት እንዳደረሷቸው ለማወቅ አልተቻለም ብለዋል።ለሚሊሻ ተብሎ ከላይ የሚላከው ጥይትም ለኦነግ ሸኔ ተላልፎ እንደሚላክ ፤ ለሚሊሻዎች ግን ቀናንሰው 4 እና 5 ጥይት ብቻ እንደሚሰጧቸው ነው ምንጫችን የገለፁት።

ኦነግ ሸኔ ከታህሳስ 15 እስከ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት እስከ 60 የሚደርሱ ተባባሪዎቹን ይዞ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ደረስ እየተሰበሰበ መሆኑን በመግለፅ ለጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ መስተዳድር እና ለልዩ ሀይሎች ብንደውልም ጩኸታችንና ጥሪያችን ባለመስማት ወረዳው ነው ያስፈጀን ብለዋል፤ ልዩ ሀይሉም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አለው ሲሉም አክለዋል።

https://mereja.com/amharic/v2/429056