Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42376
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ገና (ልደት) ልክ 2 ሳምንት ቀረው !

Post by Horus » 24 Dec 2020, 03:14

Last edited by Horus on 24 Dec 2020, 03:56, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42376
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና ልክ 2 ሳምንት ቀረው !

Post by Horus » 24 Dec 2020, 03:34

አንጋቻ ማለት ድመት ማለት ነው !!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42376
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና ልክ 2 ሳምንት ቀረው !

Post by Horus » 24 Dec 2020, 03:52

Character Matters!!


eden
Senior Member
Posts: 10085
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: ገና (ልደት) ልክ 2 ሳምንት ቀረው !

Post by eden » 25 Dec 2020, 15:04

Horus wrote:
24 Dec 2020, 03:34
አንጋቻ ማለት ድመት ማለት ነው !!!!
Horus,

What's the significance of አንጋቻ. I know it has profound cultural (story telling) meaning.

I know Mesqel is # 1 holiday and all from cities go visit back home. what how about ገና (ልደት) how big is it compared to other holidays?

Horus
Senior Member+
Posts: 42376
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ገና (ልደት) ልክ 2 ሳምንት ቀረው !

Post by Horus » 25 Dec 2020, 18:45

ኤደን፣
አንጋቻ ምንም ሌላ ትርጉም የለውም፣ ድመት ማለት ነው ። የጠቀስኩት ከላይ ባለው የልጆቹ ሆያ ሆዬ (እኛ እንዞሪቴ እንለዋለን) ውስጥ ጥሩ ስጦታ ለሰጠች እናት (ሴት) ስናመሰግን ፣ ስንመርቅ የዛሬ አመት ወንድ ልጅ ይስጥሽ ስንል ምንም ላልሰጠችው ንፉግ የዛሬ አመት ድመት (አንጋቻ) ይስጥሽ አንላታለን። ስለሚያስቅ ነው የጠቀስኩት ።

ገና ያው ልደት ማለት ሲሆን የቃሉ ሌጣ ትርጉም ንጋት፣ የጸሃይ መውጣት፣ የጸሃይ ልደት ማለት ነው ። የብርሃን ልደትና የክርስቶስ ልደት በሜታፎር በምሳሌ ተያይዟል። በጉራጌዎች ዘንድ የቤተ ክርስቲያን (በአለ ወልድ) ቢከበርም በባህልነቱ የልጆችና ወጣቶች ባህል ነው።

ከላይ የምታየው የገና ጨዋታ (ሆኪ ጌም) ለአንድ ወር እንጫወተዋለን ። የመጨረሻው ግጥሚያ ቀበሌና ቀበሌ ተጫውተው ጥንግ (አንቃት) የሚባለው ክብ የክትክታ ስር አንደኛ ቀበሌ ድረስ ከተወሰደ ጎል እንደ ገባ ተቆጥሮ የወሩ ቶርናሜንት ይዘጋል። ያ የሚሆነው የገና ቀን ከሰአት በኋላ ነው።

ጎረምሶች በጥቅምት አቦ፣ በህዳር ሚካኤል ፣ በገና ቀን የፈረስ ጉግስ ያደርጋሉ። ይህ ከቦታ ቦታ ይለያያል ። አንዳንዱ ቦታ ፈረሰኛና ፈረሰኛ ነው። አንዳንድ ቦታ ቀበሌና ቀበሌ ነው ። ግ ን በመሰረቱ የገና በአል የልጆች ባህል ነው

ሆያ ሆዬ (እንዞሪቴ) አንድ ቀን ሳይ ከአንድ እስከ 2 ሳምንት ነው የምንዞረው ማታ ማታ። ገንዘብ፣ እህል የሰጠናል ። እህሉን ሸጠን በተሰበሰበው ገንዘብ በግ ወይም ትንሽ ወይፈን ይገዛል። ከዚያም የገና እናት ትመረጣለች፣ ባልና ልጅ የሌላት አሮጊት እናት የሆኑ። እሷ ቤት ስጋው እስከሚያል እየተዘፈነ ይበላል ። ያቺ የገና እናት ስራ የሚፈልግ ነገር የሚቆፈር፣ የሚታደስ ነገር ሁሉ እነዚያ ልጆች ይሰሩላታ። ስለዚህ በገና ወር ቀን ቀን ከብት እያገድን ግና (አንቃት) እንጫወታለን ፣ ማታ ምታ ከብት ካስገባን በኋላ እንዞሪቴ እየዞርን ገንዘብ ሰብስበን በገና እናት ቤት ለሳንምት ያህል እንከትማለን ። በገና እለት ታቦት ከገባ ኋላ ሜዳ ለሜዳ ልጆች በየቀበሌያችን ቦድነን አንዱ ቀበሌ አሸንፎ ሊመሽ አካባቢ ያበቃል ።
ኬር

eden
Senior Member
Posts: 10085
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: ገና (ልደት) ልክ 2 ሳምንት ቀረው !

Post by eden » 25 Dec 2020, 23:38

Thanks for sharing Horus. I found it fascinating and it took me back to my own childhood.

Post Reply