Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Kasahun Wolde-Georgis : Too much politics and social studies in Ethiopia

Post by Abe Abraham » 20 Dec 2020, 07:22

ድሮ ተምረን የሚሉት ጥራዝ-ነጠቅና ያልበሰሉ ሰዎች ከነጮች የማርክስና ሌኒን ሃሳብ ተበድረው ሃገሪትዋን በ ' ላብ ኣደር " ፡ " ኣርሶ ኣደር " " ከበርቴ " " ንቃተ-ህሊና " " የጋርዮሽ ስርዓት " ሞልተው የጥንት ሃይማኖቱን ኣቋሽሸው በእድሜ የገፉው ንጉሱን ገድለዉ ኢትዮጵያን የኣለም ማሳቅያ ኣደረግዋት ። ብዙ ደም ደሞ ፈሰሰ በጓድ መንግስቱ ሃይለ-ማርያም ። መንግስቱ ወደ ዚምባብወ ኣፍሪቃውያን ወንድሞችን ለመጎብኘት ሄዶ እዛ ሲቀር ኣልባናውያን የኣንዋር ኸሊል ኾጃ ተከታያች በኣቶ ከፋፎሎ ይግዛቸው ተመርተው ስልጣን ይዘው ስለ " ክልል " " ብሄር ብሄረ-ሰቦች " " ቢሮክራቲክ ካፒታሊዝም " " ኣርቲክል 69 " " ችግራይ ትስፋፋ ኣንጋፋው እንዲ ሰፋ " '' መንግስቱ በየኣንጋፋው ኢትዮጵያዊነት ይቀና ነበር " "" ኣቦይ - ለምሳሌ ኣቦይ ስብሃት " " ዲቨሎፕመንታል ግማሹ ለኔ የቀረው ላንተ ኤኮኖሚ " የሚሉ ሃሳቦች ኣስርጸው ወደ ሃገረ-ሰላምና ወርቅ-ኣምባ ሄደው ቀሩ ( ፍለጋው እየቀጠለ ነው ) ። ኣሁን ንግግሩ ስለ " ፈደራሊስቲክ-ኮንፈደራሊስቲክ-ማልቲ-ናሽናሊስቲክ ደሞክራቲስቲክ ፖፑላሪስቲክ ኣስተዳደር ፍልስፍና - የ ቺካጎው ፕሮፈሰር ኤፒስቲን መጽሓፍ መሰረት ያደረገ " ነው ። ሰዎች ለምን ስለ " ፊዚክስ " እና " ማተማቲክስ " ኣይናገሩም ? ለመጻኢ እሱ ነው የሚጠቅመው ።

ጋሽ ካሳሁን ወልደ-ጊዮርጊስ ( የገብሬ ልጅ )