Page 1 of 1

ጋዜጠኝነት እንዴ ስዩም ተሾመ ከሆነ እኔ በአፍንጫዬ ይውጣ::

Posted: 19 Dec 2020, 11:47
by Abere
ጋዜጠኝነት እንዴ ስዩም ተሾመ ከሆነ እኔ በአፍንጫዬ ይውጣ::እኔ እኮ ጋዜጠኝነት ወይም የፓለቲካ ተንታኝ በሥነ-ምግባር እና በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተመረኮዘ ለአድምጭ ህዝብ የሚያቀርብ ነበር የሚመስለኝ።

ሰሞነኛውን ብልፅግና ፓርቲን የሚቃወም ሀሳብ ያለው በሙሉ በነካካ እጅ ማጥፋት የሚል ወቅታዊ አሰላለፍ ለማሳመር በፓለቲካ ትንታኔ እና አጢኖ የተካነውን የኤርምያስ ለገሠን ስም ለማጥፋት ስዩም ተሾመ የሄደበት መንገድ እጅግ አስቂኝ ብቻ ሳይሆን በእውነት የአድማጭን የማስላት እና መረጃ የማበጠር ችሎታ እንዴ መሳደብ ይቆጠራል። እጅግ የወረደ ነው። በመጀመሪያ የወጭ እና ገቢ ፍጆታ የግል ማስታወሻ የሚመስል ሰንጠረዥ በሀሰት በመስራት ኤርሚያስ ከጌታቸው አሰፋ ደመወዝ ተከፋይ እንደ ሆነ ወሬ ተሰራጨ። ያ ሰንጠረዥ ሙሉ በሙሉ ውሸት ነበር - ለምን ቢባል ማንም ሰው ሊሰራው በእጁ ፅፎ ሊሰራው የሚችል። ወይ የባንክ ሂሳብ ቁጥር የለው፣ ወይ ሙሉ አመታዊ የወያኔ የኦዲት ሂሳብ መረጃ ላይ አልታዬ። በመቀጠል ማንም ያ አልሰራ በማለቱ እንዴ ገና የውሸት ኢ-ሜይል አስመስለው ፅፈው የኤርምያስ ነው አሉን። እንዴዛ አይነት በእንግሊዘኛ እና በአማረኛ የተተረጎመ በMicrosft Word ሶፍትዌር የተፃፈ የኢንፎርሜሽን ፎረንዚክ መረጃ መስፈርት አያሟላም። ስዩም አቀብት ቁልቁለት እንድሁ በከንቱ ክሚታክት ለምን በሀሳብ በልጦ አይገኝም። ለመሆኑ የእርሱን የእራሱን ከብልፅግና ወይም ሌላ አካል ኦነግም ሊሆን ይችላል ያለውን የሂሳብ የውል ሰነድ ለምን አያቀርባም። ለመሆኑ እርሱ እራሱ ምን ያህል ንፁህ ነው።

በመጨረሻ እኛ አንድን ግለሰብ ወይም ሚድያ መመዘን ያለብን በሚድያው ላይ የሚያቀርበው ሃሳብ ከኢትዮጵያ ህዝብ አመላከት እና ምኞት ጋር ይጣጣማል ወይ ነው። የፓለቲካ ትንታኔው ከኢትዮጵያ ጥቅም እና ፍላጎት በሚድያው ተለይቶ ካየነው ተፃራሪ ሃሳብ ነው - በዚያን ሰዓት ግን እኛም እንቃወማለን። እስከ አሁን ግን ኤርሚያስ ይሁን ኢትዮ 360 ምንም መጥፎ ነገር ሲያቀርቡ አልሰማንም። እንደ ስዩም ተሾመ ዓይነቶቹ ተደጋፊ ተደማሪዎች አጀንዳ ግን እውነቱን ለህዝብ የሚያበስሩትን ማጥፋት/ Killing the messenger/ እንጅ የኢትዮጵያን ችግር መንስዔ ማጥፋት አይደለም። እውነት የሚናገሩትን ማዳመጥ አንዳንድ ጊዜም በደመ ነፍስ ተሽቀዳድመን ከመኮነን ጊዜ ወስደን ማጣራት ባህላችን ይሁን።

Re: ጋዜጠኝነት እንዴ ስዩም ተሾመ ከሆነ እኔ በአፍንጫዬ ይውጣ::

Posted: 19 Dec 2020, 11:58
by Wedi
ስዮም ተሾመ እኮ የማይረባ ጥጃ ነው!! ደግሞ ጋዚጠኛ ብለህ አትጥረው፣ ጋዚጠኛ አይደለም፡፡ ጋዚጠኛ የሚባለው የተከበረ ሙያ ነው፣ እንደ ስዮን ተሾመ ያለ አንድም የጋጠኛነት ትምህርት ያልተከታተለ ሰው እንዴት ነው ጋዚጠኛ ተብሎ የሚጠራው?

ስዮም ተሾመን ጋዚጠኛ ብሎ መጥራት ለጋዘጠኛነት ሙያ ስድብ ነው!!

Re: ጋዜጠኝነት እንዴ ስዩም ተሾመ ከሆነ እኔ በአፍንጫዬ ይውጣ::

Posted: 19 Dec 2020, 12:08
by Abere
Wedi wrote:
19 Dec 2020, 11:58
ስዮም ተሾመ እኮ የማይረባ ጥጃ ነው!! ደግሞ ጋዚጠኛ ብለህ አትጥረው፣ ጋዚጠኛ አይደለም፡፡ ጋዚጠኛ የሚባለው የተከበረ ሙያ ነው፣ እንደ ስዮን ተሾመ ያለ አንድም የጋጠኛነት ትምህርት ያልተከታተለ ሰው እንዴት ነው ጋዚጠኛ ተብሎ የሚጠራው?

ስዮም ተሾመን ጋዚጠኛ ብሎ መጥራት ለጋዘጠኛነት ሙያ ስድብ ነው!!
ትክክል ነው ያልከው። የጋዜጠኝነት ሙያ ክቡር ነው። ለእርሱ አይመጥነውም።

Re: ጋዜጠኝነት እንዴ ስዩም ተሾመ ከሆነ እኔ በአፍንጫዬ ይውጣ::

Posted: 19 Dec 2020, 14:43
by Lakeshore
ኣበረ አና ወዲ ስዩምን ስትቃወሙ ኢናንተም ቢሆን አንዲሁ በደፈናው ግለሰቡን ከመሳደብ አና ከማጥላላት በስተቅር ምንም ያቀረባች ሁት ማሰረጃ የለም።
ከሱ የምትጠብቁትን ሙያተኝነት ደረጃ አናተም አሱን ስትቃወሙ ኣላሳያች ሁም።
ይህ ይህ ያቀረባቸው ሃሳቦች ትክክል ኣይደሉም ብላች ሁ ማሰረጃዎቹን በማቅረብ መተቸት ሲገባች ሁ ዝምብላች ሁ አሱን መኮነን በራሱ ኣፍራሽ ነው። ስዩም የሚያቀርባቸው የመረጃ ትንታኔዎች ሙሉ በ ሙሉ አንኳን ትክክል ኣይደሉም ብንል ግን ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባቸውን ነገሮች ለሚመለከተው ኣካል በምጠቆም በጣም ጥሩ ስራ አየሰራነው በዬ ኣምናል ሁ።
ስለዚህ ነቀፋው ወደ ቀረበው ሃሳብ ብቻ ያተኮረ ቢሆንና አኛስ ምን ኣደረግረናል ከሚለው ጋር ኣብሮ ቢታይ ና ሰዎችን ከማቃለል ብንቆጠብ።