Page 1 of 1

የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 04:17
by Horus
እያመለጡ ያሉበት ዘዴ እንደ ሚከተለው ነው ።

በአሜሪካ፣ አውሮፓና እስራኤል እጅግ ከፍተኛ የኮማንዶና ልዩ ኦፐሬሽን ስልጠና ያላቸው ገንዘብ ተከፍሏቸው በጣም ከባድ የሆኑ ኦፐሬሽኖችና ሚሽኖችን የሚያከናውኑ ቅጥረኛ (Soldiers of Fortune) አሉ ። እነዚህ ብዙ ኢሊዮን ዶላር የሚያስከፍሉ እግጅ ጠንካሮች ከተለያዩ አገር ልዩ ሃይሎች የወጡና በጣም ምስጢር ለሆኑ ሚሽኖች የሚገዙ የቅጥር ወታደሮች ናቸው።

ድሮ ትህነግ በረሃ በነበረ ግዜ ሁሉ ካርቱም ቤዝ አድረገው በእርዳታ ስም መሳሪያ በረሃ ድረስ ለማቀበል ያሜሪካ መንግስት፣ እንግሊዝ በምስጢር ይቀጥሯቸው ነበር ። አንዱ የነሱ አቀናባሪ አብዱ መሃመድ አባ ቦራ ነበር ፣ ካርቱም ሱዳን ።

ዛሬም ተመሳሳይ የግል ድርጅት ያላቸው ፣ ብሎም ከብዙ መንግስታትና የስለላ፣ የደህነንት ድርጅቶ እንደ ሞሳድ፣ ሲ አይ ኤ፣ ኤም 7 ጋር የሚሰሩ ናቸው እጅግ ረቂቅ ቲክኖሎጂና ማናልባትም በራዳር ማይታይ ሄሊኮፕተር ይዘው ወያኔዎቹን በለሊት መንጥቀው እንደ ሚያሸሿቸው ጥርጥር የለውም።

ለዚህ ደሞ ቴድሮስ አዳኖም ፣ ሰዬ ወዘተ ከውጭ ሆነው ባሁን ሰዓት ሚሽኑን ቢያቀናብሩ መደነቅ የለብንም ። ይሞክሩታል ፣ ያደርጉታል ።

የኢትዮጵያ ደህንነት ይህን መሰል እጅግ ከፍተኛና ረቂቅ እርምጃ ለመቋቋም ያለው ብቃት እኛ ሲቪል ሰዎች ልናውቅ አንችልም ። የትግሬን ሰማይ ቀንና ለሊት መጠበቅ እንደ አለበት ግን እናውቃለን ።

ሌላው ነገር ወንጀለኞቹ ሁሉም ለየብቻ ተበታትነዋል የሚለው ሙሉ በሙሉ ትክክል ሊሆን አይችልም ። አንድ ብቻውን የተደበቀ ዎያኔ አንድ ሙሉ የአለም አቀፍ መርሲነሪ ልዩ ሃይል ሊቀጥር አይችልም ። ሰዎቹ ላንድ ሰው ብለው የህይወት ሪስክ መውሰድ ስለማይፈልጉ።

ስለሆነም የጁንታው ቡድን በአንድ ልዩ ሄሊኮፕተር ተሳፍረው ወደ ሆነ ደሴት ወይም ትንሽ አገር ወይም ግብጽ መሸሽ የሚችል ከ5 እስከ 10 ሰው ያለው ቡድን መሆን ግድ ይላቸዋል። ሚጓዙት ወይ ወደ ግብጽ፣ ወይ ወደ አንድ የቀይ ባህር ደሴት፣ ወይ ደቡብ ሱዳን ጫካ ነው ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ሰርዊትና ደህንነት ልክ አቢይ እንዳደረገው ከነሱ በጣም ቀድሞ በማሰብ መላ የትግሬን ሰማይና መሬት በቀንም በለሊትም ማየት መጠበቅ ይኖርበታል ።

ሰዎቹ ከዚህ በኋላ አንድ የባላገር ገበሬ ቤት ተደብቀው አይገኙም። እነሱ አሁን በአለም አቀፍ የግል ኮማንዶ ቡድን ተረድተው በማምለጥ ላይ ናቸው ።

ግዜ በተሰጣቸው ልክ የማምለጥ እድላቸው እያደገ ነው ።

በዚህ ግምት የምትስማሙ ሃሳቡን ለሚመለክተው ሁሉ አድርሱ እላለሁ ! አይነ ኩሉ ሆረስ !

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 04:29
by Horus





Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 11:28
by Horus
ይህ የሱዳን ጉዳይ ወንጀለኞቹን ለማስመለ በግብጽ የታቀደ መሆን አለበት

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 11:42
by Horus

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 12:34
by Guest1
አይነ ኩሉ ሆረስ !
:roll:
በጦርነት ሁኔታ ግማሹን ስራ የሚሰራው ፕሮፓጋንዳ ነው።
ሬዲዮ ለገጠሩ ህዝብ ይታደል ወይም በሳምንት ገበያ ላይ ማክሮፎን ጭኖ ፕሮፓጋንዳውን ማቀጣጠል ህዝብ እንዲረጋጋ።

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 16:10
by Horus
ማንም ሰው ለመገመት እንደ ሚችለው በመላ ትግሬ የተበተኑት ትህነጎች በሁለት የሚከፈሉ ይመስለኛል ። እስከ ሞት ለመዋጋት የወሰኑትና ሽሽተው ካገር የሚወጡት ። ለመዋጋት የወሰኑት ምን እንደ ሚያደርጉና የት እንዳሉ ማውቅ አያዳግትም ። ሲደራጁ፣ ሲንቀሳቀሱ፣ ሲያጠቁ ይታላያሉ ። እነሱ ችግር አይደሉም።

ካገር ለማምለጥ ያቀዱት ግን አንድ ቦታ ተቀምጠው አይገኙም ። ገበሬም፣ ነጋዴም፣ ቄስም፣ ለማኝም ቢመስሉ ዞሮ ዞሮ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አለባቸው ።እነሱ ሙቪንግ ታርጌት ናቸው። ደሞ ገንዘብ አላቸው ። ስለዚህ ለገንዘብ ብሎ እነሱን አሳልፎ የሚሰጥ የሚኖር አይመስለኝም።

ይልቅስ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ጽኑ ጸረ ትህነግ ሰዎችን በመላ ትግሬ በትኖ መፈለግ ነው ።

ከሁሉም በላይ በቅጥረኛ ኮማንዶች ረዳትነት ወይም በሱዳን ወታደሮች ረዳትነት ግብጽ እንዳይሸሹ በሮቹን መዝጋት ነው።

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 18 Dec 2020, 22:21
by Horus

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 19 Dec 2020, 03:03
by Horus
ያልተያዙት የጁንታው መሪዎች የት ነው ያሉት? ለዚህ ጥያቄ ያሉት መልሶች 4 ናቸው ።

አንዱ ቲኦሪ ሰዎቹ መቀሌና ሌላ ከተማ ውስጥ ተደብቀው ነው ያሉት፣ የትም አልሄዱም የሚል ነው ። ለምን ቢባል? ሰዎቹ የሸመገሉ ብዙ በሽታ ያላቸው ስለሆኑ ነው ።

ሁለተኛው ቲኦሪ ሰዎቹ ከተማ ትተው በትግሬ ባላገር ተበታትነው ነው ያሉት የሚል ነው ! ከዚያስ ምን የማድረግ አላማ አላቸው ለሚለው ይህ ቲኦሪ መልስ የለውም ።

ሶስተኛው ቲኦሪ ሰዎቹ በተከዜና ሌሎች የትግሬ በረሃዎችና ተራሮች ውስጥ አዲስ የጎሬላ ዉጊያ እየደራጁ ነው የሚል ነው ።

አራተኛው የኔ ሆረስ ቲኦሪ ሰዎቹ በትናንሽ ቡድን ተከፋፍለው በተለያዩ የውጭ ኮማንዶዎች በመረዳት ወደ ቀይ ባህር፣ የመን፣ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን ኬኒያ ለመሸሽ እያሴሩ ነው የሚል ነው ።

What is the truth?

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 19 Dec 2020, 04:59
by Horus

Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 19 Dec 2020, 18:50
by Horus
ይሀው ሌላው ወንጀሎችን ማስመለጫው ሴራ !!


Re: የትህነግ ከፍተኛ መሪዎች እያመለጡ ነው

Posted: 19 Dec 2020, 19:14
by Horus
ይሄ ሰው ስለ ታሰሩ ሰዎች ምን አገባው?