Page 1 of 1

ከሰል የመሰለው ጀግና! ልክ እንደ ጥቁር ሰው !!!

Posted: 15 Dec 2020, 04:13
by Horus



Re: ከሰል የመሰለው ጀግና! ልክ እንደ ጥቁር ሰው !!!

Posted: 15 Dec 2020, 05:38
by Horus
አሁን ምን ያረጋል ፈሪ ማቀንቀኑ፣
አይበጠስ ቅጠል ካልደረሰ ቀኑ፤
ተብሎኮ ነበር ባባቶች ሲነገር፣
ብቻ ዛሬ ሆኖ የንቶ ፍንቶ ነገር፣
ሌባና ሰካራም ባንድነት ሲደመር፤

አይጥና አምበሳ ጦርነት ቢጋጠም፣
አያስደንቅ ምንም፣
ምንም አያስገርም፣
ጸሃይ እስኪወጣ አለሙ ቢጨልም፣
ጀግናው እስከ ሚያጥስ አረሙ ቢረዝም፤

ያ ነበር አበቅቴው እኛ የጠበቅነው፣
ያ ነበር ጨዋታው እኛ የጓጓነው፤

ያም ሆኖ አበቃ ጀግና ሰንጋ በላ፣
ፈሪ ጉድጓድ ማሰ በትግሬ በሞላ፣
ረጭ ክስም አለ ደግሞ ላይነሳ ከንግዲ በኋላ።