Page 1 of 1
የሚቀጥለው የአቢይ አህመድ ግዙፍ ስህተት፤ ሕወሃትን በአሸባሪነት ፈርጆ ሙሉ በሙሉ አለመደምሰስ
Posted: 04 Dec 2020, 17:05
by Horus
የኢትዮጵያ መንግስት ትህነግን ፍጹም ሕገ ወጥ ድርጅት አድርጎ እንደ ድርጅት ካልደመሰሰ፣ ካላፈረሰ በስተቀር ለርጅም ግዜ በምስጢር ከተደራጀ ትህነግ አሸባሪ ጋር በትግሬ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ጭምር የሽብር እንቅስቃሴዎችን ሲያሽኮረምም ይኖራል ። አቢይ ይህን ግዙፍ ስህተት ከመፈጸም እጅጉን መጠንቀቅ አለበት ።
አንድ፣ ትህነግ አሸባሪ ጽረ ኢትዮጵያ፣ ጸረ ሰላም፣ ጸረ ሕዝብ ድርጅት አድርጎ በሕግ መደንገግ ፣
ሁለት፣ በዚህ ድርጅት ስር ሆነ ስም መንቀሳቀስ ወንጀር እንደ ሆነ መደንገግ፣
ሶስት፣ የዚህን ድርጅት ነብረት የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ወርሶ የፌዴራሉን ለፌዲራል የክልሉን ለክክል መንግስት እና ለህጋዊ የትግሬ ፓርቲዎች መስጠት
አራት፣ የትህነግ አርማ፣ ምልክት፣ ማንኛውም የሚታይ የሚዳሰስ ቁሳቁሶችን መጠቀም ወንጀል አድርጎ መደንገግ ።
አምስት፣ በትህነግ ስምና አላማ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች፣ ቡድኖችን እያደኑ ለሕግ ማቅረብ፣ እንደ ሚቀርቡ ከወዲሁ ለትግሬ ወጣት ማሳወቅ ።
አበው እንደሚሉት አለው አለውና ሳይመታው ቀረ እንዳይሆን
Re: የሚቀጥለው የአቢይ አህመድ ግዙፍ ስህተት፤ ሕወሃትን በአሸባሪነት ፈርጆ ሙሉ በሙሉ አለመደምሰስ
Posted: 04 Dec 2020, 18:11
by Guest1
የኢትዮጵያ መንግስት ትህነግን ፍጹም ሕገ ወጥ ድርጅት አድርጎ እንደ ድርጅት ካልደመሰሰ፣ ካላፈረሰ በስተቀር ለርጅም ግዜ በምስጢር ከተደራጀ ትህነግ አሸባሪ ጋር በትግሬ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ጭምር የሽብር እንቅስቃሴዎችን ሲያሽኮረምም ይኖራል ። አቢይ ይህን ግዙፍ ስህተት ከመፈጸም እጅጉን መጠንቀቅ አለበት ።
አንድ፣ ትህነግ አሸባሪ ጽረ ኢትዮጵያ፣ ጸረ ሰላም፣ ጸረ ሕዝብ ድርጅት አድርጎ በሕግ መደንገግ ፣
ሁለት፣ በዚህ ድርጅት ስር ሆነ ስም መንቀሳቀስ ወንጀር እንደ ሆነ መደንገግ፣
ሶስት፣ የዚህን ድርጅት ነብረት የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ወርሶ የፌዴራሉን ለፌዲራል የክልሉን ለክክል መንግስት እና ለህጋዊ የትግሬ ፓርቲዎች መስጠት
አራት፣ የትህነግ አርማ፣ ምልክት፣ ማንኛውም የሚታይ የሚዳሰስ ቁሳቁሶችን መጠቀም ወንጀል አድርጎ መደንገግ ።
አምስት፣ በትህነግ ስምና አላማ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች፣ ቡድኖችን እያደኑ ለሕግ ማቅረብ፣ እንደ ሚቀርቡ ከወዲሁ ለትግሬ ወጣት ማሳወቅ ።
ህግ ለማስከበር እየተካሄደ ያለ ጦርነት አይደል? ይደመሣሉ ወይም ተይዘው ለፍርድ ይቀርባሉ። ያኔ በቀረበው ክስ መሰረት በሽብርተኛነት መመደባቸው የማይቀር ይመስላል። የፓርቲ ደንብና ስነስርኣት ስለጣሱ ከምርጫ ቦርዱ እውቅና አይኖራቸውም ማለት ህገወጥ ይደረጋሉ። በስማቸው ከቀጠሉና በህግ ወጥ ተግባር ከተሳተፈቱ እንደማንኛውም ድርጅት መንግስት ምላሽ ይሰጣል። ህገወጥ ፓርቲ መባሉ ስለማይቀር የፓርቲ አባል ነኝ ብሎ በግልጽ የምንቀሳቀስ አርማውም አይኖርም። በህቡዕ ይደራጁ ይሆናል። ገንዘብ በጃቸው ስለሆነ ሚርሲነሪ መቅጠርም ይችላሉ። ሽብሩ ከቀጠለ መንግስትም ሰላም ማስከበሩን ይቀጥልበታል። ምንድነው ችኮላው?
የድርጅቱን ንብረት ለትግራይ ክልል ይሰጥ ለምን አልተባለም? ጭራሽ ለፓርቲዎች ይሰጥ? የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ነው እየተባለ? ለትግራይ ፓርቲዎች ይሁን ከተባለ ለተቃዋሚ ፓርቲዎችም አረና ፈንቅልን ...ያካትታል? ክክክክክክክክ። የብልጽግና ፓርቲ ይወረሰው ለማለት ከሆነ ይዝረፍ እንደማለት ወይም ፓርቲዎችን መንግስት እየደለለ ህገወጥነትን እያስተማረ ነው ይባላል። መንግስት ጠላትና ወዳጅ ለየ ማለትስ አይሆንም? ክክክክክ
የንብረት ጉዳይን ፍርድ ቤቱ ከአገር ከዝና የተሰረቀውና በግል ወይም በድርጅት ያገኙትን ከለየ ብኋላ ለትግራይና ለተጎዱ የአማራ ክልሎች መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም ለኤርትራም ለተወረወረባት ሚሳኤል መካስ አለባቸው። ቀሪው ለመንግስት ገቢ ማድረግ። ባዶ ካዝና ነው የተረከበው አልተባለም? የዘመኑ የሃብት ክፍፍል የሚባለው ነገርን ተግባራዊ እናደርጋለን ከተባለ ለሁሉም ክልሎች ማከፋፈል ነዋ! አይ የኢትዮ ነገር!! የራሴ የምትለው ሃብት የሌላት፤ የራሴ የምትለው ጦር ያልነበራት፤ ደሃ አገር! በእንደዝህ አይነት አሰራር ከቀጠለ ለነገው ጦርነት አገሪቱ ትዘጋጅ። እንደገና ሁሉም ዜሮ ዜሮ
አጭር መልስ ህግ ይከበር!!
Re: የሚቀጥለው የአቢይ አህመድ ግዙፍ ስህተት፤ ሕወሃትን በአሸባሪነት ፈርጆ ሙሉ በሙሉ አለመደምሰስ
Posted: 04 Dec 2020, 19:33
by Horus
Guest
የምትለው ቢገባኝም ያን መሰል ሪቴይል (ችርቻሮ) አካሄድ ዝም ብሎ ነገሮችን ማወሳሰብ ነው። በኢትዮጵያ ፓርላማ አማካይነት ሙሉ በሙሉ ወንጀለኛ ሕግ ወጥ ድርጅት ማድረጉ ባገርም ሆነ ባለም ደረጃ ሰዎቹን ለማሳደድ እጅግ ይመቻል ። ይህ ድርጅትኮ ግዙፍ ወንጀር የሰራና ሚሰራ ነው። እነሱን መሰል ጠላት ፈጽሞ ጨርሶ መደምሰስ ነው ትክክለኛው መጽሃፍ ሚያዘው ። ሽብርተኛ ማለቱ መሰረታዊ ችግሩ ምንድን ነው ። ኦነግንም ይመለከታል፣ ለኦነግ ሲባል ትህነግም ታለፍ ከሆነ ያ ሌላ ሞቲቬሽን ነው ። ሕግ ማስከበርና አንድ ሽብርተኛ ድርጅት ሽብርተኛ ማለት ለየቅል ናቸው። ኪስ አቅላዊን ማሰርኮ ሕግ ማስከበር ነው ።
ያው ነገሩ የማይጸዳ ሽንፍላ እንደ ማለት ነው። ለማንኛውም ይታያል!!
Re: የሚቀጥለው የአቢይ አህመድ ግዙፍ ስህተት፤ ሕወሃትን በአሸባሪነት ፈርጆ ሙሉ በሙሉ አለመደምሰስ
Posted: 04 Dec 2020, 19:48
by Abere
ይመስለኛል ወያኔን አሸባሪ ብለን ከፈረጅን ኦነግን የግደታ አሸባሪ ማለት ይገባል የሚለው ሁኔታ ዐብይ አህመድን ግራ ያጋባው ይመስለኛል። ኦነግ እና ወያኔ ሁለቱም የአሸባሪ ቡድን መስፈርቶች ከመቶ ፐርሰንት በላይ ያሟላሉ። ሌላው የጎንዮሽ ስጋት እነኝ አሸባሪ ቡድኖች የጎሣ ርዕዮተ ዓለም ተከታዮች ስለሆኑ እነርሱን ማውገዝ እና በህግ መከልከል ሌሎች የጎሣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንድሁም እራሱን ብልፅግናን ጨምሮ በህግ ሊያስገድብ ይችላል የሚል ነው። እንዴሚታወቀው የጎሣ ፓርቲ እና ክልል ነው እነኝህን አሸባሪዎች ከዚህ የሽብር ጣርያ እንድ ወጡ ያደረሳቸው።
Re: የሚቀጥለው የአቢይ አህመድ ግዙፍ ስህተት፤ ሕወሃትን በአሸባሪነት ፈርጆ ሙሉ በሙሉ አለመደምሰስ
Posted: 04 Dec 2020, 20:21
by eden
Horus,
Have you considered the psychological impact on its base in seeing its struggle leaders in handcuffs while leaders of TPLF sister Parties of 30 years keep powerful positions in the country? Mind you, many families are related with TPLF one way or another.
Have you considered the loss to the country of administrative, diplomatic, business and military skills and experiences that could be used and transferred to next generation?
Have you considered, in the absence of TPLF, there may be lack of check and balance against dictatorship tendencies at local and federal level?
Do you believe the people there agree with your proposal? If they don't, would you insist and go ahead to use force against them using other people?
Re: የሚቀጥለው የአቢይ አህመድ ግዙፍ ስህተት፤ ሕወሃትን በአሸባሪነት ፈርጆ ሙሉ በሙሉ አለመደምሰስ
Posted: 04 Dec 2020, 21:35
by Horus
eden,
የትህነግ መሪዎች እጃቸው በካቴና መታበቱ እንዲያውም ትልቅ ትምህርት ነው፣ወደ አምባገነንነት ምኞት ላላቸውና በግፍ፣ በሌብነት መክበር ለሚሹ ። በቤተሰቦቻቸው ላይ ትልቅ ሳይኮሎጊያዊ ቁስል እንዳለው አቃለሁ። ስለዚህ ነውኮ ነው የሌባ ሚስት፣ የግፈኛ ልጅ መሆን የሌለብን ። አንድ ማህበረሰብ በውስጡ ያሉ ካንሰሮች ማስወገድ የጋራ ሃላፊነቱ ነው ። የሞራል ተመን ሲደረግ የጋራችን ደህንነት ከግለሰብ ጥቅም የሚልቀው ለዚህ ነው። ስለዚህ እዚህ ላይ የሞራል ኤቲካል ክርክር የለም።
የዎያኔ መሪዎች ለልምድና ክህሎታቸው ሲባል እንሽኮርምምላቸው የሚለው ትክክል አይደለም፣ ደሞን ያስቃል! እንደ አንድ ያመራር መደብ እንደ ትህነግ ቡድን ያለ እውቀት አልባ፣ አሳፋሪ ፣ ክህሎት አልባ የመሪዎች ቡድን ኢትዮጵያ ኖሮዋት አያቅም። ተመልከት የዎያኔ ጄኒራሎች ሁሉ በሌሉበት ሰራዊቱ የሚሰራውን ስራ?
የጎሳ ሚዛን ምንም ከዚህ ጋር አይያያዝም። የጎሳ ሰራት የሚኖር ከሆነ የትግሬ ህዝብ በሌላ ድርጅት ተወክሎ ሚዛኑን ይጫወጣል ። ትህነግ ምንም ታሪካዊ አስፈላጊነት የለውም ።
የትግራይ ሕዝብ ትህነግ ቢወገድላቸው ደስታውን አይችሉትም። አሁንኮ ትግሬ በትህነት እየተገዛ አይደለም ። ተስማማን !! ሃቁ ያ ነው ።
አቢይ ትህነግ ን አሸባሪ ሊለው ካልፈለገ ምክኛቱ ሌላ ነው የሚሆነው? ከኢሃዴግ እና ብልጽኛ ወይም ኦነግ ጋር የተያያዘ ነው የሚሆነው። ያም ሆነ ይህ ካላደረገው ስህተቱን ባጭር ግዜ የሚታይ ይሆናል ።
አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዲሉ !!!