Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15258
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ዐብይ አህመድ ለምን ስለምርጫ አሁን ያወራል? 1ኛ) ገና አገር አልተረጋጋም 2ኛ) የፓለቲካ ፓርቲ ገና የለም

Post by Abere » 02 Dec 2020, 15:22

ዐብይ አህመድ ለምን ስለምርጫ አሁን ያወራል? 1ኛ) ገና አገር አልተረጋጋም 2ኛ) የፓለቲካ ፓርቲ ገና የለም

በእኔ ግምት ገና ቢያንስ 3 ዓመታት ጊዜ ይፈጃል ብዙ መቀየር እና መሻሻል ያለባቸውን ሥራ ብቻ ለመስራት። ይኸ ቶሎቶሎ ዓይነት ነገር ያንኑ ወያኔን አሰራር ለማስቀጠል እና ለቀጣዩ ዘመናት ሥልጣን ይዞ ለመቆየት የሚደረግ ጥረት ያስመስላል። የህዝቡ አንገብጋቢ ጥያቄዎች እና የውይይት አጀንዳዎች የሆኑት ኢትዮጵያ እንዴ ሌሎች የዓለም አገራት ተአማኒነት ያለው የመስተዳደር አካሄድ ላይ ማሰብ ነው።
1ኛ) የጎሣ ፓለቲካል ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆን ይገባዋል። ይኸ ማለት ብልፅግና ኦደፓ፣ አደፓ፣ወዘተ ጨምሮ ይሆናል
2ኛ) የጎሣ ፌደሬሽን የሰበዓዊ ማህበረሰብ ሊከተለው የሚገባ ስነ-መንግሥት አይደለም። እንሰሳው ደመ-ነፍስ የሆነ የመንጋ አካሄድ ነው።የሰው ልጅ ከቋንቋ ወይም ስነ-ልሳን በላይ ነው።
3ኛ) የብዙሃን መገናኛዎች ይሁኑ ተፅእኖ ፈጣሪ ቡድኖች እና ግለሰቦች በኢትዮጵያዊነት ሥነ-ዜጋ እና ሞራል ላይ ከፍተኛ አስተምህሮ ማድረግ አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ጊዜ ይፈልጋል። ወያኔ እና ኦነግ በህዝብ መካከል የፈጠሩት የአመለካከት ፣ የስነ-ልቦና እና የጥላቻ ቀውስ እጅግ ግዙፍ ነው። ይኸ በጣም ስራ ይፈልጋል። በተጨማሪም በሶሻል ሜድያዎች እንዴ ምናየው ከፍተኛ ስነምግባር የጎደለው ባህርይ በዜጋ ዘንድ ተስፋፍቷል። ይኸም የእምነት ተቋማት እራሳቸውን ወደ ጥንታዊ ምግባራቸው በመመለስ ዜጋን ማረም መቻል አለባቸው።

--- ይህንን የመሳሰሉ እና ሌሎች ብዙ የተበላሹ ጉዳዮች ባሉበት ጥሩ ድሞክራሲ ሳይሆን በችኮላ ለመዝራት የሚታሰበው አሜካላ እሾ እና የወንጀል አዝርዕት ለማዘመር ይመስላል። ዐብይ አህመድ ትንሽ ጠለቅ አድርገህ ተመልከት። ምርጫ አያስፈልግም። እንደዛ ከሆነማ ወያኔም ምርጫ ማካሄዷ ትክክል ነበር ማለት ነው።