Please wait, video is loading...
መናበብና የጨዋታን ህግ ማወቅ ከድል ያደርሳል...
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡ ገራገር ኣይደሉም ግን ክፉ ሰው ናቸው ለማለትም አያስደፍሩም ~ ላሁን እንደው ፡ ዝም ብለን የሚሆናቸውን የሚያውቁ ብልህ ሰው ናቸው ብለን እንለፋቸውና ፡ የነዚህን ሁለት መሪዎች ግጥምጥሞሽ በጥቂቱ እንመርምር…
ጠቅላዩ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ የስኬት ሰው የሚያደረጋቸውን አንድ አንኳር እርምጃ ወሰዱ ~ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር አብሮ መስራት ~ የቀድሞዋ የLTV Hardtalk አዘጋጅ ቤተሊሔም አሰፋ ባንድ ወቅት የግንቦት 7ቱን ከፍተኛ አመራርና የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስንና ዶክተር አብይን በማገናኘቱ ረገድ የነበራቸውን ተራ ስትጥይቃቸው ~ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ክሬዲቱን መውሰድ ባይፈልጉም ፡ ከፕሬዝዳንቱ በወቅቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተገቢ መልስ መስጠታቸውን ገልጸው ነበር… "ከዚህ ልጅ ጋር መስራት ይቻላልን ? " ይጠይቃሉ ፕሬዝዳንቱ ~ አቶ አንዳርጋቸው "አዎን ፡ መስራት ይቻላል..." በምላሻቸው " በጥቂቱም ቢሆን ከየመን በወያኔ የጸጥታ ሰዎች ታግተው አዲስ አበባ ለእስር ከተዳረጉ በኋላ ፡ እድሜ ለታላቋ ብሪታኒያ መንግስት ወያኔ አኮላሽቶ ህይወታቸውን ሳይቀጥፍ ፡ የዶር አብይ ለውጥ መጥቶ ከእስር ሲፈቱ ፡ እኝህ ገብስማውና ደርባባው ሰው ፡ ከዶሩ የለውጡ መሪ አብይ አህመድ አሊ ጋር በመጠኑም ቢሆን ተገናኝተው ነበርና ~ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጥያቄ መልስ ለመስጠት አላቅማሙም ~ "አዎን መስራት ይቻላል" ነበር መልሳቸው…ታድያ ኢሳያስ "ካልክ ይሁና" ነበር መልሳቸው ~ እንግዴ ፡ ይህ በዚህ የቀጠለ ግንኙነት ፡ ዶር አብይን የኖቤል ሎሬት ተሸላሚ ከማድረጉ ባሻገር ፥ ያ እንደ ተራራ የማይገፋ ይመስል የነበረን መቀሌ የመሸገና የሰላም ጋሬጣ የሆነውን የህወሃትን አጥፊ ቡድን ፡ እንደ ጉም ሲበን እንዲያዩ አስድርጎላቸዋል ~ ፕሬዝዳንቱ ጠቅላዩን "እኔ የምልህን ብቻ ስማኝ ~ እመነኝ …በቀናት ውስጥ ዓለምን ጉድ ታሰኛታለህ ~ ስለ ኖቤል ሽልማትህ አትጨነቅ ፡ ሲፈልጉ ሽልማታቸውን መልሰው ይውሰዱት ፥ የነሱ ሽልማት መሸንገያ ነው ፡ እኔ የማሸልምህ ግን እውነተኛውን በህዝብህ ዘንድ የሚያስከብርህን ሽልማት ነው…" ያሉት ይመስላሉ ፕሬዝዳንቱ ፡ በዚህ የሰሞኑ የዲፕሎማሲና የተነጋገሩ ጋጋታ ከመስመሩ ፈልከት እንዳይል በየደቂቃው እየደወሉ ~ እኔ ይላሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ "እኔ እጄን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላስገባ አላስገባ ማን ምንስ ሲያገባው ነው ?
ደግሞም'ኮ አስቀድሜ ተናግሬያለው ~ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አልገባም አላልኩም ~ ይህን የሰላም ጉዞ እውን ለማድረግ ስራ እንጂ ጸሎት ዋጋ የለውም ~ ቆራጥነት እንጂ ማባበል - መወላወል የትም አያደርስም ~ በዚች በምንኖርባት ፕላኔት ፡ ወያኔን ለማጥፋት አብይን አገዝክ ብሎ እኔን ሊጠይቀኝ የሚችል ሰብእና ያለው ማንም ሰው የለም ~ እኔና ዓለም በሚገባ እንተዋወቃለን ~ ሶስት ሩብ እድሚዬን የጨረስኩት የአለምን ቅጥፈት ሳጋልጥ ነው ~ አንተ ልጅ ነህ ~ ተለማማጅ ፖለቲከኛ ~ ከአሜሪካው ነጩ-ቤት እስከ ክሬምሊን - የሌኒን ግራንዱ ህንጻ ፣ ከፖላንዱ ዋርሶው እስከ ብራሰልሱ ኔቶው ፣ ከአፍሪካው/OAU-AU/ እስከ የጂቡቲው ኢጋድ ስብስብ ፣ ከየመኑ ትሪዮ የመሰሪ መሪዎች ስምምነት/Sanaa Trio Agreement - Yemen,Sudan & Ethiopia/ እስከ ያንተው የኦስሎው የኖቤል ሽልማት ድረስ አንገቴን ሊያስደፉኝ ሞክረው ፥ ምንም አልተሳካላቸውም...
አሁን ይህን እንርሳና ፡ አንተ ካልክ ቢያንስ ኦፕሬሽኑን እስክንጨርስ ድረስ ጉዳዩን በሚስጥር ልይዝልህ እችላለው ~ እጅህን አስገብተሃል ሲሉኝ ሽምጥጥ አረጋለው ~ ልብ በል እኔ ላንተ ስል ነው እንጂ ፡ እኔ ቃሌ አንድ ናት ~ ከግዜ ጋር የሚቀያየር ፖለቲካ የለኝም ~ አሁን ግን ቢያንስ ዝም እላለው ~ የዝምታ ፖለቲካዬ የስንቱን ሆድ ይቆርጣል ~ እንደው ያንተ ነገር ፡ በትንሽ የጥንቃቄ ጉድለት ያንተው ጁንታ እጅ በገቡ ሮኬቶች ቤትህን ደፍረው ይህው ደጄን እየደፈሩ ነው ~ ግን ለዚህም መልሴ ዝም - ጭጭ ነው ~ ወንድ ልጅ እየፎከረ ስራ አይሰራም ~ ናጊ ቲቦር
/Nagy Tibor/ አመሰገነ - ኮነነ አሁንም ጉዳዬ አይደለም ~ አንድ ነገር ግን ላሳስብህ እወዳለው ፡ አንተ ይበልጥ ከፈት ያለ ፖለቲካ/More Liberal Politics/የምትከተል ሰው ስለሆንክ ፡ ጋዜጠኛ ካላስገባንና ፣ እኛ ገብተን ካልፈተፈትን የሚሉህን ሁሉ ~ ምላሽህ ኖ…! ነው መሆን ያለበት ~ ይህን የያዝነውን ጉዳይ የልጅ ጨዋታ እንዳታረገው ~ ነግሬሃለው እኔ የተዝረከረከ ነገር አልወድም ~ ይህን ጁ.ን.ታ.. ነው ያልከው ባንተ አጠራር ?
እኔ እንኳን ቀደም ብዬ ጃንዳ ብዬዋለው ~ የማይረባ የዝንጀሮ ስብስብ ማለት ነው ~ ጭፍራም እጨምርለታለው ~ አሁን ስሙ አያጣላንም ፡ ጁንታም ይባል ጃንዳ ብቻ ይህን የአፍሪካ ቀንድ ነቀርሳን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወደ ጀሃነም እንወርውረውና ህልመኞቹን አሸቃዮቹም ተስፋቸውን ቆርጠው ይቀመጡ ~ ፋታ የለም የ72 ሰአት ፡ የ24 ሰአት እያልክ ግዜያችንን አታባክን ~ ፋታ የለም ~ ወቅቱ የመሀር ነው ~ አዝመራን በግዜ ካልሰበሰብን ፡ ምርታችንን ተባይ ይበላብናል ~
ዳይ...ሂድ መቀሌ ግባ !
የሽምቁን ውግያ ለኛ ለሽምቅ ውግያ ፈጣሪዎቹ ተውልን…" የሚለው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉትጎታ ፡ ሰባተኛውን ንጉስ ጠቅላይ ሚኒስተሩን አጀግኖ ፡ ማማ ላይ አሰቅሏቸዋል።
በዛም ይሁን በዚህ እንግዴ ፡ ግዜ ደጉ ይህ ወጣት ጠቅላይ ምንስቴር ፡ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ሰብእናን ለማንበብ የጓደኞቹን የነ ዶር ብርሃኑ ነጋ ይሁን አንዳርጋቸው ጽጌን ፣ ዳውድ ኢብሳ ወይ ገመቹ ገለታን በር አንኳኩቶም ሆነ በርግዶ ፣ ወይ ባለው ፈጣን የቋንቋ ክህሎት የፕሬዝዳንቱን የቪዲዮ አርካይቮችን ቀምሎና ፈትሾ ፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን የልብ ወዳጅ አርጓቸው አርፎታል ~ ደጺ/ዶር ደብረጺዮን/የዛሬን አያርገውና የአዋሳው ስብሰባ ላይ " እኛ የማንደፍራቸውን ሰውዬ ወዳስመራ ቦሮ ቦሮ…ኢሱ እያለ…" ያለበትን አጋጣሚ ስናስብ ፡ እውነትም ደጺ አብይ ፡ ከኢሳያስ ጋር እንዲህ ከገጠመ የወያኔ ነገር እንደሚያከትም ልቡ ከወዲሁ ነግሮት ነበር ያስብላል.