Page 1 of 1

በማይካድራ ተጨማሪ 72 ሰዎች ጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኙ!

Posted: 27 Nov 2020, 14:03
by Ejersa
በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው ተገኝተዋል። በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል። አሁንም ሴንትራል፣ ደሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ እንደሚጨምር የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸውልናል። በዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ናቸው የሚባሉት ተጠርጣሪዎች በብዛት ሱዳን ሐሻባ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።