Page 1 of 1

አረመኔው የትግራይ ፋሽሽት እስረኞች ሳይቀር "ሳይናይድ በተባለ" መርዝ ሁሉ ሳይቀረ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደሚገድል ታውቃላችሁ?

Posted: 24 Nov 2020, 16:24
by Wedi
አረመኔው የትግራይ ፋሽሽት እስረኞች ሳይቀር "ሳይናይድ በተባለ" መርዝ ሁሉ ሳይቀረ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደሚገድል ታውቃላችሁ?

ትህነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አርዮስ እና አረመኔ የሆነ ድርጅት መሆኑን ማያሳያ
"በ1975 ላይ ከየት ቦታ እንደተማረኩ ባላውቅም ከሰባ በላይ ምርከኞች ነበሩ፡፡ ለመግደል ተፈለገ፡፡ "ሳይናይድ" የሚባል መርዝ አለ፣ ከቀመስከው ትሞታለህ፡፡ ውሻ ሲያብድ እሱን በስጋ ብትጠው ይሞታል፡፡ መለስ ዜናዊ ራሱ ለሕክምናው የቴክኒክ ክፍል ሃላፊ ለነበረው ለአባዲ መስፍን መርዙን እንዲልክለት መምርያ አስተላለፈ፡፡ የእስር ቤት ሃላፊው ብስራት አማረ ሂዶ ሳይናይዱን ማለት መድሃኒቱን ይዞ መጣ፡፡ የቴትራሳይክሊን ዱቄት ካፕሱል እየከፈቱ በውጡ የነበረው መድሃኒት እያራገፉ በሳይናይድ መርዝ ሞሉና እንደነበር አደረጉት፡፡ ሁሉን ነገር ካስተካከሉ በኋላ በዚያ አካባቢ ሚንጃይተስ በሽታ ስለገባ እንዳትታመሙ ይህን መድሃኒት ዋጡ ብለው ሰጡአቸው፡፡ የሚጠጡት ውሃ ከሚቀመጥበት እንስራ ውስጥ ሁሉም መድሃኒቱን ጨመሩበት፡፡ መድሃኒቱን እንደውጡ ሁሉም ረገፉ (ሞቱ)፡፡"

"የወያኔው ታሪክ በቀድሞ አባላቱ ሲገለጥ" በሚል ርዕስ በ1982 ዓም በአቶ ገብረመድህን አርያ እና አቶ አብርሃም ያየሄ ከተፃፈው መፅሃፍ ገጽ 71 የተወሰደ፡፡