Page 1 of 1

ከባሕር ዳር ከተማ ለመቀሌ ከተማ የተጻፈ ደብዳቤ!!

Posted: 24 Nov 2020, 07:29
by Wedi
:lol: :lol: :lol:
ባሕር ዳር ለመቀሌ የጻፈችው ደብዳቤ
(አሳዬ ደርቤ)
.
"ውዷ እኅቴ እንዴት ሰንብተሻል? እኔ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በእሳት ፈንታ በሮኬት የተጠበሰ በቆሎ ከመብላቴ ውጭ ደህና ነኝ፡፡
ይሄን ብዬ ወደ ዋናው ሐሳቤ ስገባ እኔ እምልሽ መቀሌዋ ያ ‹‹ደብረ ጽዮን›› የሚባል ጥምልምል መሪሽ ያንጠለጠልኩት ብልት ምነው ሮኬት ነው አለ?
ዐቦይ ስብሐት የሚባል ቅንዝራም ሰውዬ በሮኬት ጥይት አንቴናዬን መምታት ምነው አማረው? 😁
ጌታቸው ረዳ የሚባል ሰካራምስ ‹‹የዘንድሮ ሃንጎቨሬ ሮኬት በማስወንጨፍ እንጂ ሽሮ ፍትፍት በመብላት የሚበርድ አይደለም›› ማለቱ ስለምን ነው?
➖
ውዷ እኅቴ፡- ከሰላምታው በላይ ወቀሳውን ያበዛሁብሽ ገዥዎችሽ የተኮሱብኝ ሮኬት ስላበሳጨኝ እንጂ ስለጎዳኝ እንዳይመስልሽ! ምክንያቱም ሮኬቶቹ የተተኮሱት ሕንጻዬን ለመደርመስ፣ አየር ማረፊያዬን ለማረስና የልጆቼን ደም ለማፍሰስ ቢሆንም በእግዜር ጥበቃ በቆሎ ከመጥበስና ልጅ ከመቀስቀስ ያለፈ ጉዳት አላደረሱም፡፡
ያም ሆኖ ግን፣ የፌደራል መንግሥቱ መቀመጫ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ እኔ ቂጥ የተዛወረ ይመስል ባንዳዎችሽ ለመቀመጫዬ ያላቸውን ጉጉት በሮኬት አማካኝነት ሊገልጹልኝ መሞከራቸው ትክን አድርጎኛል፡፡ ለስኳር ፋብሪካ በተመደበለት በጀት የስኳር በሽታ የሸመተ ያ ‹‹አባይ ጸሐዬ›› የሚባል ሌባ ኢንሱሊኑን አርፎ እንደመወጋት በሚሳይል እኔን ለመውጋት መነሳሳቱ አበሳጭቶኛል፡፡
➖
ሲቀጥል ደግሞ መቀሌዋ፡- አንቺም ብትሆኝ በእኔ በእኅትሽ ላይ አላስፈላጊ ጥቃት ሲፈጸም ዝም ማለትሽ አስገርሞኛል፡፡
ቆይ እኔ እምልሽ ውዷ እኅቴ ስለ እኔ ስታስቢ ቅናት ቢጤ ይሰማሻል እንዴ?
የምር እንደዚያ ካሰብሽ ትክክል አይደለሽም! ምክንያቱም ከእኔ በሚሰረቅ ሐብት በፎቅና በወርቅ ስትንቆጠቆጪ የኖርሺው አንቺ እኮ ነሽ! ማኛ ጤፉ የሚመረተው እኔ ጋር ቢሆንም እንጀራው ግን ሲነጎትና ሲበላ የኖረው አንቺ ጋር ነው፡፡
‹‹አይጫንም እንጂ- ውሃ በመኪና፤
መቀሌ ነበረ- ይሄን ጊዜ ጣና›› እስኪባል ድረስ ከእኔ ወዳንቺ የሄደ እንጂ ከአንቺ ወደ እኔ የመጣ ምንም ነገር የለም፡፡
ስለዚህ በቅናት መንጨርጨርም ሆነ ሮኬት መወርወር የነበረብኝ እኔ ብሆንም በበኩሌ ግን ጸሎት ከማድረግ ባለፈ መጥፎ ነገር አስቤብሽ አላውቅም፡፡
ተፈጥሮም ብትሆን ለእኔ ዓባይ ወንዝን ስትሰጥ፣ ለአንቺም ዓባይ ጸሐዬን አልነፈገችሽም፡፡ በአንዳንድ የተፈጥሮ ጸጋዎች ብበልጥሽ እንኳን በሰው ሰራሽ ጸጋዎችና በተፈጥሮ ጸሮች አልደርስብሽም፡፡
ስለዚህ ውዷ እኀቴ፣ እንደ ጀግና የምትቆጥሪያቸውን ባንዳ ገዥዎችሽን እኔ የዓባይ ማደሪያ እንጂ የዶክተር ዐቢይ ማደሪያ አለመሆኔን አስታውሰሽ ‹‹በሌሊት ሮኬት እየተኮሳችሁ እኅቴን እንቅልፍ አትንሷት›› ብትያቸው ጥሩ ነው፡፡ ነፍጠኞቹም የተቆጣጠሩት አድዋ ተራራን እንጂ ጣና ሐይቅን ስላልሆነ አፈሙዛቸውን ወደዚያ ያዞሩ ዘንድ ብትመክሪያቸው ጥሩ ነው፡፡
➖
በተረፈ መቀሌዋ ከወላጅ እናትሽ ኢትዮጵያም ሆነ ከእኔ እኅትሽ ድርጅትሽን ማስቀደምሽ ልክ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ድርጅትና ሥርዓት አላፊ ሲሆኑ የእኛ እኅታማችነት ግን ቀጣይ ስለሆነ ዝምድናችን መበላሸት የለበትም፡፡
በመሆኑም ጉያሽ ውስጥ የደበቅሻቸው ከሃዲዎች ለባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የገነቡትን አፍርሰው፣ የተወለደውን አጥፍተው በፍርስራሽ ሳይሞሉሽ በፊት በተሰጠሽ 72 ሰዓት ውስጥ ከጭንሽ መንግለሽ ትወረውሪያቸው ዘንድ በማሳሰብ ደብዳቤዬን እቋጫለሁ፡፡"
ያንቺው እኅት ባሕር-ዳር
#Share
ከአሳየ ደርቤ