Page 1 of 1

ሰበር መረጃ፦ በጁንታው መሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፀመ!

Posted: 19 Nov 2020, 16:24
by Ejersa
ማምሻውን በመቀሌ ከተማ ላይ የተመረጡ የባለሥልጣናት ተሽከርካሪዎች ላይ ያነጣጠረ የድሮን የአየረ ጥቃት ተፈፅሞ:: ማምሻውን በተደረገው ጥቃት 3 መኪኖች ወድመዋል፡፡ በመኪኖቹ ውስጥ ባለስልጣኖቹ ይኑር አኑር የታወቀ ነገር የለም:: በዚህ ጉዳይ የጁንታው ቡድን እስካሁን ምንም ያለው ነገር የለም:: ትህነግ በአላማጣ አካባቢ ተቆራርጠው የቀረው ሚሊሻዎቿና የጁንታው ልዩ ሀይል በመከላከያ ሠራዊት እና አማራ ልዩ ሃይል አማካኝነት በቆረጣ ተከበው ከቆዩ በኃላ 120 የሚሆኑ ሚሊሻና የትህነግ ልዩ ሀይል በርሀብና በጥማት ተሰቃይተው ለመከላክያ ሰራዊት ያለምንም ተኩስ ማምሻው ከነመሳሪያቸው እጅ ሰተዋል::