Page 1 of 1

ህወሓት ጨርሶ መወገድ ያለበት ሽብርተኛ ጁንታ ነው!!!!

Posted: 19 Nov 2020, 14:09
by Ejersa
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦንብ እና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የጦር መሳሪያ አከማችተው በሚገኙ ተቋማት ላይ የሚደረጉ ፍተሻዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ለከተማችን አዲስ አበባ የጥፋት ሃይሎች የደገሱላትን ሽብርና እልቂት ለመቀልበስ የሚከናወነው ጠንካራ ህግን የማስከበር ተግባር በህብረተሰቡ የዕለት -ተዕለት መረጃ ሰጪነት እየታገዘ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀው፡፡

ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦንብ ፣55 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 21 ሽጉጦች ፣ 2 ኤስ ኬ ኤስ ጠመንጃ ፣3 ቺኮዝ፣ 1ብሬን ፣6 ቺቺ ጠመንጃ፣ እና ሌሎች ጠመንጃዎች በአጠቃላይ 113 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል ፡፡ በተጨማሪም 309 የሽጉጥ እና 4829 ዓይነታቸው የተለያየ ጥይቶች ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ትራኮን ሪልስቴት አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 64ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር መያዙን እና ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ከሃዲው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ በከተማችን አዲስ አበባ የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች ሽብር እና ሁከት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ከበርካታ የጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ኮሚሽኑ ከህዳር 3 ቀን 2013 ዓ/ም በፊት በተሰሩ ስራዎች 744 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና 4628 ልዩ ልዩ ጥይቶች ስለመያዛቸው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ከሰጠ በኋላም ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተከናወነ ተግባር ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተያዘውን ጨምሮ ከህዳር 3 ቀን ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተሰሩ ስራዎች 37 የእጅ ቦንብ፣ 1ብሬን፣ 5የጦር ሜዳ መነፅር፣18 የሬዲዮ መገናኛ ቁሳቁሶች፣589 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣350 ሽጉጦች፣46 የተለያዩ ጠመንጃዎች በአጠቃላይ 1023 የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ከ10ሺህ 404 መሰል ጥይቶች ጋር በብርበራ እና በፍተሻ ተይዘዋል፡፡ 738 የተለያዩ የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳት በፍተሻው ወቅት መገኘታቸውንም የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሷል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ተጥለው የተገኙ 7 የእጅ ቦንብ፣5 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣1 ተቀጣጣይ ፈንጂ፣ 3 ሽጉጥ፣ 2የተለያዩ ጠመንጃዎች ከመሰል 841 ጥይቶቻቸው ጋር በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዘዋል፡፡

በሀገሩ ጉዳይ ድርድር የማያውቀው ህዝባችን አንድ መሆኑ ያሥጨነቃቸው የጥፋት ሃይሎች በየጥጋ-ጥጉ እየጣሉት ከሚገኘው የጦር መሳሪያ ባሻገር በጥርጣሬ ውስጥ ከገቡ ተቋማትና ግለሰቦች በፍተሻና በብርበራ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና የጦር ሜዳ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን የገለፀው ኮሚሽኑ የህብረተሰቡን ድጋፍና ጥቆማ በመጠቀም የጦር መሳሪያ ያከማቻሉ ተብለው በሚጠረጠሩ ተቋማት ላይ የሚያደርገውን ክትትል እና ፍተሻ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡