Page 1 of 1

"ጦርነት ለአማራ ሰርጉ ነዉ" መለስ ዜናዊ

Posted: 14 Nov 2020, 17:16
by Wedi
"ጦርነት ለአማራ ሰርጉ ነዉ" መለስ ዜናዊ

✍️ ዶ/ር አብርሃም አማረ (በፈቃደኝነት ወደ ጦር ግ ንባር በመሄድ ለታጋዮች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ያለ ስፔሻሊስ)

ከወልቃይት

መለስ ዜናዊ "ጦርነት ለአማራ ሰርጉ ነዉ" አለ የተባለውን ነገር ያመንኩት ሰሞኑን ነዉ !!!

ምን ሆነ መሰላችሁ ፡ የህዝብ ማመላለሻ የመኪና እንቅስቃሴ ከአብራጅራ ወደ ሁመራ እስከዚህም ነዉ ፡ የለም በሚለዉ ብንይዘዉ ይቀላል ። ይህንን ችግር ታዲያ ተቋቁመው የይለፍ ማህተም ብቻ አድርገዉ ከ150 ኪሜ በላይ እየተጓዙ እድል ሲቀናቸዉም በትራክተር መኪኖች ትንሽ መንገድ እየተሸኙ ወገኖቻቸውን በጦር ሜዳ ለማገዝ የሚሄዱ አያሌ ወገኖቻችንን ስታይ ፤ ከዉስጣቸዉ የሚነበበውን ደስታ ስታይ ሰርግ ቤት የሚሄዱ እንጅ ወደ ሞት በሮች የሚሄዱ አይመስሉም። በፍጥነት እየበረረ የነበረውን መኪናችንን እጆቻቸውን ዘርግተው እባካችሁን ዉሰዱን ሲሉ ጠየቁን ፤ ሁመራ እንደሚሄዱ ነግረዉን ተሳፈሩ ። የሚያወሩት ሁሉ ይጣፍጣል ። አርሶ አደር ናቸው ፤ ማስተዋልን እዉቀትን የሀገር ፍቅርን እስካፍንጫው ተከናንበዋታል። ለሰላሳ አመት ያረፈባቸው የትህነግ በትር ልባቸውን አድንድኖታል ፤ ሞቶ ያልቀበሩት ወገናቸው ጠፍቶ ያላገኙት ልጃቸው ሆዳቸውን እያላወሰዉ ከንግግራቸው እና ኮስተር ፈታ ከሚለው ግንባራቸው ጎልቶ ይነበባል ። በጨዋታ መሃል እንጠይቃቸዋለን እነሱም በፍቅር እና በጀግንነት ይመልሳሉ ... እኛ ከየት እንደመጣን እና ለምን እንደመጣን ስንነግራቸው አቅፈዉ መሳም ነዉ የቀራቸው !!

ከአዉደ ዉጊያዉ እየዋሉ ምሽት ከተማ መጥተው አድረው ንጋት ላይ እንደሚሄዱ አወጉን። ይሄንን ለብዙ ቀን ያደርጉታል ፤ እኛም በጣም ተገረምን !! ይባስኑ ይሄን ትንሽ እንግፋ እና ቶሎ ተመልሰን ወደ ዳንሻ እና ወደ ራያ እንሂድ ብለው ሀሳብ አቀረቡ እና ትንሽ ከተወያዩበት በኋላ ወደ ራያ ቶሎ እንደሚመለሱ ወሰኑ ። የምሰማውን ሁሉ እንደፊልም እንጂ እንደእውነት ገሀድ አለም ላይ ያለ ሁሉ አይመስለኝም ነበር ። ግን አጠገቤ ሁነዉ በአይኔ እያየኋቸዉ ነዉ። በሁመራ በኩል ያለዉን ቶሎ ደምስሰዉ ለራያዉ ወገናቸው ለመድረስ ተቻኩለዉ ሳይ እዉነትም "ጦርነት ለአማራ ሰርጉ ነዉ" የሚለው ሀረግ ይገልዉ እንደሆን እንጂ ሌላ ቃል አጣሁለት!!

ቸር ይመልሳችሁ ወገኖቼ!!🙏🙏

Please wait, video is loading...