Page 1 of 1

መንግስት የትግራይ ልዩ ኃይልን ቀሚስ ከመልበስ ይታደገው!

Posted: 09 Nov 2020, 21:27
by Ejersa
የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት አብዛኛው ወልቃይት ጠገዴና ራያ ላይ ከዕዛቸው ተቋርጠዋል። ብዙዎቹ መሳርያ በልብስ ቀይረው እየሸሹ ነው። የወንድ ልብስ ያጡት ቀሚስ እየለበሱ ለመሸሸት እየሞከሩ ነው። ከዕዝ በመቋረጣቸው በርሃብ እየተጎዱ ነው።

ወልቃይት ጠገዴ ላይ መብራት ጠፍቷል። መብራት ቢኖርና የልዩ ኃይል አባላቱ በየሚሸሹበት ቲቪ ማየታቸው አይቀርም። ቢያንስ በክላሽ ቀሚስ የሚቆይሯቸው ይነግሯቸዋል። በመሆኑም መብራት እንዲኖር አድርጎ በቴሌቪዥን በየመሃሉ ጥሪ ያቅርብላቸው። በራያና ወልቃይት ጠገዴ ብቻ ሳይሆን በትግራይም ያሉት የልዩ ኃይል አባላት ቀሚስ ከመልበስ ይታደጋቸው። በየሚዲያው በዜና እና ፕሮግራሞቹ መሃል ጥሪ ይቅረብላቸው!