በዛሬው እለት ሁለት ዲጅታል ወያኔዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ!
Posted: 07 Nov 2020, 15:36
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ፥ በድብቅ << Yeha Press >> በሚል ገፅ የህወሓትን የፕሮፓጋንዳ ክንፍ ሲመሩ የነበሩ ሁለት ጋዜጠኞችና አንድ ሌላ ግብረ-አበራቸው ፥ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እነዚህ ሓፍቱ ገ/እግዚያብሔርና ፀጋዬ የተባሉት በከፍተኛ ሪፖርተርነት ደረጃ ሲሰሩ የነበሩት ጋዜጠኞች ፤ ከጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ውጭ በሆነ መልኩ የትህነግን የጥፋት አጀንዳ በበላይነት ሲመሩ እንደነበርም ከምንጮቼ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል፡፡

