አሸባሪው ህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት ፈረሰ!!
Posted: 07 Nov 2020, 05:44

አሸባሪው ህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት ፈረሰ!!
በትህነግ ሲመራ የነበረው የትግራይ ክልል መንግስት ፈረሰ‼
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስትን በይፋ አፍርሶ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ያቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል።
1. አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤
2. የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤
3. ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል፤
4. አግባብ ባለው ህግ መሰረት በክልሉ ምርጫ የሚከናወንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
5.የክልሉን እቅድና በጀት ያፀድቃል፤
6. በፌዴራል መንግስቱ የሚሰጡ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ሲል ምክር ቤቱ አጽድቋል።