የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ):ህወሓት ሀገራዊ መግባባት የሚፈጥሩ እድሎችን በሙሉ ዘግቶ የጦርነት አማራጭ መተጠቀሙ ትልቅ ጥፋት ነው
Posted: 06 Nov 2020, 20:03
አቶ ቀጄላ መርዳሳ: ህወሓት በድፍረት የጀመረው ጦርነት ለየትኛውም ወገን አይጠቅምም ።ህወሓት የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንደራሱ ወገን ከመመልከት ይልቅ እንደጠላት ተመልክቶ ጥቃት መሰንዘሩ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ነው። በጦርነቱ የትኛውም አካል ቢያጠቃ ሀገሪቱ የምታተርፈው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ብቻ ነው”ብለዋል ።
ህወሓት ከሁለት ዓመት በፊት በሀገሪቱ መንግሥት ውስጥ የነበረው ሚና እየቀነሰ ሲመጣ ያጣውን ስልጣን ለማግኘት ሲል የቀየሰው ስትራቴጂ እንደሆነ አመልክተው፣ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት ግጭቶች የህወሓት ድጋፍ ያላቸው እንደሆኑ የሚመላክቱ ነገሮች አሉ ብለዋል ።
መንግሥት ጦርነቱን በአጭር ጊዜ በበላይነት በማጠናቀቅ የችግሮች ምንጭ ስለሚወገዱ በየጊዜው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ግጭቶች ይቀንሳሉ፤ የውጭ ጥቃትን ለመመከት የሚያስችል አቋምም ሊጠናከር እንደሚችል ጠቁመዋል። ህዝቡ በጦርነቱ ሳይሸበር በተረጋጋ መንፈስ አካባቢውን እየተቆጣጠረ የተለመደ ሥራውን መስራት እንደሚገባውም መልዕክት አስተላልፈዋል
https://mereja.com/amharic/v2/389477