Page 1 of 1
Re: IS ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA202? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው የሰርብ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን?Informative art
Posted: 04 Nov 2020, 20:31
by free-tembien
No, it’s more like woyane criminals heading to kaliti
Please wait, video is loading...
Re: ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA 202? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው የሰርብ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን?-INFORMATIVE ARTI
Posted: 04 Nov 2020, 20:32
by Fiyameta
yaballo, the defeated Weyane from Adwa,
When you wanted to pretend to be an Oromo you used the nickname yaballo, and when you wanted to pretend to be an Amhara you used the nickname Revelations. Do you know why your evil plans to create a conflict between the Oromo and Amhara people did not work?

Re: IS ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA202? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው የሰርብ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን?Informative art
Posted: 04 Nov 2020, 20:47
by TGAA
Yabello you have been singing this doom and gloom for some time. Weyanes convinced you with their bravado that the tribalist states of Ethiopia is at hand. It was obvious then and it is obvious now that arrogance comes before a fall, and all along your hopes was pinned that Weyanes would bring about the Yogoslavization of Ethiopia. Booooooooom . At the end of this week, you have to go back to the drowing board and revise your ambiclie understanding of what Ethiopianness means. Ethiopia the one that is United while cherishing their difference is here to stay. All your naive dream of dismantling Ethiopia is falling off the wall one by one :
Re: IS ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA 102? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው የሰርብ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን? INFORMATIVE P
Posted: 04 Nov 2020, 20:50
by Abdisa
Please ignore the Woyane yaballo. He's having a bad day watching his Woyane bosses being arrested by Ethiopian forces.
Re: IS ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA 102? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው የሰርብ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን? INFORMATIVE P
Posted: 04 Nov 2020, 22:07
by TGAA
Projection is a psychological defense mechanism in which an individual attributes unwanted thoughts, feelings and motives and inadequacies onto another person. where robust manhood exists a washala talk is beneath one. That aside, your analogy of unrelated issues as if they are one and the same shows your showmanship and dishonesty. Yugoslavia and Ethiopia not the same. Ethiopian nationalism has never been the kind that comes to dominate with brute force. That is why it has more defender of it from the periphery than in the center. That is why the periphery doesn't react resolutely against Ethiopiansm even when agitated , and its why the center holds.
Re: IS ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA 102? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው የሰርብ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን? INFORMATIVE P
Posted: 04 Nov 2020, 22:16
by AbebeB
yaballo wrote: ↑04 Nov 2020, 20:24
IS ETHIOPIA HEADED FOR YUGOSLAVIA 102? አሃዳዊቷን ዩጎዝላቪያ አልሞ ሰባት ሉኡላዊ መንግስታትን ካዋለደው እና በሶሎቦዳን ሚሎሰቪች የተመራው አክራሪ የሰርብ አሃዳዊ እንቅስቃሴ ምን እንማራለን? - AN INFORMATIVE & EDUCATIONAL ARTICLE.
***********
በበላይነት ስሜት የተሞላው የሰርብ ብሄርተኝነት እየጎላ መምጣት የሌሎቹን ሪፑብሊኮች ህዝቦች በበኩላቸው ማንነታቸውን ጠበቅ አድርገው እንዲይዙ አነሳሳ። ክስተቱም የሌሎች ሪፑብሊኮች ህዝቦች በአካባቢያቸው የሚኖሩ ሰርቦችን ድርጊት በጥርጣሬ እና በስጋት መከታተል እንዲጀምሩ ስለገፋፋ ከሰርብ ሪፑብሊክ ውጪ የሚኖሩ የሰርብ ማህበረሰብ አባላትን ምቾት ያሳጣ ጀመር።
የእስሎቦዳን ሚሎሶቪችና [Slobodan Milosevic] ተከታዮቻቸው ሰርቦች በዩግክዝላቪያ ውስጥ የነበራቸዉን ስፍራ እንዲሸረሸር ምክንያት የሆነው የ 1974 ቱ ህገ መንግስት ነው የሚል ጽኑ እምነት ስላላቸው የሕጉን ዋነኛ ውጤት የሆነዉን ራስን በራስ ማስተዳደርን ለመቀልበስ የሚቻላቸውን ሁሉ ማድርግ እንዳለባቸው ወስነው እንቅስቃሴ ጀመሩ: : ትልማቸዉንም ለማሳካት፥ .. 1ኛ) በቅድሚያ በሰርብ ልሂቃን ቁጥጥር ስር የነበረዉን የዩጎዝላቪያን ሚድያ ተጠቅመው የተቀናበረ ዘመቻ በመክፈት የ1974 ቱን [federalist] ህገ መንግስት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ መስራት ጀመሩ። በተቀናጀ ዘመቻም የ 1974 ቱ ሕገ መንግስት ዩጎዝላቪዊነትን እና ብሔራዊ ስሜትን የሸረሸረ መሆኑን በስፋት በማስወራት ወደ አንድነት ለመምጣት ይቻል ዘንድ ህገ መንግስቱ ሊሻር ይገባዋል የሚል ፕሮፖጋንዳ ማሰራጨት ተያያዙ :
ከአቡ ኢምራን:
<<በ 1918 የኦቶማን ቱርክ ኢምፓየር ሲፍረከረክ ከአገሪቱ ሕዝብ አብላጫውን ቁጥር የነበራቸው ( 36.3%) ሰርቦች ተፅዕኖ ጎላ ብሎ የሚታይበት የዩጎዝላቪያ ንጉሳዊ አገዛዝ ተመሰረተ:: ሰርቦች ተፅዕኖአቸውን ለማስቀጠል ጠንካራ የተማከለ (አሃዳዊ) ሥርዓት እንዲኖር ግፊት ሲያደርጉ የተቀሩት የማህበርሰብ አባላት ግን በተቃራኒው ራሳቸዉን ለማስተዳደር የሚያስችላቸውን ሥርዓት ጠየቁ :: የተመሰረተው የዘውድ አገዛዝ የተለያዩ ማንነቶች ያሉዋቸውን ህዝቦች ተፎካካሪ ፍላጎቶች ለማስተናገድ ዝግጁ ስላልነበር አገሪቱ ከጅምሩ ያልተረጋጋች ሆነች ::
.
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በምዕራቡ አጋር ኃይሎችና በቀድሞዋ ሶቬት ህብረት ድጋፍ አሸናፊ ሆኖ የወጣው የጆሲፕ ብሮዝ ቲቶ ቡድን በወቅቱ የነበረውን የንግስና ሥርዓት በማስወገድ ስድስት ሪፑብልኮች (የቦስንያ ኸርዘጎቪና ፣ ክሮአት ፣ ሰርብ ፣ ማሴዶንያ ፣ ሞንቴኔግሮ እና የስሎቬንያ ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ) እና ሁለት በሰርብ ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ውስጥ የታቀፉ የራስ ገዝ ክልሎች (ቮጅቮዲና እና ኮሶቮ )ያላት ፈደራላዊት ሶሻሊስት ዩጎዝላቪያን መሰረተ::
.
በሶሻሊስት መርሆ ላይ የተመሰረተው ፈደራላዊ አስተዳደር የይስሙላ ስለነበር ወደ ተማከለ ስርአት ያደላ ነበር። ሶሻሊስታዊዉ የፌደራል ስርዓት የተማከለ አሰራር መከተል ቀደም ሲል በንጉሳዊቷ ዩጎዝላቪያ በነበራቸው ተፅዕኖ dominant ስፍራ ምክንያት በሁሉም ክልሎች ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ የሰርብ ልሂቃን የተመቸ ነበር :: ነገር ግን የፌደራል መርህ በትክክል ያለመተግበር የሌሎችን
ብሄር ብሄረሰቦች ተስፋና ፍላጎት ለማሳካት ስላልቻለ ከግዜ ቡሃላ ተግዳሮቶች ተደቀኑበት::
.
የቲቶ መንግስት አገሪቱን የተጋፈጣትን ችግር ለመፍታት የተዘረጋውን የይስሙላ ፈደራሊዝም ወደ እውነተኛ የፌደራል አስተዳደር ማሸጋገር ግድ መሆኑን ተገነዘበ :: አዲሱንም ሥርዓት በሕግ መሰረት ላይ ለማቆም በማለም በ 1974 ለስድስቱ ሪፑብልኮች እና በሰርብ ሪፐብሊክ ስር ታቅፈው ለነበሩት ሁለት ልዩ ክልሎች የራስን በራስ ማስተዳደር መብት ያጎናፀፈ ህገ መንግስት አጸደቀ ።
.
ሕገ መንግስቱም በሰርብ ሪፑብሊክ ውስጥ የተካተቱት ቮጅቮዲን እና ኮሶቮ በፓርላማ ድምፅ እንዲኖራቸው ስላደረገ የሰርብ ሪፑብሊክ በሁለቱ ክልሎች ላይ የነበራት ተጽዕኖ እጅጉን ቀነሰ:: ክስተቱም ብሄርተኛ ሰርቦችን ክፉኛ ስላስቆጣ የክልሉን ነዋሪዎች መተንኮስና ማጥቃት ጀመሩ ።
.
ራስን በራስ የማስተዳደር ስርዓትም ሶቬት ህብረት እስከተፈረካከሰችበት 1990 ድረስ ደረጃ በደረጃ ስር እየሰደደ ሄደ :: የሕጉ መተግበር በየሪፑብሊኮቹ በትምህርት ፣ በፖለቲካ ፣ በአስተደደር ፣ በንግድ ወዘተ ዘርፎች ተፎካካሪ የሆኑ ልበሙሉ (assertive)
ልሂቃን በብዛት እንዲፈልቁ አስቻለ።
.
ክስተቱም የሰርብ ልሂቃን በዩጎዝላቪያ ውስጥ የነበራቸው ተፅዕኖ እንዲሸረሸር አደረገ::ከወገኖቻቸው ጋር በእኩልነት መኖርን እንደ መበለጥ የተመለከቱ በርካታ የሰርብ ልሂቃን በበኩላቸው በዩጎዝላቪያ ዉስጥ የነበራቸውን ላቅ ያለ ጥቅምና ተጽእኖ ያሳጣቸው የየሪፑብልኮች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተሳደር መሆኑ በግልጽ ስለታየ ገናና የነበሩባትን ፣ የተማከለች እና አሃዳዊት ዩጎዝላቪያን የመመለስ እንቅስቃሴ ጀመሩ። አላማቸውንም ለማሳካት በሰርብ ሪፑብሊክም ሆነ በሌሎች ሪፐብሊኮች ውስጥ የሚኖሩ የሰርብ ብሄር አባላት አንድነቷ የተከበረ ታላቌን ዩጎዝላቪያ መልሶ ለማቌቌም እንዲንቀሳቀሱ ቅስቀሳ አጧጧፉ። በሌሎች ሪፑብሊኮች የሚኖሩ ሰርቦች የፈደራል ስርአትን አምርረዉ በማውገዝ አሃዳዊ ስርአትን ለመመለስ የሚደረገዉን እንቅስቃሴ ተቀላቀሉ።
.
በበላይነት ስሜት የተሞላው የሰርብ ብሄርተኝነት እየጎላ መምጣት የሌሎቹን ሪፑብሊኮች ህዝቦች በበኩላቸው ማንነታቸውን ጠበቅ አድርገው እንዲይዙ አነሳሳ። ክስተቱም የሌሎች ሪፑብሊኮች ህዝቦች በአካባቢያቸው የሚኖሩ ሰርቦችን ድርጊት በጥርጣሬ እና በስጋት መከታተል እንዲጀምሩ ስለገፋፋ ከሰርብ ሪፑብሊክ ውጪ የሚኖሩ የሰርብ ማህበረሰብ አባላትን ምቾት ያሳጣ ጀመር።
.
አክራሪ የሰርብ ብሄርተኖች በተለያዩ ሪፑብሊኮች ውስጥ የሚኖሩ ሰርቦችን ውጥረት ውስጥ መሆን በመጠቀም ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ እና መከታዎቻቸው ሆነው በመቅረብ በሰርብ ሪፑብልክ ዉስጥ ያላቸዉን ተቀባይነት እያጠናከሩ ሄዱ። በሰርቦች ቁጥጥር ስር የነበረዉን የዩጎዝላቪያን ሚዲያ በመጠቀም የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቶችን ማባባስ ተያያዙ።
.
ወቅቱ ዩጎዝላቪያ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የገባችበት ስለነበር ችግሩን ለመቅረፍ የመንግስት ዋነኛ ትኩረት የኢኮኖሚዉ ሁኔታ የሚሻሻልበት መንገድ ማፈላለግ ሆኖ እያለ የሰርብ ብሄርተኛ መሪዎች ትኩረት ግን በኢኮኖሚው ቀውስ ምክንያት በስራ አጥነት የተከፉ ሰርቦችን በበላይነት ስሜት በተሞላ ብሄርተኝነት በማንቀሳቀስ አላማቸዉን ማሳካት ስለነበር የሰርብ ሪፑብሊክ ኢኮኖሚ ክፉኛ አሽቆለቆለ።
.
የሌሎች ሪፑብሊኮች አመራሮችም ትኩረት ለኢኮኖሚያቸዉ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸው እንዳይነጠቁ መከላከል ላይ ስላደረጉ በመላው አገሪቱ ኢኮኖሚው አሽቆለቆለ ። አስከፊ እየሆነ የሄደው የኢኮኖሚ ሁኔታ በቀላሉ ግጭቶችን ለመቀስቀሰ እና አገር ለማተራመስ ለሚያስቡ ሃይሎች ምቹ ሁኔታ ፈጠረላቸው።
.
በዚህ መልክ በፌደራል ሥርዓት ስር ከወገኖቻቸው ጋር በእኩልነት መኖር ያልተመቻቸው አክራሪ ሰርቦች በአንድነት ስም የጥንቱን የሰርብ የበላይነት የሰፈነባት የተማከለ (አሃዳዊ ) አስተዳደር ያላት ዩጎዝላቭያን ለመመለስ ቆርጠው ተነሱ:: በዚህ ወቅት የእስሎቦዳን
ሚሎሶቪች ተጽዕኖ ጎልቶ መውጣት ጀመረ።
.
የእስሎቦዳን ሚሎሶቪች በፖለቲካው መድረክ ጎልተው መታየት መጀመር የሰርብ ብሄርተኝነት እጅግ ከሮ እንዲወጣ ያደረገ ክስተት ነበር :: የእስሎቦዳን ሚሎሶቪች ባህሪያቸው የተቀረፀው ባመኑባቸው በተቃርኖ የተሞሉ ትርክቶች እንደሆነ ይነገራል። ይሄውም እስሎቦዳን ሚሎሶቪች በጥንታዊቷ ገናና ሰርብ ትርክት በእብሪት የተሞሉ ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚዎች በክሩዋቶች ትብብር በሰርብ ላይ ባደረሱት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ቂም የቌጠሩ ፣ ከቲቶ የወንድማማችነት እና አንድነት የመሸንገያ መርህ አንድነትን ለፖለቲካ ሸፋን መገልገልን የተማሩ ፣ በኮሚኒስት ስርዓት ውስጥ ከቀናቸው ሰዎች ስለነበሩ ፀረ ዲሞክራሲ አቌም የተላበሱ ውስብስብ ግለሰብ ናቸው ይባላል።
.
የእስሎቦዳን ሚሎሶቪችና ተከታዮቻቸው ሰርቦች በዩግክዝላቪያ ውስጥ የነበራቸዉን ስፍራ እንዲሸረሸር ምክንያት የሆነው የ 1974 ቱ ህገ መንግስት ነው የሚል ጽኑ እምነት ስላላቸው የሕጉን ዋነኛ ውጤት የሆነዉን ራስን በራስ ማስተዳደርን ለመቀልበስ የሚቻላቸውን ሁሉ ማድርግ እንዳለባቸው ወስነው እንቅስቃሴ ጀመሩ: : ትልማቸዉንም ለማሳካት፥
.
1ኛ) በቅድሚያ በሰርብ ልሂቃን ቁጥጥር ስር የነበረዉን የዩጎዝላቪያን ሚድያ ተጠቅመው የተቀናበረ ዘመቻ በመክፈት የ 1974 ቱን ህገ መንግስት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ መስራት ጀመሩ። በተቀናጀ ዘመቻም የ 1974 ቱ ሕገ መንግስት ዩጎዝላቪዊነትን እና ብሔራዊ ስሜትን የሸረሸረ መሆኑን በስፋት በማስወራት ወደ አንድነት ለመምጣት ይቻል ዘንድ ህገ መንግስቱ ሊሻር ይገባዋል የሚል ፕሮፖጋንዳ ማሰራጨት ተያያዙ ::
.
ከዚያም በመቀጠል ለ 1974 ቱ ህገ መንግስት ግንባር ቀደም ተከላካይ የሆኑትን ክርዋቶችን ፣ እስሎቨኖችን ፣ ማሰዶኖዊያንን፣ የቦዝኒያን ሙስልሞች እና የኮሶቮ አልባኒያን ህዝቦች ማንነት በተቀናበረ ፕሮፖጋንዳ በማጠልሸትና በማሸማቀቅ ለህገ መንግስቱ ከመቆም እንዲያፈገፍጉ ሙከራ አደረጉ። በዚህ አላበቃም የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት እና ውንጀላዎችን በመደደር ማንነታቸዉን በማጠልሸት ከሌሎች የመነጠል ሥራ በስፋት ሰሩ ::
.
በተቃራኒዉ ደግሞ ሰርቦችን የዩጎዝላቪያ የጀርባ አጥንት ፣ መከታ ፣ ብቸኛ ተቆርቌሪ ወዘተ አድርገው በመሳል በንጉሳዊቷ ዩጎዝላቪያ የነበራቸዉን የበላይነት መልሰው የሚያገኙበትን የስነ ልቦና ሁኔታ ለማመቻቸት በስፋት ሰሩ።
.
2ኛ) የ 1974 ቱ ህገ መንግስት ስራ ላይ ከዋለበት ግዜ ጀምሮ ዩጎዝላቪያ ስድስቶቹ ሪፐብሊኮች እና ሁለቱ ልዩ ክልሎች (ወይም ዞኖች) በአቻነት በሚሣተፉበት የጋሪዮሽ አመራር እንድትተዳደር ስለተደረገች በጋሪዮሹ አመራር ዉስጥ ያለዉን የድምፅ ስሌት ለሰርብ ሪፐብሊክ በሚያመች መንገድ መዘወር (manipulate) የሚቻልበትን ሁኔታ በማዘጋጀት ላይ ተረባረቡ።
.
ይህን ሴራ ለማሳካት በአንድ በኩል በሰርብ ሪፑብሊክ ውስጥ የሚገኙትን ሁለት ዞኖች(ቮጅቮዲናን እና ኮሶቮን)መሪዎቻቸዉን ያለ አንዳች ተጽእኖ የመምረጥ ስልጣናቸዉን በመግፈፍ የማስመሰያ ምርጫ አካሂደው የሰርብ አጋሮች እንደተመረጡ በማስመሰል ከሰርቢያ ሪፑብሊክ ብቻ በጋሪዮሹ
አመራር ውስጥ ካለው ስምንት ድምጽ በቌሚነት ሶስት ድምጽ እንዲኖራቸው ሰሩ (ከሰርቢያ ሪፑሊክ 1 ፣ ከቮጅቮዲና 1 እና ከኮሶቮን 1 ድምጽ)።
.
በሌላ በኩል ደግሞ በሰርብ ተጽእኖ ስር ትገኝታ በነበረችው ሞንቴኔግሮ ውስጥም የሰርብ ታማኝ አገልጋይ እንዲመረጥ በማድረግ ከሰርብ ሪፑብሊክ ሶስት ድምፅ ከሞንቴኔግሮ አንድ በማስመዝገብ ከስምንት ድምጽ አራት ለመያዝ በቁ:: በቌሚነት በጋሪዮሽ አመራር ውስጥ ከ ስምንት ድምፆች ዉስጥ አራቱን ለመቆጣጠር በመቻል ቢያንስ ውሳኔዎች እንዳይወሰዱ ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ
ፈጠሩ።
.
የሰርብ ሪፑብሊክ አክራሪ አሃዳዊ መሪዎች የ 1974 ቱ ን ህገ መንግስት በመሻር የቮጅቮዲናን እና የኮሶቮን ራስን በራስ የማስተደር መብት መግፈፍና ሞንተኔግሮን በተጽእኗቸው ስር በማስገባት አንድነቷ የተጠበቀ ዩጎዝላቪያን መልሶ ለማቌቌም እቅዳቸዉን መፈጸም መጀመራቸዉን ያስተዋሉ የተቀሩት ሪፑብሊኮች ከሰርብ ጋር አብሮ መቀጠል የማይቻል ነው ወደሚል መደምደሚያ ስለ ደረሱ
መገንጠል የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ጀመሩ።
.
የተቀሩትን ሪፑብሊኮች የመገንጠል እንቅስቃሴ ለማስቆም የሰርብ ሪፑብሊክ
አክራሪ አሃዳዊ መሪዎች ለረዥም ግዜ በሰርቦች ተፅዕኖ ስር የነበረዉን የዩጎዝላቪያን የሃገር መከላከያ ሰራዊት በመጠቀም ለመገንጠል የሚሞክርን ሪፑብሊክ በማሸማቀቅ እስከ ማስቆም የሚቻልበትን መንገድ በመቀየስ ወደተግባር ለመግባት ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ::
.
3ኛ) በዝያ ወቅት ከ 275 000 በላይ መደበኛ ወታደሮች ፣ 960 000 ተጠባባቂ ወታደሮች ፣ 400 የጦር አውሮፕላኖች ፣ 200 የጦር ህሊኮፕተሮች ወዘተ የነበረው የዩጎዝላቪያ ህዝባዊ ሰራዊት ከከፍተኛ የጦር ሃይል አዛዦች እስከ ተራ ወታደሮች ድረስ ሰርቦች በከፍተኛ ቁጥር የሚገኙበት ስለነበር ከሰርብ አክራሪ ብሄርተኞች የፖለቲካ እይታ ጋር የሚጣጣመውን “አንድነቷ የተጠበቀች ዩጎዝላቪያን ማስቀጠል” የሚለውን የመሸንገያ አገራዊ ስሜት መቀስቀሻ በማስተጋባት ሰራዊቱን ለመጠቀም የተቀናበረ ሥራ ሰሩ።
.
የዚህም ዝግጅት ዋንኛ ግብ ከዩጎዝላቪያ የመገንጠልን ተነሳሽነት ሰራዊቱን አንደ ማስፈርስሪያ በመጠቀም ቀድሞ ማምከን እና የመገንጠልን እንቅስቃሴ የሚጀምር ሪፑሊክ ካለ ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ማንበርከክ ነበር። ለአክራሪ ሰርቦች ድርጊት ከተቀሩት ሪፑብሊኮች የተሰጠው ምላሽ ግን ሰርቦች የተመኙት የሰርብ የበላይነት የሚንፀባረቅበትን አንድ ዩጎዝላቪያን አጠናክሮ የመቀጠል ፍላጎት ማሳየት ሳይሆን የጠነከረ የመገንጠል ጥያቄ ነበር ::
.
በዚህ ሁኔታ ሪፐብሊኮቹ የመገንጠል እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ሰራዊቱ ምንም እንኳን በሰርቦች ተፅዕኖ ስር የነበረ ቢሆንም ሌሎች የተለያዩ ብሄር አባላት ያሉበት ስለነበር እና እነዚህም የሰራዊቱ አባላት በህዝባቸው ላይ ጥቃት ለመፈፀም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የመገንጠል እንቅስቃሴውን ለማፈን የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። በዚህም ምክንያት እንደ መሶዶንያ ያሉ ይህ ነው የሚባል ሰራዊት የሌላቸው አነስተኛ ሪፐብሊኮች (ከ 700000 በታች ህዝብ ያላቸው) ጭምር ነጻነታቸውን በማወጅ ራሳቸውን የቻሉ ሃገር መሆን ችለዋል ::
.
ለዚህ ማሳያ ዩጎዝላቪያ በመበታተን ጉዞዋ ባጋጠማት አራት ጦርነቶች ወቅት የዩጎዝላቪያ ብሔራዊ ሰራዊትን ሚና በአጭሩ እንዳስሳለን
.
በ June 1991 ስሎቬኒያ ነፃነቷን ስታዉጅ የዩጎዝላቪያ ህዝባዊ ሰራዊት ለአስር ቀናት ብቻ ከስሎቬኒያ ሃይል ጋር ፍጥጫ ዉስጥ ገብቶ ስሎቬኒያ ነፃ አገር መሆኗን የተቀበለ ሲሆን በዝያውኑ ወቅት አንዳችም እንቅስቃሴ ሳይደረግ የመሰዶንያን ነፃ አገር መሆን እንደገና ታወጀ :: ሁለቱ ክስተቶች ያሳዩት በአገር አንድነት ስም የሚነግዱት የሰርብ አክራሪ ብሄርተኞች እንደ ጠበቁት የዩጎዝላቪያ ህዝባዊ ሰራዊት ተልእኮዬ የዩጎዝላቪያን አንድነት መጠበቅ ነው በሚል ጭፍን አካሄድ የስሎቬኒያን እና የመሰዶንያን እንዲሁም በሁለቱ ሪፑብሊኮች ይኖሩ የነበሩ የሌሎች ሪፑብሊክ ዜጎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያለመፈቀዳቸውን ነው።
.
በዚያው አመት በ June 1991 ክሮሺያ ነጻነቷን ማወጇን ተከትሎ ክሩዋት ነፃ ከሆነች የግዛቷ አካል ሆነው መቀጠል የማይፈልጉ በክረጂና የሚኖሩ ሰርቦች ነጻ የሰርብ ሪፑብሊክ በክረጂና ለመመሰረት መንቀሳቀስ ጀመሩ። ወደ ክሮሺያ የተሰማራው በሰርብ ተጽዕኖ ስር እንደነበረ የሚታወቀው ዩጎዝላቪያ ህዝባዊ ሰራዊት እንደ አገራዊ ሰራዊት ሁሉንም በክሮሺያ ይኖሩ የነበሩ ዩጎዝላቪያዊያንን
በእኩልነት የማገልገል ግዴታዉን ከመወጣት ይልቅ ከክረጂና ሰርቦች ጎን በመሰለፍ በክረጂና ይኖሩ በነበሩ ክሩዋቶች እና የሌሎች ብሄረሰቦች አባላት ላይ እጅግ አስከፊ ጭፍጨፋ ፈጸመ።
.
እስከ 1991 ማለቂያ በቆየዉ ጦርነትም ምክንያት የክረጂና ህዝብ 36% የነበረው የክሩዋቶች ቁጥር ወደ 12% እንዲሁም የክረጂና ህዝብ 12% የነበሩት የሌሎች ብሄረሰብ ህዝቦች ቁጥር ወደ 5% ሲወርድ የሰርቦች ቁጥር ከ 52 % ወደ 88% ከፍ አለ።
.
በክሮሺያ የታየው ክስተት የሚያመላክተው የሰራዊቱን ውጫዊ ገፅታና ስለ ሰራዊቱ ይስተጋባ የነበረውን ፕሮፖጋንዳ በማድመጥ ብቻ የዩጎዝላቪያ ህዝባዊ ሰራዊት በአገራዊ (በብሔራዊ) ስሜት የታነፀ እና አገራዊ እይታ የነበረው ነው ከሚል መደምደሚያ በመድረስ የሰራዊቱ አባላት ለ ethnic ማንነታቸዉ ይሰጡ የነበረዉን ስፍራ ከግምት ያለማስገባት የተሳሳተ ስሌት እንደ ነበር መሆኑን ነው ::
.
በ1992 ቦስኒያ ሄርዘጎቪና ነጻነቷን ማወጇንም ተከትሎ የቦስኒያ ሰርቦች በበኩላቸው ሪፑብሊክ ሰርብስካን መመስረታቸዉን ይፋ በማድረግ ሰርቢያን መቀላቀል እንደወሰኑ ገለፁ :: የቦስኒያ ሰርቦችም የዩጎዝላቪያ ህዝባዊ ሰራዊት ለቀው ወደ ሰርብ ሰራዊት በተቀላቀሉ ሰርቦች በመታገዝ በፈጸሙት ጥቃት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የቦስኒያ ሙስሊሞች እና ክሩዋቶችን በጅምላ ጨፍጭፈው በጅምላ መቃብሮች ቀበሩ ፣ እንደ Omarska concentration camp በመክፈት በቦስንያ ሙስሊሞችና ክሩዋቶች ላይ አሰቃቂ ወንጀሎችን ፈጸሙ፣ በሰረብረኒካ ቁጥራቸው ከስምንት ሺ የሚበልጡ ሙስሊም የቦስኒያ ጎልማሶችና ወጣት ወንዶችን በተባበሩት መንግስታት በሰላም አስከባሪዉ ሃይል እይታ ስር በግፍ ጨፈጨፉ።
.
ቀጣዩ ጦርነት ከ 1998 እስከ 1999 በኮሶቮ የተደረገው ነው። በዚህ ጦርነት የሰርብ መሪዎች አስከፊ ጥቃት ፈጸሙ። ጥቃቱ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ። ሁኔታውን በነበረበት ለመግታት ሰርቦች ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ መፈጸማቸው ሲታወቅ NATO በኮሶቮ ያለዉን የሰርብ ሃይል እንዲሁም በቤልግራድ በሚገኙ ቁልፍ ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን ፈጸመ። የ NATO ን ጥቃት ተከትሎ ሚሎሶቪች
የጦር ሃይላቸዉን ከኮሶቮ አስወጡ።
.
ኮሶቮም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር እንድትተዳደር ተሰወሰነ። በመቀጠልም እስሎቦዳን ሚሎሶቪች በጦር ወንጀል ተከሰው ታሰሩ። ዩጎዝላቪያም ሰርቢያና ሞንተኔግሮ በመባል መጠራት ከጀመረችበት ከ 2003 በኌላ በኦፊሻላዊ መንገድ ከሰመች።
.
በዚህ መልክ በፌደራል ሥርዓት ስር ከወገኖቻቸው ጋር በእኩልነት መኖር ያልተመቻቸው አክራሪ ሰርቦች በአንድነት ስም የጥንቷን የሰርብ የበላይነት የሰፈነባት አሃዳዊ አስተዳደር ያላት ዩጎዝላቭያን ለመመለስ ያደረጉት እንቅስቃሴ እነሱ በሚመኟት ሰርብ አምሳል የተገነባች አንድ ዩጎዝልቪያን ሳይሆን ሰባት ነጻ መንግስታቶችን አዋለደ ።
.
አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ እያንዳንዳችን ከስሜታዊነት እና ከእልሕ ፖለቲካ በመዉጣት የሌሎች ወገኖቻችንን ፍላጎት ለመረዳት በመሞከር ራሳችንን ለሰጥቶ መቀበል የምናዘጋጅበት ወቅት እንጂ በእብሪት ተሞልተን ወገናችንን ካሰመርኩልህ መስመር ልትወጣ አይገባም የምንልበት አይደለም ::
.
እናም ወገን በጀመርነው የቁልቁለት መንገድ ብዙ ርቀን ሳንሄድ ቆም ብለን ብናስብ የሚበጀን ይመስለኛል ::>>
photo: Abiy Ahmad ... Ethiopia's own Slobodan Milosevic [an ultra Serbian 'ahadawi' nationalist - the architect of Yugolslavia's disintegration]?
yaballo,
It is clear that the so-called Amhara (mix) community’s regime worst that Serbs of Serbia. Consequently, it is in near future we are gonna witness several republics in the HA.