ሰበር ዜና፣ የትግራይ ልዩ ሃይል በኤፍ ኤስ አር (FSR) መኪኖች ተጭነው ከወደ ትግራይ እየመጡ ነው!
Posted: 03 Nov 2020, 10:06
በዚህ ሰዓት ብዙ ቁጥር ያለው የትግራይ ልዩ ሃይል በኤፍ ኤስ አር (FSR) መኪኖች ተጭነው ከወደ ትግራይ እየመጡ ነው:: ራያ ኮረምን አቆራርጠው ወደ ራያ አላማጣ ወደ ራያ ዋጃ ጥሙጋ እና ሰሌን ውሃ እየከነፉ ነው። የራያ ሚሊሻዎች ቤተሰቦቻቸውን እንዲሰናበቱ ታዘዋል:: ለግዳጅ የሚወጣ ሰው መቸ እንደሚመለስ አይታወቅም የሚል መልእክት እያስተላለፉ ነው። በሰሌን ውሃ አድርገው ራያ ቆቦ አካባቢ እንደሚገቡ እና ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ተነግሯቸዋል::
"ሰራዊት አዘጋጅተናል:: ሚልሻ አዘጋጅተናል:: ልዩ ሃይል አዘጋጅተናል:: ለሰላም ነበር የተዘጋጀነው:: ጦርነቱ የሚጀምር ከሆነ ግን እናሸንፋለን::" ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
ይሄው ባሉት መሰረትም ልዩ ሃይሉን ወደ ራያ አላማጣ ራያ ዋጃ ጥሙጋ : ራያ ጨርጨር እና ራያ አዘቦ ድንበሮች ላይ እያስጠጉ ይገኛል:: ህዝቡን ለጦርነት እየቀሰቀሱ ነው:: ሚሊሻውን እያዋከቡት ሲሆን አሁን በዚህ ሰዓት ሚሊሻው ወደ ግንባር እንዲዘምት እየሰበሰቡት ይገኛሉ:: በቅርብ ቀናት ውስጥ የትህነግ ልዩ ሃይል የአማራ ክልልን ይወጋል:: ጦርነቱን ስለፈለጉት አይቀሬ ነው:: ትንኮሳ ፈፅመው ቶሎ ያስጀምሩታል:: አንድ ክልል የፌደራል መንግስትን ወጋ ተብሎ በታሪክ ይፃፋል!!!