Dear Eden:
You may consider this as background knowledge for your research
Any improvement displayed by the MLLT/TPLF (Tigraiy People's Liberation Front) might appear to be better than never, but the issues that cause problems to Etiyopiya and Eritrea are more than just the case of a federal State structure based on nations and nationalities. The fundamental problem with MLLT/TPLF leaders is the fact that they are not true to themselves and others. Do you know how one could tell when they are lying? When they open their mouths to talk. Deception seems to be their over-arching modus operandi (i.e. their established way of doing things). Read the following interview (part 2) carefully as well as patiently.
አዲስ ዘመን፡- በ35 የጀመረው ስብስብ በ25 ጸንቶ ጥምረቱን መፍጠሩ ይታወቃል:: ሆኖም በተፈጠረው የሀሳብ ልዩነት አሁን ላይ እናንተ ወደ አዲስ አበባ ስትመጡ የተወሰኑት ከህወሓት ጋር መሆናቸው ታውቋል:: ይሄን በቁጥር ቢገልጹልን? በጥምረቱ አባላት መካከል ይሄን መሰል መከፋፈል የተፈጠረበትን ምክንያትም ቢያስረዱ?
አቶ ደረጀ፡- የጥምረቱ 25 አባል ፓርቲዎች ያቀረብነውን ጥያቄ ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ መሆናቸውን አረጋግጦ በደብዳቤ ያሳወቃቸው ናቸው:: ከእነዚህ 25 ውስጥ ደግሞ አዲስ አበባ የተሰባሰብነው 18 ፓርቲዎች ነን:: ህወሓትን ጨምሮ ሰባቱ መቐሌ የቀሩ ናቸው:: በመሆኑም 18ቱ ፓርቲዎች ከፌዴራሊስት ኃይሉ ጋር እየተንቀሳቀሱ ያሉ ናቸው:: ለዚህ መከፋፈል ያበቃው ደግሞ ሌላ ምንም የሚጠቀስ መሰረታዊ ጉዳይ የለም:: ዋናው ጉዳይ መቐሌ ካልሆነ የሚለው የህወሓት ምክንያት አልባ ሴራ ነው:: እኛ ደግሞ ማዕከሉ አዲስ አበባ ይሁን የምንል ሃይሎች ነን፡፡
ስብሰባው አዲስ አበባ እንዳይካሄድና መቐሌ እንዲካሄድ ደግሞ ህወሓት ለእኔም ጭምር እዚህ ድረስ የአውሮፕላን ትኬት ልኳል:: አልጋ የት እንደተያዘልኝም ተነግሮኛል:: ሆኖም ልዩነቱ የተፈጠረው በዋናነት መቐሌ በመሄድና አዲስ አበባ በመሄድ ነው:: በዚህም 18ታችን እዛ ላለመሄድ በመወሰን አዲስ አበባ ቀርተናል:: እንደሰማሁት ከሆነ ህወሓት የተቀሩትን የራሱ አጋር እንዳደረጋቸው ሲሆን፤ እኛ ወደ አዲስ አበባ አንመጣም የሚል አቅጣጫ ይዘዋል፡፡
እነዚህ ፓርቲዎች ደግሞ በፊትም የሚንቀሳቀሱት በትግራይ አካባቢ ሲሆን፤ የተወሰኑት ደግሞ በአዲስ አበባ ነበር:: በመሆኑም እዛ የቀሩት የትግራይ እና የአዲስ አበባ ፓርቲዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ከህወሓት ጋር ሶስቱ የትግራይ እና በልጅ መስፍን የሚመራውን ፓርቲ ጨምሮ ከአዲስ አበባ ያሉ ናቸው:: ከእነዚህ ውጪ ሌሎች የሶማሌ፣ የአፋር፣ የሐረሪ፣ የኦሮሚያ፣ የደቡብና ሌሎችም ክልሎችን የወከሉ ፓርቲዎች በሙሉ እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ነው ያሉት፡፡
አዲስ ዘመን፡- ከሰሞኑ አዲስ አበባ ላይ ያካሄዳችሁት ስብሰባ ዓላማው ምንድን ነው? ምንን መሰረት ያደረገስ ነው?
አቶ ደረጀ፡- ስብሰባው ግልጽ ነው:: ለእነሱም ነግረናል:: ይሄ የተለየ ፖለቲካዊ አጀንዳ የያዘ አይደለም:: የስብሰባው ዓላማም ሆነ መሰረት አንድምጥምረቱ ጽህፈት ቤቱንም ሆነ ስብሰባውን አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ መወሰኑን ለመግለጽ ነው። ከዚህ ባለፈ ደግሞ አገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም ምርጫውን ተከትሎ ህወሓት የያዘው የብቻ ውሳኔ ላይ ያለንን አቋም ማሳወቅ ነው:: ከአገራዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ስለ ኮቪድ 19 ወረርሺኝ ጉዳይ ሲሆን፤ በዚህም ህዝባችን ከዚህ ወረርሽኝ መጠንቀቅ እንዳለበት እና እኛም እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ ጥምረት ጉዳዩ ስለሚመለከተን ህዝባችን ከዚህ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለበት የራሳችንን መግለጫ መስጠት/ለማውጣት ነው፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ፣ የ2012ቱን አገራዊ ምርጫ የተመለከተ ሲሆን፤ በዚህን ጊዜ ሰው ተራርቆ በሚንቀሳቀስበት፣ ተራርቆ በሚበላበት፣ ከቤት በማይወጣበትና ፍርሃት ባለበት ሰዓት ምርጫ ማካሄዱ አግባብ አይደለም የሚለውን አቋማችንን ያሰማንበትን ዓላማ መሰረት ያደረገ ነው:: ሶስተኛም፣ እኛ ከገዢው ፓርቲ ጋር መደጋገፍም ሆነ ተቃውሞ ቢኖረንም በአገር ጉዳይ አንድ መሆናችን ለመግለጽ ነው። በዚህም የህዳሴ ግድቡ የሁላችንም ጉዳይና ፕሮጀክት እንደመሆኑ ይሄንን የሚመለከቱ ማናቸውንም ጉዳዮች ብሎም ከውጪ የሚመጡ ተቃውሞዎችን ከመንግስት ጎን ሆነን ለመከላከል ያለንን አቋም ለመግለጽ ነው፡፡ በግድቡ ላይ የሚቃጡ ማናቸውንም ነገሮች ከመንግስት ጎን ሆነን አብረን መከላከል አለብን እንጂ መቃወም የለብንም፤ ግንባታውም ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን መቋረጥ የለበትም:: ለምን ቢባል፣ ግድቡ የእናቶች፣ የወጣቶች፣ የአዛውንቶች በጥቅሉ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አሻራ እና ላብ እስከሆነ ድረስ ጉዳዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን የአገርና ህዝብ ህልውና ጉዳይ በመሆኑ ነው:: እኛም ይሄንን አቋም ነው ያራመድነው፡፡
ከዚህ ውስጥ ግን ህወሓት ምርጫውን አካሂዳለሁ አለ:: ያንን ምርጫ ለማካሄድ ግን እንደ ስብስብ ኃይሉ የጋራ ስምምነት እኛን ማሳወቅ አለበት:: ምክንያቱም እኛ ልናውቅ እና ወይ ልንቃወም ወይም ልንደግፍ ይገባል:: የጋራ ጥምረት እንደመሆኑ በጋራ ነው ወስነን መሄድ የነበረብን፤ በጋር የተመሰረተ ጥምረት እንደመሆኑም መግለጫውን መስጠት የነበረብን በጋራ ነው:: ሆኖም ወደ 20 የሚሆኑት የጥምረቱ አባላት ምርጫውን አናካሂድም እያሉ ባለበት ሁኔታ ህወሓት ለብቻው ይሄን ውሳኔ ማሳለፉ ተገቢም ትክክልም አይደለም፡፡
ምክንያቱም ሰው ሊመርጠን የሚችለው ሰላምና ጤነኛ ሆኖ ሲኖር ነው:: አገርም ተማምኖ መሄድ ሲችል ነው::ካልሆነ በጀብደኝነት ተነስቼ ምርጫ ላካሂድ ብል አያዋጣም:: እኛም ይሄን ስለምንገነዘብ ለምን እኛን ሳታማክሩ መግለጫ ሰጣችሁ ብለንም ጠይቀናል:: ሆኖም ይህ የግሌ ነው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አይመለከታችሁም የሚል ሀሳብ ይዞ ነው የመጣው:: እኛም በበኩላችን የስብስቡ አባል እስከሆናችሁና የጋራ ስምምነት እስካለ ድረስ መፈጸም ያለበት በጋራ እንጂ በአንድ ፓርቲ የግል ፍላጎት አይደለም፤ አካሄዱም
አንድነት አያመጣም፤ ምክንያቱም፣ ሶማሌው ለብቻ አንድ ሲል፣ አፋሩም ሌላ ሲል፣ ኦሮሞውም ለብቻው ሌላ ሲል ነገሮች ልክ አይመጡምና ምርጫውን ማካሄድ አትችሉም በማለታችን በመካከል ጭቅጭቅ ነበር:: የአዲስ አበባውስብሰባ መሰረትና አንዱ ዓላማ በዚህ መልኩ ከጥምረቱ አቋም ውጪ ህወሓት ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ የወሰነው ግላዊ ውሳኔ ተገቢም ትክክልም አለመሆኑን ለመግለጽ ነው::ን
አዲስ ዘመን፡- በዚህ ሁሉ ሂደት ውስት ከህወሓት ጋር በጥምረት በቆያችሁባቸው ጊዜያት ቀደም ሲል ከውጭ ስትሰሙትና ስትገምቱት ከነበረው አንጻር ስለ ህወሃት ባህሪና እውነተኛ ማንነት ምን የተለየ ነገር ተገነዘባችሁ?
አቶ ደረጀ፡- እውነት ለመናገር፣ ከህወሓት የተረዳነው ባህሪ አንዱ፣ ህወሓት ማለት የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው::የተወሰኑ ቡድኖች ብዬ ስል የትግራይ ህዝብ ወይም በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ተማሪውም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍልን ስታይ ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም:: ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ጨምሮ ሌሎችም የትግራይ ክልል ክፍሎችን ባስጎበኙኝ ወቅት ተመልክቼ ተገንዝቤያለሁ:: በእነዚህ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በነበረኝ ጉብኝት ተመለከትኩት
እና አንዳንዴም አማርኛ የሚናገሩ/የሚችሉ ሰዎችን አነጋግሬ እንደተረዳሁት፤ ህወሓት ከህዝቡ ጋር የለም:: ምናልባት የተወሰነ ህዝብ ነው ከህወሓት ጋር ያለው፡፡
ይሄ የተወሰነ ህዝብ ደግሞ በመቐሌ ከተማ እና ዙሪያዋ ያሉ ጥቂት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ ሌላው ቀርቶ ወደ አድዋና አክሱም ስንሄድ እውነት ለመናገር ህዝቡ የሚያሳዝን ህዝብ ነው:: ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ ህዝብ አንደኛ፣ በአሁን ጊዜ በዚህ ዘመን ለእግሩ እንኳን ጫማ የሌለው ህዝብ ነው:: ልብስ በረከሰበት በዚህ ወቅት ልብስ እንኳን መልበስ ያልቻለ ህዝብ ነው:: ይህ ደግሞ ጥቂት የህወሓት አመራሮችና አባላት ገንዘቡንም ለራሳቸው፤ አገሩንም የራሳቸው አድርገው እንደያዙት የሚያሳይ ነው፡፡
እንዳየሁት ከሆነ ህዝቡ መፈናፈኛ ስላጣ ነው ዝም ያለው:: ለዚህ ደግሞ ወደ ዛላንበሳ በሄድኩበት ወቅት ያነጋገርኳቸው አንድ አዛውንት ያጫወቱኝ ትልቅ አብነት ነው:: እኚህ አዛውንት እንዳጫወቱኝ፣ እዚሁ ተወልጄ የኖርኩ ነኝ፤ ነገር ግን ስርኣቱ ወይም የህወሓት አስተዳደር ለእኔም ሆነ ለአካባቢው ምንም ያደረገው ነገር ስለሌለ አብዛኛው በችግር ውስጥ ያለ፤ በእድሜ መግፋት ምክንያት ከቤት የማትወጣው ባለቤቴም ሆነች እኔም በቤተ ክርስቲያን እርዳታ ኑሮዬን እየገፋሁ የምንኖር ህዝቦች ነን ነበር ያሉኝ:: በህወሓት አገዛዝ ምክንያትም በርካታ ወጣቶች ከአገር ለመውጣትና ለመሰደድ ስለመብቃታቸውም ነው ያጫወቱኝ፡፡
ይሄን ከመስማቴና ክልሉን በተለይ ገጠራማውን አካባቢ ከመመልከቴ በፊት፤ እኔም የነበረኝ ግንዛቤ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች በተለየ መልኩ እንደተጠቀመ፤ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ብዙ ነገር እንዳገኘ ነበር:: እንደኔ ሁሉ ሌሎችም እንዲሁ ሊያስቡ ይችላሉ:: እውነቱ ግን ይሄ አይደለም፤ የትግራይ ህዝብ ጭቆና ውስጥ ነው ያለው:: የትግራይ ህዝብ በኢኮኖሚው አሁንም ወደኋላ የቀረ ነው:: የኢኮኖሚው ችግር ደግሞ ከምግብ እስከ አልባሳት በሚፈልገው ልክ እንዳያገኝ ያገደው ህዝብ ነው:: መቐሌን ጨምሮም በየከተማው ያለ ወጣትም መስራት በሚችልበት እድሜውና ሰዓቱ ያለስራ ከጠዋት እስከ ማታ በየበረንዳውና በየመንገዱ ላይ ባሉ የጀበና ቡናዎች ወንበር ላይ ተቀምጦ ዳማ እና ካርታ ሲጫወት የሚውልበትን እውነት ተመልክቻለሁ:: ከዚህ በተቃራኒው ግን ጥቂት የህወሓት አባላትና ወደ ህወሓት የሚጠጉ ሰዎች ግን የናጠጠ ኑሮ ይኖራሉ፡፡
ስለዚህ ህወሓት አንድ ነን እንደሚለው፤ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአንድ ላይ ማየት የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ:: ምክንያቱም፣ ከዚህ በፊት ከአመራሮቹ ስንሰማ እና እኔም ትግራይ ስሄድ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ፤ የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው ብዬ ነበር የምወስደው:: አሁን ውስጡ ገብቼ ባየሁት መሰረት ግን በጣም የተራራቁ ናቸው:: ህዝቡ ከእጅ ወደ አፍ በሆኑ ኑሮ ውስጥ ነው ያለው:: ጥቂት የህወሓት አመራሮችና እነርሱን ተጠግተው ያሉት ግን በጣሙን ከህዝቡ የራቀና ሊነጻጸርም በማይችል የናጠጠ ኖሮ ውስጥ ነው ያሉት:: በትላልቅ ሆቴሎች ነው የሚዝናኑት:: ህዝቡ ግን አሁንም ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው:: በመሆኑም የህወሓት ጥቂት ቡድኖች እንደሚሉት ህዝቡን እና ህወሓትን አንድ ላይ ጨፍልቆ ማየቱ ተገቢ አለመሆኑን፤ እነዚህ ጥቂት የህወሓት አመራሮች የሚሉትም በጣሙን የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ:: እኔም ትግሬ ሁሉ የተጠቀመ፤ ትግሬ ሁሉ የህወሃት አባል የሆነ አድርጌ ሳይ የነበረበት ሁነት የተሳሳተ መሆኑን አይቼ በመገንዘብ፤ ይሄን ምስል ያስያዘኝ የህወሓት አሳሳች የሴራ ምስል መሆኑን በተግባር አረጋግጫለሁ፡፡
አዲስ ዘመን፡- ከፌዴራሊዝም አንጻር እርሶ ስለ ፌዴራሊዝም ካለዎት ግንዛቤ በመነሳት እንዲሁም ህወሓት በቃል ከሚናገርለት ፌዴራሊዝምና የፌዴራሊዝም ጠበቃነት አኳያ፤ በጥምረት አብረው በቆዩበት ጊዜ በህወሓት ቤት ፌዴራሊዝም በቃል እና በተግባር እንዴት የሚገለጹ ሆነው አገኟቸው?
አቶ ደረጀ፡- ፌዴራሊዝም እኮ የእኩል አስተዳደር ነው:: ፌዴራሊዝም ስንልም የጋራ አስተዳደር ማለታችንም ነው:: ህወሓት ግን የእኩል አስተዳደር ብሎ ነገር የለውም::ህወሓት የበላይነቱን ለማንጸባረቅ ብቻ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: የህወሓት አመራሮች ቦረና ያለውን ከብት አርቢ ነው፤ ሶማሌ ያለውን እንዲህ ነው እያሉ ከመናገር ውጪ፤ ቦረና ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ ሶማሌ ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ እንዲሁም የአካባቢውን ልማት መምራት ይችላል ብሎ የሚያስብ ቡድን አይደለም:: የራሱን የበላይነት ብቻ ለማንጸባረቅ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: ይሄን የበላይነቱን ለማረጋገጥም በየቦታው የራሱን የስለላ መረብ በመዘርጋት የሚሰራ ቡድን ነው፡፡
ፌዴራሊዝም ማለትኮ የመጀመሪያው ጉዳይ ራስን ማስተዳደር ነው:: በራስ መዳኘት ነው:: በራስ ቋንቋ መማር ነው:: ህወሓት ግን ያንን ለይምሰል ይናገር እንጂ ውስጥ ገብተን ስናየው የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚጨፈልቅ ቡድን ነው:: ይሄንን መብት ጨፍልቆም እሱ እንዴት መግዛት እንደሚችል የሚያስችለውን የወጥመድ መረብ የሚዘረጋ ነው:: ለዚህ ደግሞ በስለላ መረብ በጣሙን የተሳሰረ ነው:: በሆቴልም ሆነ በየትም ያለ ሰራተኛን በዚህ መረብ ውስጥ በማስገባት የስለላ መረቡ አባል አድርጎታል:: ከዚህ አንጻር ለምሳሌ እኔ በጅማ ወይም ኢሉባቦር አካባቢ ሄጄ አንድ ነገር ስፈጽም የህወሓት ሰላዮች እዛው ስላሉ ወዲያው መረጃው ይደርሰዋል:: ስለዚህ እኔ በጥምረቱ ውስጥ ካለሁት ሰው ይልቅ እነርሱን ይቀበላል:: ይህ ደግሞ የፌዴራሊዝሙን ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለውን የሚያፋልስ ነው፡፡
የዚህ ጨፍላቂነቱ ማረጋገጫ የሚሆነው ደግሞ፤ እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎችና ምርጫ አናካሂድም በሚሉበት ወቅት እርሱ አካሂዳለሁ ማለቱ የራሱን የበላይነት ለማንጸባረቅ የሚያደርገው ድርጊት ነው:: ከዚህ ባለፈ ስለ ህዳሴው ግድብ ያገባናል ብለን ሁላችንም ፓርቲዎች ስንናገር፤ ስለሱ ጉዳይ መንግስትን እንጂ እኛን አይመለከትም ማለቱ ነው:: ይሄን የሚል ድርጅት ደግሞ የፌዴራሊዝም ጠበቃ ሊሆን አይችልም:: ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት ከዳር እስከዳር ያሉ የፌዴራል መንግስቱ አባል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ያሉ ህዝቦች ፕሮጀክት ሆኖ ሳለ፤ ይሄን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ስለሆነው ግድብ አያገባንም ብሎ መናገር አግባብነት የሌለው፣ ስለፌዴራሊዝም የማያስብና የራሱን ኑሮ ብቻ ለማንቀሳቀስ የሚጥር ድርጅት መሆኑን ነው የተረዳሁት፡፡
አዲስ ዘመን፡- እርሱ ከውጪ ሆነው ሲያዩት እና በውስጡ ሆነው ሲያዩት ስለ ህወሓት ከተገነዘቡት አንጻር፤ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስለ ህወሓት ሊያውቁት ይገባል ብለው የሚነግሩትና የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- አንደኛ ለትግራይ ህዝብ ነው መልዕክት የማስተላልፈው:: ይሄውም ህወሓት ላለፉት 40ም ይሁን 50 ዓመት ታግሏል:: አንድ ትግል ደግሞ ወደ ህዝቡ ሰርፆ ይገባና ያድጋል፤ ያለበለዚያ ደግሞ ይከስማል:: አሁን በህወሓት ላይ የምናየው ይሄንኑ ነው:: ምክንያቱም ላለፉት 45 ዓመታት የዘለቀው የህወሃት ትግል የጉዞ ምዕራፉ ወደ መጠቃለሉ እንደመሆኑ መጠን፤ አሁን ላይ የትግራይ ወጣት የህወሓትን ወቅታዊ አካሄድ አይቀበለውም:: ህዝቡም አሁንም በድህነቱ ያለ እንደመሆኑ ከድህነት መውጣትን ይፈልጋል:: ምክንያቱም ህወሓት የዘረፈውን ወደ አውሮፓና መሰል አገሮች ከማሸሽ የዘለለ ለህዝቡ የሰራለት ነገር የለም::
ስለዚህ በተለይ በትግራይ ያለው የገጠር ህዝብ ስለ ህወሓት መሰሪነትና ተንኮል በደንብ ተረድቷል:: የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውንም አካሄድ ተገንዝቧል:: ይሄን የተገነዘበ ህዝብ ደግሞ ህወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል:: የትግራይ ተወላጆችና የትግራይ ህዝብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል:: የትግራይ ወጣቶች፣ የትግራይ ምሑራን፣ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ህወሓትን በቃህ ሊሉት ይገባል:: ለዚህ ደግሞ አንድም፣ ላለፉት 45 ዓመታት ያደረጋቸውን በማሰብ፤ ሁለተኛም አንድ ነገር የተወሰነ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚያቆም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ የህወሓትን አመራሮች እዚህ ጋር በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል፡፡
ለምን ቢባል፣ እነዚህ አመራሮች የራሳቸውን ሀብት አካብተዋል:: ይህ ሀብት ደግሞ በመቐሌ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ጭምር ከህንጻ እስከ ተሽከርካሪ የሚገለጽ ሀብት ነው:: በክልሉ ደግሞ ለእለት ጉርሱም ሆነ ለእግሩ ጫማ እና ለሰውነቱ ልብስ መለወጥ ቀርቶ ማሟላት ያቃተው ህዝብ (በተለይ ገጠሩ) ተፈጥሯል:: እናም እነዚህ አመራሮች እውነትም ለዚህ ህዝብ ታግለንለታል ካሉ ያ ህዝብ ነጻ መውጣት ነበረበት:: ቢያንስ ትንሽ እንኳን መሻሻል ማሳየት ነበረበት:: ስለሆነም እኔ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ ልሂቃንና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የማስተላልፈው ይሄ ለህዝቡ የጠቀመው ነገር የለምና ለህዝቡ የሚጠቅም ፓርቲ ማግኘት ስላለባቸው ለእርሱ የሚያደርጉት ድጋፍ ማቆም መቻል አለባቸው:: ምክንያቱም ይህ ፓርቲ ድጋፍ እያጣ አሁንም ወደ ከተማ የተሰበሰበ እንደመሆኑ፤ አሁን ያለውና የቀረውም ማቆም አለበት:: ይሄን በማድረግም ለራሳቸው የሚበጀውን ማሰቡ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
በየክልሉ ተበትነው ያሉም ሆኑ በውጭ አገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆችም ለህወሓት የሚያደርጉትን ቆም ብለው ማሰብ መቻል አለባቸው:: በሚያደርጉት ድጋፍ በአገሬ ላይ ምን ለውጥ መጣ? ምንስ ታየ፣ የትስ ደረሰ? ማለት አለባቸው:: ህወሓት 27 ዓመት ኢትዮጵያን ሲገዛና ሀብቱን እንደፈለገው ሲያሽከረክር ለእኛ ለትግራይ ህዝቦች ምን አደረገ? ብለው ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው::
ምክንያቱም እነዚህ ቡድኖች ዛሬ ችግር ሲመጣ ወደዛ ተሰበሰቡ እንጂ አካባቢውን እንኳን ሄደው አይተው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው:: ለዚህ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤ ክልሉን ባስጎበኙኝ ጊዜ ከተመለከትኳቸው አከባቢዎች አንዱ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትውልድ አካባቢ ነበረ:: በወቅቱ ስንጎበኝ እርሱም አብሮን ነበር:: የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ እንደሰማሁት ግን አምባሳደር ስዩም ከዛን እለት በስተቀር እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ከማየት ውጪ በአካል አይተውት እንደማያውቁ ሲገልጹ ነበር፡፡
እናም በዚህ መልኩ አካባቢያቸውን በልማት ማገዝ ቀርቶ በአካል ሄዶ መመልከት ሳይችሉ የኖሩ አመራሮች፣ ዛሬ ችግር ሲገጥማቸው ወደ ህዝቡ ገብተው ህዝቡን ለሌላ ጭንቀት ይባስ ብሎም ከሌላው ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን ጥረት በግልጽ ይታያል:: እነርሱ ሲደላቸው እርሱ ሲቸገር የነበረው ህዝብ በእነርሱ ሴራ ዛሬ ከእነርሱ ጋር ተጨፍልቆ እንዲታይ እያደረጉትም ይገኛል:: እናም በክልሉ ያለውም ሆነ በሌሎች ክልሎች ብሎም በውጭ አገራት ያለው የትግራይ ተወላጅ ይሄን ሊያውቁ፤ ለህዝቡ ምን አደረገለት ወይም ምን አደረገበት ብለው ሊመረምሩ እና እነዚህን ግለኛ አመራሮች በቃ ሊሏቸው፤ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ሁሉ የሚፈልገውን ፓርቲ ደግፎ የነጻነት አየር መተንፈስ መቻል አለበት፡፡
ሌላው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ደግሞ፤ የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው:: ዛሬ ላይ የትግራይን ህዝብ እገነጥላለሁ ብሎ የሚፎክረው ህወሃትም የግል ስሜትና ፍላጎቱን እንጂ በህዝቡ ፍላጎትና ድጋፍ እንዳልሆነም ማወቅ ይኖርበታል::
ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ወጥቶ የድጋፍ ድምጽ እንዲሰጥ ይደረግ ቢባል እንኳን አምስት በመቶ እንኳን አያገኝም:: ይሄንንም በክልሉ ቆይታዬ በነበረኝ ጉብኝት ከተለያዩ አካላት (ምሑራንና ህዝቡን ጨምሮ) ባደረኩት የሀሳብ ልውውጥና ውይይት መገንዘብ ችያለሁ:: ህዝቡ ለህወሃት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሚሰጥ እና ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡
ህወሓትም ቢሆን እንደሚያወራው ለብሔር ብሔረሰቦች የሚሰራው ስራ የለም:: ይልቁንም ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ማስቀጠያ በሚያመች መልኩ እንጂ ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለክልሉ የተሻለ እድገት ሲል ያከናወነው ነገር አይታይም:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ በትግራይ ውስጥ በክልሉ ከተወለዱ ህዝቦች እና ጥቂት የመንግስት ስራን ማዕከል አድርገው ካሉ ዜጎች ውጪ በትግራይ የሚኖርም፤ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖረውም አለመደረጉ ነው:: ለምሳሌ፣ በክልሉ አንድም ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር ሆቴል ያለው፤ ፋብሪካ የከፈተም የለም:: በአንጻሩ በሌሎች የክልል ከተሞችና ክልሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሆቴልም ሆነ በሌሎች በርካታ ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ይገኛል:: በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው የማግለል ተግባር ግን የህወሓት ስራ ውጤት እንጂ የህዝቡ ፍላጎትም ተግባርም አይደለም::
በዚህም ዛሬም ቢሆን የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ ያለ፤ የነጻነት አየርን በወጉ ያላጣጣመና በአፈና ውስጥ ያለ፤ ዛሬም ቢሆን ከስጋት ያልተላቀቀ ህዝብ ነው:: ዛሬም እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ ፍላጎት ያለውና ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን የሚናፍቅ ህዝብ ነው:: ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ህዝብም ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ የህዝቡን እውነት ማድመጥ ይኖርበታል:: ህወሓት እንደሚለውም ሁሉም ትግሬ የህወሓት አባል ወይም ደጋፊ ነው ብለው ማሰብም የለባቸውም:: በአንጻሩ ሁሉም ትግሬ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው ማሰብ፤ ንጹሁን ህዝብም ከሰላዩና ዘራፊው ለይተው ማየት አለባቸው:: ምክንያቱም ዛሬ ከህወሓት ጥቂት ቡድኖች ጋር ያሉት አንድም እነዚሁ የቡድኑ አባላት፤ ሁለትም ከህወሓት ጋር በፈጠሩት ትስስር እርሱንም መከታ አድርገው ሲዘርፉና የሰውን ንብረት ጭምር ሲበዘብዙ የነበሩ ቡድኑን ከተውት ያላቸውን የሚያጡ የሚመስላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ፡፡
አዲስ ዘመን፡- አሁን ላይ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገለጻል? ምንስ ይፈልጋል?
አቶ ደረጀ፡- አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ጉዳይ ስናይ የታየውን አገራዊ ለውጥ/ሪፎርም ተከትሎ አገር እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ነው:: አገር ያለ መሪ ልትኖር ስለማትችልም ይህ መሆኑም ያለበት ነው:: በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከሰተ:: ይህ በሽታ ሲገባ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጠው ለህዝብ ነው እንጂ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም አስተዳደር ወይም ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚንስትርነት አይደለም:: ህዝቡ ደህና መሆን ስላለበት መጀመሪያ ለህዝብ ጤንነትና ደህንነት ነው::
ሆኖም አሁን የፖለቲካ አሰላለፉን ስናይ በአብዛኛው አንድ ላይ እየተሰበሰበ ነው ያለው:: እኛም በዚህ መልኩ ሰብሰብ ማለታችን ይሄ አስፈላጊ በመሆኑ ነው:: ስለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታው ይሄንን ማድረግን ወይም ሰብሰብ ማለትን ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በዚህ መልኩ አንድ ላይ መምጣት ይገባል እንጂ፤ እኔ የመንደር ፖለቲካ አቋቁሜ ኢትዮጵያ ላይ እንደፈለኩ መጮህ አልችልም:: አንድ ላይ ከመጣንና ድምጻችን መሰማት ከጀመረ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆን አለብኝ:: የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኔ ወይም ስሆን ደግሞ ኦሮሞን አስደስቼ አማራን ማስከፋት የለብኝም፤ አማራን አስደስቼ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን ማስከፋት የለብኝም፤ ሁሉንም አንድ ላይ ነው ማየት ያለብኝ:: የእኛም ጥምረት ለዛ ነው ኢትዮጵያን በሙሉ ያቀፈውና በሁሉም ክልሎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው:: ይህ ደግሞ አንድ ቦታ ላይ ለሚደርስ ችግርና ተጽዕኖ ሁላችንም ተጠያቂ ነን፤ ሁላችንም ይመለከተናል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ አመራር በያዘው አካሄድ አገር አቀፍ ሆኖ ቢንቀሳቀስ ጥሩ ነው:: በዚህ እንቅስቃሴው ሌሎችንም ለማሳተፍ መሞከሩም ጥሩ ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲናገሩ “ልንረዳችሁ የምንችለው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ ላይ ስትሰባሰቡ ነው” ነው ያሉት:: በዚህ ንግግራቸው “ስትጨፈለቁ ነው” አላሉም፤ “ስትሰባሰቡ” ነው ያሉት:: ስትሰባሰቡ ግን እንደማንኛውም አገር አስርም እንሁን አምስትና አስራ አምስት በእውነት ለህዝብ የምንታገል፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ በዓላማ የምንገናኝ ሰብሰብ ማለት እንችላለን፡፡
ለምሳሌ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ በኦሮሞነቴ ሶማሌውን እንደራሴ ነው ማየት ያለብኝ:: አንዱ አማራም አንዱን ደቡብ እንደራሱ ነው ማየት ያለበት:: በዚህ መልኩ አንዱ ሌላውን እንደራሱ ማየት እንጂ ነጣጥሎ ማየት የለበትም:: በዚህ መልኩ እንደ ኢትዮጵያዊነት ማየት እና በኢትዮጵያዊነት መታገል፤ በህዝባችን ላይ ፍትህ ሲጓደል ለፍትህ መቆም ይገባል:: የፖለቲካ መሪ ማለትም ለህዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ እንጂ ለመዝናናት የተዘጋጀ አይደለም:: ሞት እንኳን ቢመጣ እቀበላለሁ ብሎ የገባ ነው:: በመሆኑም በዚህ መልኩ ሞት እንኳን ቢመጣ ካንተ በፊት እኔ እቀበላለሁ ብዬ እስከገባሁ ድረስ በኢትዮጵያዊነቱ አንድ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰብሰብ ብለን በጋራ መስራት ይኖርብናል፡፡
ካልሆነ ለአንዷ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ወይም ለሚኒስትርነት ቦታ ሁሉም ሊደርስ አይችልም:: 110 ሚሊዬን ህዝብም ሆነ 107 ፓርቲ ይሄን ማድረግ አይችልም:: ሆኖም 110 ሚሊዬኑም ህዝብ አገሬ ነው ብሎ በእኩልነት ያለመሳቀቅ ህግን አክብሮ እንደ ልቡ የሚኖርበትን አገር መፍጠር ይቻላል:: አሁን ያለው አመራርም ከልምድ የሚመነጭ የፖለቲካ አመራርነት ብስለት ይጎድለው እንደሆን እንጂ ይሄን ከማድረግ አኳያ አቅም አለው:: ለምሳሌ፣ እኔ ባለሁበት ኦሮሚያ ክልልን ብንወስድ በዞንና ወረዳ እስከ ቀበሌ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚቀመጡ አመራሮች በህዝብ አስተዳደር ልምድ ማነስና በፖለቲካው ካለመብሰል የተነሳ የውሳኔ ሰጪ አካላት ማነስ ይስተዋላል:: እነዚህ ደግሞ በመቀራረብ ወይም በጓደኝነት የመጡ እንጂ በህዝብ ተተችተውና ይሁንታ አግኝተው ስላልሆነ ነው:: ከዚህ ውጪ ግን እንደ ብልጽግና ፓርቲ እንዳየሁት ጥሩ ፕሮግራም ነድፏል:: ይህ ፕሮግራምም ኢትዮጵያም ብዝሃነቷን ጠብቃ አንድ የሚያደርጋት መሆኑንም ተመልክቻለሁ:: ባህርዳር፣ ጅግጅግጋ፣ ሐዋሳ፣ ሰመራ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጅማም ሆነ ነቀምቴ፣ ወዘተ. ያለው ብልጽግና ፓርቲም አንድ አይነት በሆነ አሰራርና ፕሮግራም የሚመራ መሆኑም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡
ለምን ከተባለ ብዝሃነትን አስጠብቆ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ያመጣልና ነው:: እኛም ለዛ ነው ፌዴራሊስት ብለን ከሶማሌውም፣ ከአፋሩም፣ ከአማራውና ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አንድ ላይ ሆነን ስንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊነትን ለመፍጠር ነው:: ለምሳሌ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ለምርጫ ሲቀርብ በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደረው የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ በራሱ አርማ ቢወዳደርም እንደ አገር የሚንቀሳቀሰው በጥምረቱ ዓርማ ጥላ ስር ሆኖ ነው:: ስለዚህ ሁላችንም ማድረግ ያለብን የነበረብን በጋራ ነው:: ሆኖም ወደ 20 የሚሆኑት የጥምረቱ አባላት ምርጫውን አናካሂድም እያሉ ባለበት ሁኔታ ህወሓት ለብቻው ይሄን ውሳኔ ማሳለፉ ተገቢም ትክክልም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰው ሊመርጠን የሚችለው ሰላምና ጤነኛ ሆኖ ሲኖር ነው:: አገርም ተማምኖ መሄድ ሲችል ነው:: ካልሆነ በጀብደኝነት ተነስቼ ምርጫ ላካሂድ ብል አያዋጣም:: እኛም ይሄን ስለምንገነዘብ ለምን እኛን ሳታማክሩ መግለጫ ሰጣችሁ ብለንም ጠይቀናል:: ሆኖም ይህ የግሌ ነው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አይመለከታችሁም የሚል ሀሳብ ይዞ ነው የመጣው:: እኛም በበኩላችን የስብስቡ አባል እስከሆናችሁና የጋራ ስምምነት እስካለ ድረስ መፈጸም ያለበት በጋራ እንጂ በአንድ ፓርቲ የግል ፍላጎት አይደለም፤ አካሄዱም አንድነት አያመጣም፤ ምክንያቱም፣ ሶማሌው ለብቻ አንድ ሲል፣ አፋሩም ሌላ ሲል፣ ኦሮሞውም ለብቻው ሌላ ሲል ነገሮች ልክ አይመጡምና ምርጫውን ማካሄድ አትችሉም በማለታችን በመካከል ጭቅጭቅ ነበር:: የአዲስ አበባው ስብሰባ መሰረትና አንዱ ዓላማ በዚህ መልኩ ከጥምረቱ አቋም ውጪ ህወሓት ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ የወሰነው ግላዊ ውሳኔ ተገቢም ትክክልም አለመሆኑን ለመግለጽ ነው::
አዲስ ዘመን፡- በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ከህወሓት ጋር በጥምረት በቆያችሁባቸው ጊዜያት ቀደም ሲል ከውጭ ስትሰሙትና ስትገምቱት ከነበረው አንጻር ስለ ህወሃት ባህሪና እውነተኛ ማንነት ምን የተለየ ነገር ተገነዘባችሁ?
አቶ ደረጀ፡- እውነት ለመናገር፣ ከህወሓት የተረዳነው ባህሪ አንዱ፣ ህወሓት ማለት የተወሰኑ ቡድኖች ናቸው:: የተወሰኑ ቡድኖች ብዬ ስል የትግራይ ህዝብ ወይም በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ተማሪውም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍልን ስታይ ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም:: ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ጨምሮ ሌሎችም የትግራይ ክልል ክፍሎችን ባስጎበኙኝ ወቅት ተመልክቼ ተገንዝቤያለሁ:: በእነዚህ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በነበረኝ ጉብኝት የተመለከትኩት እና አንዳንዴም አማርኛ የሚናገሩ/የሚችሉ ሰዎችን አነጋግሬ እንደተረዳሁት፤ ህወሓት ከህዝቡ ጋር የለም:: ምናልባት የተወሰነ ህዝብ ነው ከህወሓት ጋር ያለው፡፡ ይሄ የተወሰነ ህዝብ ደግሞ በመቐሌ ከተማ እና ዙሪያዋ ያሉ ጥቂት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ ሌላው ቀርቶ ወደ አድዋና አክሱም ስንሄድ እውነት ለመናገር ህዝቡ የሚያሳዝን ህዝብ ነው:: ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ ህዝብ አንደኛ፣ በአሁን ጊዜ በዚህ ዘመን ለእግሩ እንኳን ጫማ የሌለው ህዝብ ነው:: ልብስ በረከሰበት በዚህ ወቅት ልብስ እንኳን መልበስ ያልቻለ ህዝብ ነው:: ይህ ደግሞ ጥቂት የህወሓት አመራሮችና አባላት ገንዘቡንም ለራሳቸው፤ አገሩንም የራሳቸው አድርገው እንደያዙት የሚያሳይ ነው፡፡ እንዳየሁት ከሆነ ህዝቡ መፈናፈኛ ስላጣ ነው ዝም ያለው:: ለዚህ ደግሞ ወደ ዛላንበሳ በሄድኩበት ወቅት ያነጋገርኳቸው አንድ አዛውንት ያጫወቱኝ ትልቅ አብነት ነው:: እኚህ አዛውንት እንዳጫወቱኝ፣ እዚሁ ነው:: ፌዴራሊዝም ስንልም የጋራ አስተዳደር ማለታችንም ነው:: ህወሓት ግን የእኩል አስተዳደር ብሎ ነገር የለውም:: ህወሓት የበላይነቱን ለማንጸባረቅ ብቻ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: የህወሓት አመራሮች ቦረና ያለውን ከብት አርቢ ነው፤ ሶማሌ ያለውን እንዲህ ነው እያሉ ከመናገር ውጪ፤ ቦረና ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ ሶማሌ ያለውም ራሱን ለማስተዳደር ይችላል፤ እንዲሁም የአካባቢውን ልማት መምራት ይችላል ብሎ የሚያስብ ቡድን አይደለም:: የራሱን የበላይነት ብቻ ለማንጸባረቅ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው:: ይሄን የበላይነቱን ለማረጋገጥም በየቦታው የራሱን የስለላ መረብ በመዘርጋት የሚሰራ ቡድን ነው፡፡ ፌዴራሊዝም ማለትኮ የመጀመሪያው ጉዳይ ራስን ማስተዳደር ነው:: በራስ መዳኘት ነው:: በራስ ቋንቋ መማር ነው:: ህወሓት ግን ያንን ለይምሰል ይናገር እንጂ ውስጥ ገብተን ስናየው የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚጨፈልቅ ቡድን ነው:: ይሄንን መብት ጨፍልቆም እሱ እንዴት መግዛት እንደሚችል የሚያስችለውን የወጥመድ መረብ የሚዘረጋ ነው:: ለዚህ ደግሞ በስለላ መረብ በጣሙን የተሳሰረ ነው:: በሆቴልም ሆነ በየትም ያለ ሰራተኛን በዚህ መረብ ውስጥ በማስገባት የስለላ መረቡ አባል አድርጎታል:: ከዚህ አንጻር ለምሳሌ እኔ በጅማ ወይም ኢሉባቦር አካባቢ ሄጄ አንድ ነገር ስፈጽም የህወሓት ሰላዮች እዛው ስላሉ ወዲያው መረጃው ይደርሰዋል:: ስለዚህ እኔ በጥምረቱ ውስጥ ካለሁት ሰው ይልቅ እነርሱን ይቀበላል:: ይህ ደግሞ የፌዴራሊዝሙን ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለውን የሚያፋልስ ነው፡፡ የዚህ ጨፍላቂነቱ ማረጋገጫ የሚሆነው ደግሞ፤ እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎችና ምርጫ አናካሂድም ሚሉበት ወቅት እርሱ አካሂዳለሁ ማለቱ የራሱን የበላይነት ለማንጸባረቅ የሚያደርገው ድርጊት ነው:: ከዚህ ባለፈ ስለ ህዳሴው ግድብ ያገባናል ብለን ሁላችንም ፓርቲዎች ስንናገር፤ ስለሱ ጉዳይ መንግስትን እንጂ እኛን አይመለከትም ማለቱ ነው:: ይሄን የሚል ድርጅት ደግሞ የፌዴራሊዝም ጠበቃ ሊሆን አይችልም:: ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት ከዳር እስከዳር ያሉ የፌዴራል መንግስቱ አባል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ያሉ ህዝቦች ፕሮጀክት ሆኖ ሳለ፤ ይሄን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ስለሆነው ግድብ አያገባንም ብሎ መናገር አግባብነት የሌለው፣ ስለፌዴራሊዝም የማያስብና የራሱን ኑሮ ብቻ ለማንቀሳቀስ የሚጥር ድርጅት መሆኑን ነው የተረዳሁት፡፡
አዲስ ዘመን፡- እርሱ ከውጪ ሆነው ሲያዩት እና በውስጡ ሆነው ሲያዩት ስለ ህወሓት ከተገነዘቡት አንጻር፤ የትግራይ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስለ ህወሓት ሊያውቁት ይገባል ብለው የሚነግሩትና የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- አንደኛ ለትግራይ ህዝብ ነው መልዕክት የማስተላልፈው:: ይሄውም ህወሓት ላለፉት 40ም ይሁን 50 ዓመት ታግሏል:: አንድ ትግል ደግሞ ወደ ህዝቡ ሰርፆ ይገባና ያድጋል፤ ያለበለዚያ ደግሞ ይከስማል:: አሁን በህወሓት ላይ የምናየው ይሄንኑ ነው:: ምክንያቱም ላለፉት 45 ዓመታት የዘለቀው የህወሃት ትግል የጉዞ ምዕራፉ ወደ መጠቃለሉ እንደመሆኑ መጠን፤ አሁን ላይ የትግራይ ወጣት የህወሓትን ወቅታዊ አካሄድ አይቀበለውም:: ህዝቡም አሁንም በድህነቱ ያለ እንደመሆኑ ከድህነት መውጣትን ይፈልጋል:: ምክንያቱም ህወሓት የዘረፈውን ወደ አውሮፓና መሰል አገሮች ከማሸሽ የዘለለ ለህዝቡ የሰራለት ነገር የለም:: ስለዚህ በተለይ በትግራይ ያለው የገጠር ህዝብ ስለ ህወሓት መሰሪነትና ተንኮል በደንብ ተረድቷል:: የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የሚያደርገውንም አካሄድ ተገንዝቧል:: ይሄን የተገነዘበ ህዝብ ደግሞ ህወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል:: የትግራይ ተወላጆችና የትግራይ ህዝብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል:: የትግራይ ወጣቶች፣ የትግራይ ምሑራን፣ በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ህወሓትን በቃህ ሊሉት ይገባል:: ለዚህ ደግሞ አንድም፣ ላለፉት 45 ዓመታት ያደረጋቸውን በማሰብ፤ ሁለተኛም አንድ ነገር የተወሰነ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚያቆም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ የህወሓትን አመራሮች እዚህ ጋር በቃችሁ ሊሏቸው ይገባል፡፡ ለምን ቢባል፣ እነዚህ አመራሮች የራሳቸውን ሀብት አካብተዋል:: ይህ ሀብት ደግሞ በመቐሌ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ጭምር ከህንጻ እስከ ተሽከርካሪ የሚገለጽ ሀብት ነው:: በክልሉ ደግሞ ለእለት ጉርሱም ሆነ ለእግሩ ጫማ እና ለሰውነቱ ልብስ መለወጥ ቀርቶ ማሟላት ያቃተው ህዝብ (በተለይ ገጠሩ) ተፈጥሯል:: እናም እነዚህ አመራሮች እውነትም ለዚህ ህዝብ ታግለንለታል ካሉ ያ ህዝብ ነጻ መውጣት ነበረበት:: ቢያንስ ትንሽ እንኳን መሻሻል ማሳየት ነበረበት:: ስለሆነም እኔ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ ልሂቃንና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የማስተላልፈው ይሄ [ገጽ 14 አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም] ለህዝቡ የጠቀመው ነገር የለምና ለህዝቡ የሚጠቅም ፓርቲ ማግኘት ስላለባቸው ለእርሱ የሚያደርጉት ድጋፍ ማቆም መቻል አለባቸው:: ምክንያቱም ይህ ፓርቲ ድጋፍ እያጣ አሁንም ወደ ከተማ የተሰበሰበ እንደመሆኑ፤ አሁን ያለውና የቀረውም ማቆም አለበት:: ይሄን በማድረግም ለራሳቸው የሚበጀውን ማሰቡ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በየክልሉ ተበትነው ያሉም ሆኑ በውጭ አገራት ያሉ የትግራይ ተወላጆችም ለህወሓት የሚያደርጉትን ቆም ብለው ማሰብ መቻል አለባቸው:: በሚያደርጉት ድጋፍ በአገሬ ላይ ምን ለውጥ መጣ? ምንስ ታየ፣ የትስ ደረሰ? ማለት አለባቸው:: ህወሓት 27 ዓመት ኢትዮጵያን ሲገዛና ሀብቱን እንደፈለገው ሲያሽከረክር ለእኛ ለትግራይ ህዝቦች ምን አደረገ? ብለው ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው:: ምክንያቱም እነዚህ ቡድኖች ዛሬ ችግር ሲመጣ ወደዛ ተሰበሰቡ እንጂ አካባቢውን እንኳን ሄደው አይተው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው:: ለዚህ ምሳሌ ለመጥቀስ ያክል፤ ክልሉን ባስጎበኙኝ ጊዜ ከተመለከትኳቸው አከባቢዎች አንዱ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትውልድ አካባቢ ነበረ:: በወቅቱ ስንጎበኝ እርሱም አብሮን ነበር:: የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ እንደሰማሁት ግን አምባሳደር ስዩም ከዛን እለት በስተቀር እንደማንኛውም ሰው በቴሌቪዥን ከማየት ውጪ በአካል አይተውት እንደማያውቁ ሲገልጹ ነበር፡፡ እናም በዚህ መልኩ አካባቢያቸውን በልማት ማገዝ ቀርቶ በአካል ሄዶ መመልከት ሳይችሉ የኖሩ አመራሮች፣ ዛሬ ችግር ሲገጥማቸው ወደ ህዝቡ ገብተው ህዝቡን ለሌላ ጭንቀት ይባስ ብሎም ከሌላው ህዝብ ለመነጠል የሚያደርጉትን ጥረት በግልጽ ይታያል:: እነርሱ ሲደላቸው እርሱ ሲቸገር የነበረው ህዝብ በእነርሱ ሴራ ዛሬ ከእነርሱ ጋር ተጨፍልቆ እንዲታይ እያደረጉትም ይገኛል:: እናም በክልሉ ያለውም ሆነ በሌሎች ክልሎች ብሎም በውጭ አገራት ያለው የትግራይ ተወላጅ ይሄን ሊያውቁ፤ ለህዝቡ ምን አደረገለት ወይም ምን አደረገበት ብለው ሊመረምሩ እና እነዚህን ግለኛ አመራሮች በቃ ሊሏቸው፤ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ሁሉ የሚፈልገውን ፓርቲ ደግፎ የነጻነት አየር መተንፈስ መቻል አለበት፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገንዘብ የሚኖርባቸው ደግሞ፤ የትግራይ ህዝብ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊና ትክክለኛ አካሄድ የሚሄድ ህዝብ መሆኑን ነው:: ዛሬ ላይ የትግራይን ህዝብ እገነጥላለሁ ብሎ የሚፎክረው ህወሃትም የግል ስሜትና ፍላጎቱን እንጂ በህዝቡ ፍላጎትና ድጋፍ እንዳልሆነም ማወቅ ይኖርበታል:: ለዚህ ደግሞ ህዝቡ ወጥቶ የድጋፍ ድምጽ እንዲሰጥ ይደረግ ቢባል እንኳን አምስት በመቶ እንኳን አያገኝም:: ይሄንንም በክልሉ ቆይታዬ በነበረኝ ጉብኝት ከተለያዩ አካላት (ምሑራንና ህዝቡን ጨምሮ) ባደረኩት የሀሳብ ልውውጥና ውይይት መገንዘብ ችያለሁ:: ህዝቡ ለህወሃት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ የሚሰጥ እና ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡ ህወሓትም ቢሆን እንደሚያወራው ለብሔር ብሔረሰቦች የሚሰራው ስራ የለም:: ይልቁንም ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ማስቀጠያ በሚያመች መልኩ እንጂ ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለክልሉ የተሻለ እድገት ሲል ያከናወነው ነገር አይታይም:: ለዚህ ማሳያው ደግሞ በትግራይ ውስጥ በክልሉ ከተወለዱ ህዝቦች እና ጥቂት የመንግስት ስራን ማዕከል አድርገው ካሉ ዜጎች ውጪ በትግራይ የሚኖርም፤ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖረውም አለመደረጉ ነው:: ለምሳሌ፣ በክልሉ አንድም ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር ሆቴል ያለው፤ ፋብሪካ የከፈተም የለም:: በአንጻሩ በሌሎች የክልል ከተሞችና ክልሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በሆቴልም ሆነ በሌሎች በርካታ ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ይገኛል:: በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው የማግለል ተግባር ግን የህወሓት ስራ ውጤት እንጂ የህዝቡ ፍላጎትም ተግባርም አይደለም:: በዚህም ዛሬም ቢሆን የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ ያለ፤ የነጻነት አየርን በወጉ ያላጣጣመና በአፈና ውስጥ ያለ፤ ዛሬም ቢሆን ከስጋት ያልተላቀቀ ህዝብ ነው:: ዛሬም እንደሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የፈለገውን የመደገፍ ፍላጎት ያለውና ከተወሰኑ የህወሓት ቡድኖች አፈና መውጣትን የሚናፍቅ ህዝብ ነው:: ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ህዝብም ለህወሓት ባዶ ፉከራ ሳይሆን ለዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ የህዝቡን እውነት ማድመጥ ይኖርበታል:: ህወሓት እንደሚለውም ሁሉም ትግሬ የህወሓት አባል ወይም ደጋፊ ነው ብለው ማሰብም የለባቸውም:: በአንጻሩ ሁሉም ትግሬ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው ማሰብ፤ ንጹሁን ህዝብም ከሰላዩና ዘራፊው ለይተው ማየት አለባቸው:: ምክንያቱም ዛሬ ከህወሓት ጥቂት ቡድኖች ጋር ያሉት አንድም እነዚሁ የቡድኑ አባላት፤ ሁለትም ከህወሓት ጋር በፈጠሩት ትስስር እርሱንም መከታ አድርገው ሲዘርፉና የሰውን ንብረት ጭምር ሲበዘብዙ የነበሩ ቡድኑን ከተውት ያላቸውን የሚያጡ የሚመስላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ፡፡
አዲስ ዘመን፡- አሁን ላይ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገለጻል? ምንስ ይፈልጋል?
አቶ ደረጀ፡- አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ጉዳይ ስናይ የታየውን አገራዊ ለውጥ/ሪፎርም ተከትሎ አገር እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ነው:: አገር ያለ መሪ ልትኖር ስለማትችልም ይህ መሆኑም ያለበት ነው:: በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከሰተ:: ይህ በሽታ ሲገባ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጠው ለህዝብ ነው እንጂ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም አስተዳደር ወይም ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚንስትርነት አይደለም:: ህዝቡ ደህና መሆን ስላለበት መጀመሪያ ለህዝብ ጤንነትና ደህንነት ነው:: ሆኖም አሁን የፖለቲካ አሰላለፉን ስናይ በአብዛኛው አንድ ላይ እየተሰበሰበ ነው ያለው:: እኛም በዚህ መልኩ ሰብሰብ ማለታችን ይሄ አስፈላጊ በመሆኑ ነው:: ስለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታው ይሄንን ማድረግን ወይም ሰብሰብማለትን ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በዚህ መልኩ አንድ ላይ መምጣት ይገባል እንጂ፤ እኔ የመንደር ፖለቲካ አቋቁሜ ኢትዮጵያ ላይ እንደፈለኩ መጮህ አልችልም:: አንድ ላይ ከመጣንና ድምጻችን መሰማት ከጀመረ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆን አለብኝ:: የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኔ ወይም ስሆን ደግሞ ኦሮሞን አስደስቼ አማራን ማስከፋት የለብኝም፤ አማራን አስደስቼ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን ማስከፋት የለብኝም፤ ሁሉንም አንድ ላይ ነው ማየት ያለብኝ:: የእኛም ጥምረት ለዛ ነው ኢትዮጵያን በሙሉ ያቀፈውና በሁሉም ክልሎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው:: ይህ ደግሞ አንድ ቦታ ላይ ለሚደርስ ችግርና ተጽዕኖ ሁላችንም ተጠያቂ ነን፤ ሁላችንም ይመለከተናል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው፡፡ በመሆኑም በአገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ አመራር በያዘው አካሄድ አገር አቀፍ ሆኖ ቢንቀሳቀስ ጥሩ ነው:: በዚህ እንቅስቃሴው ሌሎችንም ለማሳተፍ መሞከሩም ጥሩ ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲናገሩ “ልንረዳችሁ የምንችለው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ ላይ ስትሰባሰቡ ነው” ነው ያሉት:: በዚህ ንግግራቸው “ስትጨፈለቁ ነው” አላሉም፤ “ስትሰባሰቡ” ነው ያሉት:: ስትሰባሰቡ ግን እንደማንኛውም አገር አስርም እንሁን አምስትና አስራ አምስት በእውነት ለህዝብ የምንታገል፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ በዓላማ የምንገናኝ ሰብሰብ ማለት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፣ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ በኦሮሞነቴ ሶማሌውን እንደራሴ ነው ማየት ያለብኝ:: አንዱ አማራም አንዱን ደቡብ እንደራሱ ነው ማየት ያለበት:: በዚህ መልኩ አንዱ ሌላውን እንደራሱ ማየት እንጂ ነጣጥሎ ማየት የለበትም:: በዚህ መልኩ እንደ ኢትዮጵያዊነት ማየት እና በኢትዮጵያዊነት መታገል፤ በህዝባችን ላይ ፍትህ ሲጓደል ለፍትህ መቆም ይገባል:: የፖለቲካ መሪ ማለትም ለህዝብ መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ እንጂ ለመዝናናት የተዘጋጀ አይደለም:: ሞት እንኳን ቢመጣ እቀበላለሁ ብሎ የገባ ነው:: በመሆኑም በዚህ መልኩ ሞት እንኳን ቢመጣ ካንተ በፊት እኔ እቀበላለሁ ብዬ እስከገባሁ ድረስ በኢትዮጵያዊነቱ አንድ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰብሰብ ብለን በጋራ መስራት ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ ለአንዷ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ወይም ለሚኒስትርነት ቦታ ሁሉም ሊደርስ አይችልም:: 110 ሚሊዬን ህዝብም ሆነ 107 ፓርቲ ይሄን ማድረግ አይችልም:: ሆኖም 110 ሚሊዬኑም ህዝብ አገሬ ነው ብሎ በእኩልነት ያለመሳቀቅ ህግን አክብሮ እንደ ልቡ የሚኖርበትን አገር መፍጠር ይቻላል:: አሁን ያለው አመራርም ከልምድ የሚመነጭ የፖለቲካ አመራርነት ብስለት ይጎድለው እንደሆን እንጂ ይሄን ከማድረግ አኳያ አቅም አለው:: ለምሳሌ፣ እኔ ባለሁበት ኦሮሚያ ክልልን ብንወስድ በዞንና ወረዳ እስከ ቀበሌ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚቀመጡ አመራሮች በህዝብ አስተዳደር ልምድ ማነስና በፖለቲካው ካለመብሰል የተነሳ የውሳኔ ሰጪ አካላት ማነስ ይስተዋላል:: እነዚህ ደግሞ በመቀራረብ ወይም በጓደኝነት የመጡ እንጂ በህዝብ ተተችተውና ይሁንታ አግኝተው ስላልሆነ ነው:: ከዚህ ውጪ ግን እንደ ብልጽግና ፓርቲ እንዳየሁት ጥሩ ፕሮግራም ነድፏል:: ይህ ፕሮግራምም ኢትዮጵያም ብዝሃነቷን ጠብቃ አንድ የሚያደርጋት መሆኑንም ተመልክቻለሁ:: ባህርዳር፣ ጅግጅግ፣ ሐዋሳ፣ ሰመራ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ጅማም ሆነ ነቀምቴ፣ ወዘተ. ያለው ብልጽግና ፓርቲም አንድ አይነት በሆነ አሰራርና ፕሮግራም የሚመራ መሆኑም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ለምን ከተባለ ብዝሃነትን አስጠብቆ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ያመጣልና ነው:: እኛም ለዛ ነው ፌዴራሊስት ብለን ከሶማሌውም፣ ከአፋሩም፣ ከአማራውና ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አንድ ላይ ሆነን ስንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊነትን ለመፍጠር ነው:: ለምሳሌ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ለምርጫ ሲቀርብ በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደረው የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ በራሱ አርማ ቢወዳደርም እንደ አገር የሚንቀሳቀሰው በጥምረቱ ዓርማ ጥላ ስር ሆኖ ነው:: ስለዚህ ሁላችንም ማድረግ ያለብን ማድረግ የሚገባንን ነው:: እናም ህብረ ብሔራዊ የሆነ ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ወደላይ እናውጣ የሚለውንማሰብ አለብን:: የወቅቱም ፖለቲካ በዚህ መልኩ መስራትና መተባበርን ነው የሚፈልገው፡፡ ይህ ካልሆነና በመንደር ካሰብን እንደ ህወሓት ተመልሰን እንገባለን:: እናም እንደዛ ማሰብ የለብንም:: እኛ የተለያየን ቢሆንም ለአንድነት ነው የምንታገለው:: ለአንድ ኢትዮጵያም ነው የምንታገለው:: እናም ይሄንን በጥንካሬና በአንድነት በሁላችንም ፖለቲከኞች ዘንድ መሆን ያለበት ነው እንጂ፤ እኔ ግዙፍ ነኝ፣ እኔ ትንሽ ነኝ፣ እኔ አገሪቷን መጠበቅ እችላለሁ፣ እኔ አገሪቷን ማረጋጋት እችላለሁ የሚለው አይሰራም:: ይሄ ቦታም የለውም:: ምክንያቱም አገር ከተበጠበጠ ይሄ ትርጉም የለውም:: በአገር ሰላም ከሌለ የትም ቢሆን ወልዶ ሊስም፣ ንብረት ሊያፈራም አይችልም:: በመሆኑም የወቅቱ ፖለቲካ ጎጠኝነትና መንደርተኝነትን መተው የሚጠይቅ ነው:: እኔም ይሄ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት ቢቀር ደስ ይለኛል፡፡
አዲስ ዘመን፡- እርሶም እንዳነሱት ወቅቱ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠትን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ምርጫ 2012 መራዘሙ ይታወቃል:: ሆኖም የምርጫውን መራዘም ተከትሎ ህወሓት ምርጫው መካሄድ አለበት ሲል፤ ሌሎች ኃይሎች ደግሞ የሽግግር መንግስት መመስረት አለበት ሲሉተደምጧል:: እርሶ በዚህ ላይ ያለዎት እይታ ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- እኔ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫው መራዘም አለበት ከሚሉት ቡድን ነኝ:: ምክንያቱም ምርጫ የሚመርጠን ዛፍ ቅጠሉ አይደለም፤ ሕዝብ ነው:: ህዝብደግሞ ሊመርጠን የሚችለው ጤና ሰላም ሲሆን፤ እንደልቡ ወጥቶ መግባት ሲችል ነው:: ልጁን እንደ ልቡ ማሳደግ ሲችል ነው:: እኔም የምመርጠው ህዝብ ለማስተዳደር ነው እንጂ መሬቷን ብቻ ለማስተዳደር አይደለም:: ህዝብ ለማስተዳደር ደግሞ ህዝቡ ሰላም ሆኖ እኔን መምረጥ መቻል አለበት:: ይሄን መሰረት በማድረግም ነው እኔ ምርጫው ይራዘም ከሚሉት ውስጥ የሆንኩት፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ (ኦነን)ም የወረርሽኙን ዓለማቀፋዊ ሁነቱን በመመልከትና እንደ ስፔንና ጣሊያን ባሉ አገራት የተስተዋለውን የሰው ልጆች እንደ ቅጠል መርገፍ በማየት ገና ቫይረሱ በኢትዮጵያ እንደተከሰተ ነው ችግሩ በኢትዮጵያ እንዳይከሰት በማሰብ ምርጫው መካሄድ የለበትም ቅድሚያ ለህዝብ ደህንነት ሊሰጥ ይገባልና መራዘም አለበት የሚል አቋሙን ያሰማው:: አሁን ላይ ደግሞ ቫይረሱ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው:: ይህ ሂደት ደግሞ በከተሞች ያለውን ያክል የጤና መሰረተ ልማት በሌለው ብሎም ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ባለበት የገጠሩ ክፍል ከገባ ደግሞ አደጋው የከፋ እንደሚሆን እሙን ነው:: ትልቁ ስጋትም ይሄው ነው፡፡ ወረርሽኙ ወደገጠር እንዳይገባ ደግሞ በጸሎት ጭምር ፈጣሪን መማጸን ይገባል:: ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማስገንዘብ እና ገበያ መውጣት ቢያስፈልገው እንኳን ሁሉም ከመሄድ ይልቅ የየሰፈሩን ሰብሰብ እያደረገ አንድ ሰው ገብይቶ እንዲመለስ በማድረግ ራሱን እንዲጠብቅ ማስቻል ይገባል:: ይሄን በሃላፊነት የሚመራ መንግስት አስፈላጊ እንደመሆኑም ምርጫው ተራዝሞ አሁን ያለው መንግስት ምርጫ እስኪካሄድ መቆየትም ግድ የሚለው ተግባር ነው:: እኛም ታግለን አታግለንም በአሸናፊነት ብንመረጥ ሌላውም ፓርቲ ቢመረጥ ይሄንኑ ህዝብ ለማስተዳደር ነው:: ለዚህ ደግሞ አሁን ምርጫ ይካሄድ የሚለው ሀሳብ ጤነኛ ያልሆነ፣ ከራስ ጥቅም በዘለለ ለህዝብ ደህንነት ያላሰበ ፍላጎት በመሆኑ ተገቢ አይደለም:: እናም ቅድሚያ ለህዝብ ጤናና ደህንነት መሰጠቱ ተገቢ ነው፡፡ የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚለው ሀሳብም ለእኔ የብጥብጥ ሀሳብ ነው:: እንደ ገና ወደ ብጥብጥ እንመለስ ማለት ነው:: ምክንያቱም በዚህ የሽግግር መንግስት ውስጥ እነማን ናቸው የሚሳተፉት? 107 ፓርቲዎች ይግቡ ወይስ 107 ሽማግሌዎች ይካተቱ ወይስ 107 ምሑራን ይግቡ? የሚለው ጉዳይ ትልቅ የውዝግብ ምክንያት የሚሆን ነው:: እንደ እኔ ግን ከዚህ ሁሉ ውዝግብ አሁን ያለው መንግስት ወይም አመራር ላይ ያለው አካል የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ማሻገር ከቻለ መቀጠል የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም:: የሽግግር መንግስት እንደገና ማቋቋምም አስፈላጊ አይሆንም:: የሽግግር መንግስት ይቋቋም ማለት ወንበር እንያዝ ማለት ካልሆነ በስተቀር ትርፍ የለውም:: ምክንያቱም የሽግግር መንግስት የሚያስፈልገው ቢያንስ አገር ችግር ውስጥ ስትወድቅ እና ህዝቡ ባለው መንግስት አመኔታ ሲያጣ ሊተገበር ይችል ይሆናል እንጂ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ የሽግግር መንግስት አስፈላጊ አይደለም:: ሆኖም አሁን ያለው መንግስት እስከ ምርጫ ድረስ ሲቀጥል የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ መስራት፤ ይሄን በሽታ እንዴት እንለፈው በሚል ከጤና ሚኒስቴር የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተፈጻሚ በማድረግ፤ ተገቢውን የመከላከልና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት ስራን በማከናወን ህዝቡን ለማሻገር መስራት ይኖርበታል፡፡
አዲስ ዘመን፡- ከዚህ ጋር በተያያዘ ህወሓት ምርጫው መካሄድ አለበት፤ ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን ተግባራዊ የሚያደርግበት ነው:: በመሆኑም ሌሎች ክልሎችም ይሄንኑ ተገንዝበው ምርጫ ለማካሄድ መወሰን አለባቸው፤ ሲል ይደመጣል:: በዚህ ላይ የእርሶ እይታ ምንድን ነው?
አቶ ደረጀ፡- ህወሓት ምርጫ ይካሄድ ብሎ የሚያወራው ለህዝቡ አስቦ አይደለም፤ ለራሱ ነው:: ይሄም ለራሱ አፍኖ በያዘው አካባቢ ለቀጣይ አምስት ዓመት ቀጣይ ኮንትራት ለማግኘት እና ያንን ዋስትና ለመያዝ ነው:: ይሄ በዚህ ጊዜ ምርጫ ይካሄድ ማለት ደግሞ ለህዝብ አለማሰብ ነው:: ይሄንን አይነትና አባባልና አካሄድ ደግሞ ማንኛውም ክልል አይቀበለውም:: ይሄንንም ምናልባት ከህወሓት ጋር አብረው የቆሙት አራት ያክሎቹ ካልሆኑ በስተቀር በቀላሉ ከጥምረቱ አባል ፓርቲዎች መረዳት ይቻላል:: ለምሳሌ፣ ጎረቤቱ ያሉ የአፋር ፓርቲዎች ይሄን አካሄድ ስለማይቀበሉ እዚሁ አዲስ አበባ ነው ስብሰባ የመጡት:: ከእኛው ጋር ምርጫው መራዘም አለበት ብለው ወስነው ነው የሄዱት:: ከአፋር ድረስ የመጡትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች አባል ፓርቲዎች በዚህ መልኩ ምርጫው መራዘም አለበት ብሎ የጋራ ውሳኔ ላይ መድረስ ደግሞ ለራስ ስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ከማሰብ የሚመነጭ ቅድሚያ ለህዝብ ደህንነት መስጠት እንደሚገባ በግልጽ ያሳየ እርምጃ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ምርጫ የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለይበት ሁኔታ የለውም:: የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ እስከሆነ ድረስ ህወሓት ብቻውን ተነስቶ ምርጫ ላካሂድ ማለቱ ለምንድን ነው? የሚለው በራሱ መታየት ያለበት ነው:: ምክንያቱም ብቻውን ምርጫ ቢያካሂድ እንኳን ፓርላማ እዛ ሊቋቋም ነው ወይስ 38 የፓርላማ አባላት ከተመረጡ በኋላ እዚህ ያሉትን ተክተው አዲስ ሊገቡ ነው? ወይስ በትግራይ ብቻ ተወስኖ ሊቀር ነው? የሚለውን እንኳን በወጉ ያላገናዘበ ነው:: እናምአገራዊ ምርጫ ሲካሄድ አንድ እና የፌዴራል ምክር ቤቱን ጨምሮ እስከ ወረዳ ያሉ የምክር ቤት አባላት የሚመረጡበት ነው:: የምርጫ ዘመናቸውም አንድ ነው:: ይሄን ችግር ተከትሎ ምርጫው የተላለፈው እንደ አገር እንደመሆኑም፤ ሶማሌ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ደቡብ፣ ወይም ድሬዳዋ ለብቻዬ አካሂዳለሁ ሳይሉ ሁሉም ናቸው እንዲተላለፍ የወሰኑት፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የሚገባው እና ተገቢም እርምጃ ሲሆን፤ ለህዝቦቻቸው ደህንነት ያላቸውን ተቆርቋሪነት እና ከምንም በፊት ለህዝብ ጤንነት መጨነቃቸውን ያሳያል:: ከዚህ ባለፈም እንደ አገር የተላለፈ ውሳኔን አንዱ ክልል ተነስቶ እኔ ውሳኔውን አልቀበልም ስለዚህ በክልሌ ምርጫ አደርጋለሁ ሊልም አይችልም:: ቢልም ማድረግ አይችልም:: ምክንያቱም አካሄዱ ሰዋዊም ሆነ ህጋዊ መሰረት የለውም:: እናም እንደ አገር የተወሰነ ውሳኔን አንዱ እንደፈለገ ተነስቶ ካላካሄድኩ ብሎ ቡራ ከረዩ ካለ ይህ ለእኔ ሕገ ወጥነት ነው:: ከዚህ አኳያ የህወሓት ፉከራም ሆነ ነገ አንዱ ክልል ተነስቶ ምርጫ ላካሂድ ቢል ይህ ህገ ወጥ ከመሆኑም ባለፈ በህዝቦች ጤናና ደህንነት ላይ መቀለድ ነው:: እናም ይህ አካሄድ የቀልድ እና በህዝብ መጫወት፣ ከማን አለብኝነት የሚመነጭ ለህዝብም ክብር አለመስጠት ነው:: ከዚህ ባለፈ ግን ተግባሩ አጀንዳ ፈጥሮ የትግራይን ህዝብ አዕምሮ በዚህ የመያዝ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አንድ ምርጫ ቦርድ እንዳለ እና ምርጫውም በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ እየታወቀ ምርጫው እንደማይካሄድ እሙን ነው:: ይሄንንም ህወሓት በደንብ ያውቀዋል፡፡
[አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ገጽ 15]
https://vdocuments.mx/-oe-oe-f-oe-aa.html
eden wrote: ↑31 Oct 2020, 09:27
Hey guys
Need your input for my new research.
Here's a question for you to reflect on and answer.
If TPLF changes its long standing position and rejects
nation & nationalities based organization in Ethiopia, will this change your heart and mind on whether you oppose or support and how intensely you oppose or support it?
Would and should Abiy and Isayas work with TPLF if TPLF renounces
nation & nationalities based organization?
.