Page 1 of 1
የቤተ ጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ
Posted: 31 Oct 2020, 00:17
by Horus
በመላ ኢትዮጵያ የዘር ሽብር፣ ቀውስ፣ አናርኪ፣ ጥላቻ፣ ክፍፍል፣ ውድቀት፣ ዝቅጠት፣ ውዥንብር፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ብልህነት ፣ ኢንተለጀንስ በጠፋበት በዚህ ዘመን ጉራጌ ራሱን እንደ አለት በጸና ባባቶቹ ካልችርና እሴት ስረ መሰረት አንድንቱን እንደ ብረት እያገንታ፣ እያበረታ ነው !!! ኤቦ ለጉራጌ ባሊቆች፣ ለጉራጌ ሊቆች፣ ለጉራጌ ጉርዛዘ !!!
Re: የቤተ ጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ
Posted: 31 Oct 2020, 01:02
by Horus
አያችሁ በዊዝደም፣ በጥበብ መመራት ማለት ይህ ነው ። እስቲ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ ። ትግሬ ተክፋፍሏል ። አማራ ተከፋፍሏል፣ ኦሮሞ ተከፋፍሏል ፣ የጎሳ ክልል፣ ጎስኘት ራሱ ጎሳውን ነው የሚከፋፍል ። የጉራጌ ወጣቶች ክልል እንፈልጋለን ብለው ሲነሱ እንደ ሌሎቹ ክልሎች ያገሩ አዋቂ፣ ባሊቅ፣ ዋይዝ ፣ ጉሩዞች በወጣቱ አልተነዱም ። ወጣቱን ሰብስብው የዚህ ንቅናቄ ሁሉ ቁልፍ አላማ ምን እንደ ሆነ አስተማሯቸው፤ እሱም የጉራጌ አንድነት እና የጉራጌ ስላም መሆኑን!!! ይህ ነው የሰከነ ሕዝብ፣ የሰክነ ካልቸር ማለት ። በጉራጌ ሁሉ ያሉትን ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ክቡር ስርዓቶችን ስብስበው በአንድ ጉባኤ አቆሙና (ቤተ ጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ) መሪነት ለወጣቱ አዘዙ ። አሁን ሂዱና ለጉራጌ ራስ ገዥነት ታገሉ አሉ ። ልጅ የሚመራው ባባቱ ነው እንጂ የተገላቢጦሽ አይደለም፤ ያውም ከሊስትሮ ተነስተው ፎቅ የሰሩ ሽማግሎች ባሉበት ቤተ ጉራጌ !!!