ይድረስ ለቀድሞ የወያኔ አመራር ቡድን አባሎች: አክሱም ሆቴል: መቀሌ፡ ትግራይ ክልል: ኢትዮጵያ!
Posted: 18 Oct 2020, 17:06
መንግስት የአይናቸሁ ቀለም አላማረኝም ካለ የፀጥታና ሌላ ምክንያት ሳያስፈልግ ኤርትራውያን ከሀገር መውጣት አለባቸው"፡ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ግልጽ ደብዳቤ
ክፍል ሥስት፡ ሰባ ስድስት ሺህ (76,000) ንፁሀን ኤርትራዊያን ንብረታቸውን ቀምታችሁ በግፍ ከሃገር ኢትዮጵያ እንዲወጡ ማድረጋችሁ
1. የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተከሰተበት ማግስት ሰባ ስድስት ሺህ (76,000) ምንም በደል ያልፈጸሙ ንፁሃን ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸውን ትውልደ-ኤርትራውያንን ከቤተሰቦቻቸው (ባል ከሚስትና ከልጆች) ለያይታችሁ፡ ለብዙ ዓመታት ሰርተው ያፈሩትን ሃብት ቀምታች፡ ለብዙ ዓመታት በሞያቸው ከሚስሩብት መሥርያ ቤት አውጥታችሁ፡ ከሰላማዊ ኑሯቸው አፈናቅላችሁ ፡ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ እንዲባረሩ አደረጋችሁ። ከነዚሁ አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉና የተዋለዱ፡ ትዳር መስርተውም ለሁለት-ሶስት አሰርተ ዓመታት በመከባብር ከህዘቡ ጋር በሰላም የኖሩ ናቸው።
2. በወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ፡ "የኢትዮጵያ መንግስት የአይናቸሁ ቀለም አላማረኝም ካለ የፀጥታና ሌላ ምክንያት ሳያስፈልግ ኤርትራውያን ከሀገር መውጣት አለባቸው" ያሉት አሳዛኝ ቃላት ኤርትራውያንን በጣም ያስቆጥና ያሳዘነ ሆኖ በፍጹም የማይረሳና ለትውልድ የሚተላለፍ ሆኗል፡፡ በተጨማሪ አቶ ገብሩ አስራት ለትግራይ ህዝብ ፡ “ምንም ያህል ጊዚ ይፍጅ፡ ምንም ያህል የሰው ህይወት ይከፈል የፈለግነውን ሳናገኝ (አስመራ ወይ አሰብን መያዝ ለማለት ነው?) ጦርነቱን እንቀጥላለን” ያሉት የጦርነት እምብልታ ነው። ይህ አርቆ የማሰብ የጎደለው የጥላቻ መልዕክት በእያንዳንዱ ኤርትራዊ ህሊና ውስጥ የተቀረጸ የማይፋቅ ትዝታ ነው፡:
3. በተለይ ድርጊቱን ዘግናኝ የሚያደርገው እንደጠላት ፈርጃችሁና ኢሰብዐዊ በሆነ መንገድ ያንገላታቹሃቸው በብዛት ሕፃናት፡ አካለ ስንኩላን፣ እርጉዞች፣ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ በሽተኞች አረጋውያን፣ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎችን መሆኑ ነው። ድርጊታችሁ በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ጃፓን የሆኑትን የጸጥታ ስጋት ናችው በሚል ስበብ የዜግነት መብታቸውን ገፋ ካምፕ ውስጥ ካስገባችው ጋር የመሳስላል። በዚሁ ጉዳይ አሜሪካ በዓለም ህብረተ-ሰብ ከፈትኛ ወቀሳ አጋጠሟት የታሪኳ ጥቁር ቀለም ሆኖባት ይኖራል። እናንተም በተመሳሳይ ተግባራችሁ የታሪክ ጠባሳ ጥላችሁ ማለፋችሁን መገንዘብ ያስፈልጋል።
4. ከኤርትራውያን የቀማችሁት ሀብት ዝርዝሩ ብዙ ቢሆንም የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች (ሆቴሎች፣ ህንፃዎች፣ ጋራዦች፣ ዳቦና ኬክ ቤቶች፡ የጫማ፣ የሹራብ፣ የመጠጥ ፋብሪካዎች፣ ግሮሰሪዎች፣ ቪላ መኖሪያ ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የጭነትና የቤት መኪናዎች)ና በብዙ መቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት በግል ባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ ያጠቃልላል፡፡ የመብት ተሟጓች ድርጅቶች ባደሩጉት ጥናት የተዘረፈው ንብረት በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት መሆኑን በጊዜው ዘግበውታል፡፡ የሚያሳዝነውና ይቅር የማይባለው ጉዳይ ግን
ከኤርትራውያን የተዘረፉትን የግል ድርጅቶችና ንብረቶች በመረከብ ተጠቃሚ የሆኑት አብዛኞቹ የናንተው የወያኔ የከፍተኛ ባለስልጣናት ቤተሰቦችና ከእናንተ ጋር ቅርብ ትስስር የነበራቸው የትግራይ ባለሀብቶች መሆኑ ነበር፡፡
5. የተባረሩት ኤርትራውያንና የኢትዮጲያ ዜግነት ያላቸው ትውልደ-ኤርትራውያን ኤርትራ ድንበር ሲደርሱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣንትና በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ወኔ በተሞላበት ሞቅ ያለ አቀባብል አደረገላቸው፡ በተፈጸመው ግፍ ቁጭቱን ብከፍተኛ ስሜት ግልጾ መላው ህዝብ ጎናቸው እንደሚቆም አረጋገጠላቸው። ኤርትራውያንን ለማሽማቀቅ የፈጸማችሁት እኩይ ድርጊት በአንጻሩ በውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩት ዞጎች በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜት እንዲነሳሱና ጸረ-ወያኔ አቋማቸው እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተውጻኦ አድርጓል ።
6. ለዚሁ ተጨባጭ ማስረጃ በወቅቱ በተለያዩ የኤርትራ ቋንቋዎች ከአስር በላይ የሚሆኑ ዜማዎችና ብዙ ድራማዎች ቀርበዋል፡፡ ከነዚህም በህዝብ ከፍተኛ ተወድጅነት ያተረፉትን ሁለት ታዋቀ የሆኑትን ብቻ ለመጥቀስ ዝነኛውና አንጋፋው አልአሚን አብደለጢፍ በትግረ ቋንቋ "ኤርትራዊነትን እንደ በደል የቆጠሩትንና ንፁህ ሕዝባችንን በግፍ ያባረሩትን ምን ጊዜም አንረሳቸውም" ሲል በተመሳሳይ አንጋፋውና ዝነኛው በረኸት መንግስትአብ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ማግስት በትግርኛ፡ "ኮብራ" በተባለው ዜማው "ማለሊት (ማርኪሲስት ሌንኒስት ትግራይ የወያኔ ህቡዕ ፓርቲ) "ንኤርትራ ዘጸመኩሞ ዕር፡ መሪሩኩም ሓቅነት ምስ ሰዓር፡ ስተይዋ'ምበር/ውሓጥውምብር አበይ ድሕር ዳሕር'የ" ይላል።[በግርድፍ ትርጉሙ ኤርትራ ላይ የጠመቃችሁት መራራ እሬ፡ ሃቅ በማሸነፉ መሯችኋል? የጠመቃችሁትን መራራ እሬ ጠጡት፡ ወዴት ማሸግሸግ ?)” ነው። ኤርትራውያን አርቲስቶች እነዚህና ሌሎች በርካታ ተወዳጅ ዘፈኖችና ድራማዎች ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን ድርሻችውን አበርክተዋል፡፡
7. ኤርትራ ዘጠኝ ብሄሮች ያላት ሀግር መሆኗን ወያኔ መቀበል ተስኗቹኋል፡፡ ከነዚህ ዘጠኙ ብሄሮች ውስጥ ሶስቱ (ትግርኛ ሳሆና ኩናማ) ብሄሮች በትግራይ ክልል ከሚገኙት ተመሳሳይ ብሄሮች ጋር የቋንቋና የዘርና የታሪክ ትስስር እንዳላቸው የማያጠያይቅ ሀቅ ሆኖ ግን ከተቀሩት ስድስቱ የኤርትራ ብሄሮች (ትግረ፡ አፋር፡ ቢለን፡ ህዳርብ፡ ናራና ራሻይዳ) ጋር የትግራይ ህዝብ ምንም የዘር ይሁን የቋንቋ ትስስር እንደሌላቸው መታወቅ ያለበት ጉዳይ ነው። በተመሳሳይ በኤርትራ የሚገኙት ሌሎች ብሄሮች በሱዳን፣ በጅቡቲና በየመን ድንበር ከሚገኙ ተመሳሳይ ብሄሮች ጋር የቋንቋና ባህልና ትስስር እንዳላቸው ግልጽ ነው፡፡ በነዚሁ ጎረቤት ሀገሮች ብዙ ኤርትራውያን እንደሚኖሩና በኤርትራም ብዙ የጎረቤት ሀገር ብሄሮች በመከባበር በሰላም እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ ዋናው ቁም ነገሩ ከነዚሁ ጎረቤት መንግስታት (ሱዳን የመንና ጅቡቲ) ጋር አለመግባባት ሲፈጠር "ኤርትራውያንን የዐይናችሁ ቀለም አላማረንምና ከሀገራችን ውጡ ብለው ግፍ የተሞላበት ድርጊት ሰላማዊ ሰዎች ላይ አልፈጸሙም፣ በተመሳሳይ በኤርትራም በኩል እንደዚሁ አልተደረገም! እንዲህ አይነት ሃላፊነት የተሞላበት ድርጊት ሰክን ያለ መንፈስ ካለውና አርቆ ማሰብ ከሚችል የሚጠበቅ ስለሆነ !!።
8. የብሄርና የእስላማዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች በማስታጠቅ የኤርትራ ህዝብ በብሄርና ሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዲጋጭ ለዓመታት በከፍተኛ ወጪ ብዙ ያልተሳካ ሙከራ አደረጋችሁ።ግን አልተሳካላችሁም፡ ምክንያቱም ኤርትራ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰማዕታት ከፍላ የተቀዳጀችውን ላአላዊነት ለማስከበርና አንድነቷን ለማስጠበቅ የብዙ ሺህ ዜጎችን መስዋዕትነት እንደገና በመክፍል ስላረጋገጥች ነው። የብሄር ብሄረሰቦችን መብት መጠበቅና ማረጋገጥ፡ የሁሉም ብሄሮች ቋንቋና ባህል እንዲዳብር ማድረግ፡ እንዲሁም የሃይማኖት እኩለትና መብቶች ማረጋጋጥ የአንድ አገር ዜጎች በእኩልነትና በመከባበር እንዲኖሩና ለሃገር ልማት በጋራ እንዲስሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አከራካሩ ጉዳይ አይደለም፡፡ የቋንቋና የዘር ክፍፍሉን የፖለቲካ መሳርያ አድርጎ በመጠቀም ህዝቡ እንዲድጋጭና ደም እንዲፋሰስ ማድረግ ግን በመሠረቱ መወገዝ ያለበት ነው፡፡ የብሄር-ብሄረስቦችን መብትና እኩልነትን ለማረጋገጥ በብሄርና ቋንቋ ላይ የተመሠረተ የክልል መንግስት ማቋቋምን አየጠይቅም !!
9. ከጥቂት ወራት በፊት አቶ አባይ ፀሐዬ፡ "የኤርትራ ህዝብ ወንድማችን ነው፡ ከኤርትራውያን ጋር እንደቀድሞው የቅርብ ግንኙነት እንፈልጋለን፡ የትግራይ ሕዝብ ቂሜታውን ረስቶታል፡ ሕወሓትም ረስቶታል፡ ምናለ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ቢረሱት” ያሉት በጣም አስገራሚ ነው። ባለፉት ሃያ ዓመታት የስልጣን ዘመናችሁ አንድም ቀን እንኳን ብላችሁት የማታውቁትን ቃላት በቅርቡ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግስት በለቀቃችሁ ማግስት እንዲህ ማለታችሁ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮሀ የሚያስብል አስቂኝ ነው። አቶ አባይ ፀሐዬ በመቀጠል “ከኤርትራ ጋር በቅርቡ የተደረገው የሰላም ስምምነት ሃሳቡን ያቀረብነውና ትልቅ ሚና የተጫወትነው እኛ ሕወሓት ነን፡፡ ቀደም ብለን ይህን የሰላም ጥሪ ያላደረግነው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ስላጋጠመንና እሱን ላይ ትኩረት በማድረጋችን ነበር” አሉን፡፡ የኤርትራ ሰማዕታት ሓውልትና መቃብር በቦንብ አፍረሳችሁ፤ ንጹሃን ኤርትራውያንን ከኑሯቸው አፈናቀላችሁ፡ ንብረታቸውን ቀምታችሁ በግፍ አባራችሁ ፡ እርሱት ማለት ከምን ይቆጠር ይሆን፡ እኛ ኤርትራውያን እኛ ላይ የፈጸማችህትን አሳዛኝ ድርጊት ፍጹም አልረሳነውም! እንዴት ይረሳል !!
10. በአቶ መለስ ዜናዊ ከፓርቲው ተባረው በውጭ ሃገር ለብዙ ዓመታት ሲኖሩ ከነበሩት የቀድሞው የአመራር ቡድን አባሎች የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃምና ጀ/ር ፃድቃን ወ/ትንሳኤ (እንዲሁም ጀ/ር አበበ ተ/ሃይማኖት) በ2018 (ኤ.አ) በኢትዮጲያ ሕዝብ ከፍተኛ ግፊት ቡድናችሁ ከስልጣን ለመውደቅ ሲንገዳገድ እሱን ላማዳን ነው መሰለኝ ዘው ብለው አገር ቤት መመለሳቸው ተሰማ። የሚገርመው በተመለሳችሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ በትግራይ ቴሌቪዥና በድምጺ ወያኔ ቀርብችሁ ስለ ትግራይ ሕዝብና በተለይ ስለ ወጣቶቹ የወደፊት ዕጣ ማውሳት ሲጠበቅብችሁ እሱን ወደ ግን ትታችሁ ስለኤርትራ ህዝብ በሶትና ስለወጣቱ ትውልድ በተደጋጋሚ መደስኮርችሁ ነው። ይህ ድርጊታቸሁ "ጽምብላሊዕ'ሲ ነብሳ ዘይከደነት መሬት ከደነት" የሚለውን የትግርኛ ምሳሌ አስታወሰኝ፡ [ግርድፍ ትርጉሙ ቢራቢሮ የራስዋን ገላ ሳትሸፍን መሬት ትሸፍናለች ነው)።
11. በርግጥ ለህዝባችሁ ተቆርቋሪ ከሆናችሁ፡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣትች ተስፋ በመቁረጥ አገር ለቀው ወደ የመንና ሳውዲ አረቢያ ሲሄዱ የሚያጋጥማቸውን ስቃይና ሰቆቃ በዓለም መገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ አይታችሁ ስለ ኤርትራ ወጣቶች ከመደስኮር ምነው በትግራይ ቴሌቪዥን ወይ ድምጺ ወያነ ስለነሱ ሰቆቃና መፍትሄው አልደሰኮራችሁ? ምናለ የልጆቻቹሁን የልድት ቀን ለማክበር በብዙ ሺህ ዶላር የሚፈጅ ውድ ኬክ ከወደ-ዱባይ አስመጥታችሁ ከመደገስ ይልቅ ለተቸገሩት የትግራይ ህጻናትና አረጋውያን ለቂጣ መጋገርያ የሚሆን ገብስ/ስንዴ ብታስገዙበትና ወገኖችህችሁን ብትረዷቸው ? በዕውነት ለህዝባችሁ ተቆርቋሪ ከሆናችሁ ባለፈው 27 ዓመታት ከሃገር ያሸሻችሁትና በውጭ ያስቅመጣችህትን በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመተውን የሀገር ሀብት ብትመልሱና ለትግራይ ወጣቶች ስራ ማቋቋሚያና ለትግራይ ሕዝብ መሰረተ ልማት መገንቢያ ብታውሉት እንደ በጎ ሥራ በተቆጠረላችሁ ነበር ! እናንተ ግን ይህን በጎ ሥራ ማድረግን ወደ ጎን ትታችሁ ስለ ኤርትራ ህዝብና ወጣቶች በቴሌቪዥናችሁ በተደጋጋሚ ብትደሰኩሩ እንደሌላው የበፊቱ ሙከራቸሁ ውጤቱ ዜሮ (በትግርኛ ባዶ) ስለመሆኑ በርግጠኝነት መናግር ይቻላል ፡፡
12. እናተም በቅርቡ ከውጭ የተመሳችሁት የቀድሞ የወያኔ አመራር ቡድን አባሎች በቅርቡ በጡረታ ከሥራ ከተሰናበታችሁ በኋል የሰላም ኑሮ ከመመረጥ ይልቅ "ጥርነት መፍጠር እንችላለን" በምትሉት ከንቱ ጉራ እንደ ሌሎቹ የቀድሞ አመራር ቡድን ጓዶቻችሁ ልጆቻቸሁንና የቅርብ ቤተሰቦቻቸሁን በአሜሪካ፣ አውስትራልያና አውሮፓ አስፍራችሁ የትግራይን ወጣት ከኤርትራ ጋር ለዳግማይ ጦርነትና አላስፈላጊ ከፍተኛ ደም መፋሰስ መጋበዛችሁ ይቅር የማይባል አላዛኝ ድርጊት ነው፡፡
13. በመሠረቱ ከኤርትራ ጋር ዘላቂ ሰላም ሳተፈልጉ የምትፈልጉ ለመምሰል የምታደርጉት የሕዝብ ግንኙነት ጭዋታ አንዴ "ሕዝብ ለሕዝብ" ቆይታችሁም "ሁላችንም አግአዝያን ነን" የምትሉት ምንም ፋይዳ አይኖረውም። በዚሁ ርካሽ ፕሮፖጋንዳ የሚታለል ኤርትራዊ ይኖራል ብሎ ማሰባችሁ የዋህነት ነው ፡፡ የኛ የኤርትራውያን ፍላጎት ከኢትዮጵያ ህዝብ ከትግራይ ክልል ህዝብ ጭምር የመልካም ጉርብትናን መርህ የተመረኮስ ግንኙነት መመስረትና በሰላምና በመከባባር ለመኖር ነው። ስለዚህ የቀድሞው የእምቢታ አቋማችሁን ትታችሁ የትግራይ ህዝብ ከጎረቤት የኤርትራ ህዝብ ጋር በሰላምና በመከባብር እንዲኖሩ በዕውነት የምትፈለጉ ከሆነ በቅድሚያ የድንብር ኮምሽን ውሳኔ መቀበልና ከላዓላዊ የኤርትራ መሬት መውጣት ይኖርባቹሃል። ይኽን ታሪካዊ እርምጃ በመውሰድ ላለፉት ሃያ ዓመታት ያመለጣችሁን ዕድል ተጠቅማችሁ በሁለቱ መንግስታት መካከል ዘለቄታ ሰላምና መልካም ጉርብትና እንዲሁም በኤርትራና በኢትዮጵያ (ትግራይ) ህዝብ መካከል በሰላምና በመከባብር እንዲኖሩ የሚያስችል ታሪካዊ ምዕራፍ ትመርጣላችሁ የሚል ተስፋ አለኝ ። ሆኖም ግን ይኽን ቆራጥ ውሳኔ ለመውሰድ የናንተ ልበ ሙሉነትና አርቆ ማሰብን ሰለሚጠይቅ የመከሰት ዕድሉ ደካማ መሆኑን በሚገባ እገነዘባለሁ። "ትላንት የአይናችሁ ቀለም አላማረንም ብላችሁ ንጹሃን ኤርትራውያን ላይ ግፍ ፈጽማችሁ ስታበቁ ዛሬ የኤርትራ ህዝብ ወንድማ ለምትሉን መልሳችን "የፈጸማችሁትን ግፍ አልረሳነውም ! እንዴት ይረሳል !! የሚል ነው።
ሰዕረ ተስፋይ
ዋሽንግተን ዲ.ሲ.