ትልቁ በአብይ ዩኒቨርስ ያለው የጨለማ ዋሻው የዜግነት የግል መብትን የማያከበርና የማይከላከል ፌዴሬሽን መኖሩኑ ነው ፡፡ The biggest Black hole in Abiy’s universe
Posted: 14 Oct 2020, 20:14
ወያኔ ያዋቀረውን የፌደራል ስርአት በተመለከተ ይህ የአብይ ቪዲዮ በግልጽ ይስቀመጠበት ትንታኔ ነው ፡፡ ምንም እንኳን የወያኔን ፊደራሊዝም ምን እንደሆነ ያስቀመጥበት መንገድ የምናውቀውና ትክክል አገላለጽ ቢሆንም ፤ የአብይ አመለካከት ወይም ፍላጎት የወያኔን የጉጥ ፊደራሊዝም ለማጠናከር ነው፤ ይህ እንዲሆን የፈለገበትም ዋና ምክንያት እርሱ በሰከነ መልክ ኦሮሙማን አሽናፊ ሆኖ ጭፍላቂ ስርአት ለማድረግ ነው፡ እውነተኛ ፊደራሊዝም የግለሰብ የማይነኩ መብቶችንና ግዴታዎችን አስቀምጦ በሁሉም ፊደራል መዋቅር ውስጥ መንግስት ሊነካቸው የማይገቡ መብቶች መሆናቸውን አምኖ ፊዴሪሽኑን ካላዋቀረ ጉጠኞች የሚጫወቱበት የጎጠኝ፤አምባ ገነናዊ ስርአት ነው የሚሆነው ፤ ያለምንም ጥርጥር ፡ ምሳሌውን ስንመለከተው የሚያሳየውም ይሄንን ነው ፡ የኛን የፕላኔት ሲስተም እንደ ምሳሌ አድርጎ ጽሀይ (የፊደራል ሲስተሙ ) ከዚያ ደግሞ 8 ፕላኔቶች እንደ ፈዴራል ስቴት አድርጎ ነው ያስቀመጣቸው ፡ ለምሳሌ ስቴቶች ወደፌደራሉ በጣም ከተጠጉ ይቀልጣሉ ( በኦሮሞዎች የሚመራው የፊደራል መንግስት ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ ኦሮሞ እንደትቀልጥና በኦሮሞ እንደትዋጥ በአቤቤና በታከለ ኡማ ሲሰራ አብይ ግድ የለውም _ ማለትም መቅለጥ ያለባቸውና መቅለጥ የሌለባቸው ፕላኔቶች አሉ ማለት ነው) በጣም ከራቁ ደግሞ ከመህዋራቸው ለቀው ይወጣሉ ይለናል ፡፡ ግን ፊዴራል መንግስት ማለት በተለያዩ መውሃር ላይ የሚዞሩ የተለያዩ ፕላኔቶች አይደሉም ለምሳሌ ሁሉም የፌደራል ስቴቶች የግል ሰቦችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተመለከተ የማይዳፈሯቸው ወይም ህግ ሊያውጡባቸው የማይችሉባችው የህግ ዘርፎች አሉ ፡፡ የንግድ ግኑኙነትን በተመለከተ በየተለያዩ የፌደራሉ ስቴቶች ማህከል ኢኮኖሚያዊ ነጻ ገበያን የሚያስተጓጉሉ ህጎች በፊደራል ሲስተም ዉስጥ ሊወጡ አይችሉም ፡ በጀርመንም ሆነ በአሜሪካ ፊደራል ሲስተም ውስጥ እነንኚህ በጭራሽ ስቴቶች ሊነኩት የማይችሉት ጉዳይ ነው፡፡ የፌደራል መንግስቱ በአንድ ስቴት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹ ፤ የስቴቱ የጸጥታ አውታሮች በዘር ማጥፋት ድርጊት ቢፈጽሙ ወይም ሲፍጸም አቅም እያላችው ህዝቡን ባይከላከሉ የፌደራል ስቴቱን ፍቃድ ጠብቆ ሳይሆን የሚገባው ስቴቱ ፍለገም አልፍለገም ገብቶ ዜጎችን ይከላከላል፡፡ አብይ ስለግለሰቦች የተወሰነ ነገሮችን ብሎል መስራት መኖር እንደመብታቸው ሳይሆን ልክ የክልሎች በጎ ፍቃድ አድርጎ ነው ያቀረበው ፡፡ ወደኋላ ሄደን ስናስታውስ አምስት የኦሮሞ ድርጅቶች እና በዚያ ግዜ የነበረው ኦዲፒ ስለአዲስ አበባ መግለጫ ሲያወጡ ፤ አዲስ አበባ የኦሮምያ ናት ግን ሌሎች መኖር ይችላሉ መብታቸው ተከብሮላቸው ነበር ያሉት ፤ አሁንም በአብይ አገላለጽ ግለሰብ ኢትዮጵያዊያን በሄዱበት በሚኖሩበት እንደዜጋ በህግ የተረጋገጠ መብት ኖሯቸው ሳይሆን የሚኖሩት በፊደራል ስቴቱ ውሳኔና ፍቃድ ነው ፡፡ በተላያየ መህዋር ላይ የሚዞር ፕላኔት ላይ ስለምንኖር ይህ አስተሳሰቡ በጭራሽ አያስገርምም፡፡ እንደማጠቃለያ በአሁኑ ሰአት በአማራዎች ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋ ፤ የመንግስት ግድየለሽነትና ፤ የወንጀል ሸፋፋኝነት አውቆ የሚሰራ ሴራ ነው ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አሁን በቅርብ ደግሞ ኢዜማ ላይ የሚደረገውም የዚሁ ኢትዮጵያዊያንንና አማራን በማዋከብ ሀይልን ለማጠናከር የሚደረግ ሴራ ነው ፡፡ ነገር ግን ከሁሉም በላይ የአማራ ብልጽግና የተጠሪነትና የሀላፊነት ወስዶ የሚወክለውን ህዝብ አለመከላከል መቻሉ የኦሮሙማን ጥጋብ መስመር እየሳተ እንዲመጣ አድርጎታል ፡፡ ነገሩ ወደ ግጭት እንደሚያመራ ምንም ጥርጥር የለውም ፤ አንዴ ሁለቴ ማታለል ይቻላል ነገር ግን ሁል ግዜም ሁሉም ቦታ ማታለል አይቻልም ፡፡ ወያኔዎች በጣም የሚያሳዝኑ ፤ የማይለወጡ ፤ መድረቅን እንደ ርእዮት አቃም የያዙ ፤ ከመሰበር በቀር መታጠፍ የማይችሉ ስዎች ስለሆኑ ፤ እነርሱን ከማየት በቀር ምንም ማድረግ አይቻልም ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን የአብይን አፍ ፓርክ በማየት ከሚደነዝዙ ፤ ነገ የሚመጥውን ፤የሚጠብቃቸውን ከአሁኑ ለማሰወገድ የወገብ አጥንት ቢያወጡ ይሻላሉ ፡፡ አሁን አሁን አብይን ኢትዮጵያ ዝማሬ በድሮ ታሪክ ፍቅር ለተጠመዱ አማሮችና ኢትዮጵያዊያንን የማሸለብያ ማደንዘዣ ነው ፤